• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በሚያከናውናቸው ስራዎች የሀገሪቱን ስፋትና የህዝቡን ብዛት ማዳረስ አልቻለም ውስንነት አለበት ተባለ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በሚያከናውናቸው ስራዎች የሀገሪቱን ስፋትና የህዝቡን ብዛት ማዳረስ አልቻለም ውስንነት አለበት ተባለ፡፡በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው አቶ ደምሰው በንቲ ለሸገር ሲናገሩ ኮሚሽኑ በግጭት አፈታት፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመከላከል፣ በክትትል የምርመራ ስራዎችና ጥናቶች በሌሎችም ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ የሚሰራ ቢሆንም በሰው ሀይል እጥረት፣ በበቂ ክህሎት አለመኖር እና በአጠቃላይ በአቅም ማነስ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ማዳረስ አልቻለም ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ስምንት ክልሎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን ከፍቶ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዳይፈጠሩ ቢሰራም ያለበት የአቅም ውስንነት አብዛኛውን የከተማውን ሆነ የገጠሩን አካባቢዎች ማዳረስ ስላላስቻለው ይህንንና ሌሎችምን እክሎችን ለማስተካከል የሚረዳውን ጉባኤ እያካሄደ ነው ያሉት አቶ ደምሰው ይህንን ጉባኤ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች እያከናወኑት ይገኛሉ ነገም ጉባኤው ያበቃል ሲሉ ነግረውናል፡፡

በ2011 ዓ/ም በፖለቲካዊ ፣ በኢኮኖሚያዊ ፣ በማህበራዊ እና በባህላዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ስራ ለመስራትም ኮሚሽኑ ያሉበትን ችግሮች ከወዲሁ ለመቅረፍ ኮሚሽነሮቹ በጉባዔያቸው መላ እየፈለጉ ነው ተብሏል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers