ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና ቼንግዙ ከተማ በረራ ሊጀምር መሆኑን ተናገረ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና ቼንግዙ ከተማ በረራ ሊጀምር መሆኑን ተናገረ፡፡አየር መንገዱ ከመጪው ሰኔ ወር ጀምሮ በሣምንት ሦስት ጊዜ ወደ ቼንግዙ ለመብረር ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን ከላከልን መግለጫ ላይ ተመልክተናል፡፡ለበረራውም B 787 እና B 777 አውሮፕላኖችን እጠቀማለሁ ብሏል፡፡
ቼንግዙ የቻይና ሰባተኛ ትልቅ ከተማ ናት፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ ከሚጀምረው የቼንግዙ በረራ በተጨማሪ በሣምንት 10 ጊዜ ወደ ጓንዡ እና በሣምንት 6 ጊዜ ደግሞ ወደ ሆንግ ኮንግ በአሁኑ ሰዓት በመብረር ላይ ይገኛል፡፡አየር መንገዱ ወደ ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ የበረረው ከዛሬ 43 አመታት በፊት መሆኑን ሰምተናል፡፡
ንጋቱ ሙሉ