• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ኢትዮጵያ የባህር በር ባይኖራትም የባህር ሀይል እንደሚያስፈልጋት ተነገረ

ኢትዮጵያ የባህር በር ባይኖራትም የባህር ሀይል እንደሚያስፈልጋት ተነገረ፡፡ለአንዲት ልኡላዊት ሐገር የባህር ክልል መኖር ከሚሰጣት ጠቀሜታዎች ውስጥ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትሩፋቶች ተጠቃሾች ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ የቀድሞ የባህር ሐይል አባላት ማህበር ሊቀመንበር ኮማንደር ተስፋዬ ታደሰ ኢትዮጵያ የባህር በር የሌላት መሆኑ የባህር ሐይል ባለቤት ከመሆን አይገድባትም ባይ ናቸው…ቴዎድሮስ ብርሃኑ ዝርዝር አለው…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የባህር በር የሌላት ኢትዮጵያ

ለምንድነው የባህር ሀይል ለማቋቋም የፈለገችው በሚል ርዕስ ቢቢሲ አንድ ፅሁፍ አስነብቦ ነበር፡፡ ፅሁፉ በአፄ ሐይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ ባህር ሐይል ምክትል አዛዥ የነበሩትን የኮሞዶር ልዑል እስክንድር ደሰታን ፎቶግራፍ ይዞ ወጥቷል፡፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ስትለይ ኢትዮጵያ በቅፅበት የባህር በር ስላጣች የባህር ሐይሏን በተነች የሚለው ይህ ፅሁፍ ጉዳዩን በጥልቀት ይተነትናል፡፡

ፅሁፉን በመንተራስ ጌታቸው ለማ ያዘጋጀውን ማህሌት ታደለ እንዲህ ታቀርበዋለች…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል ባለፈው አመት ተከስቶ በነበረው ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ የማቋቋሙ ስራ አዝጋሚ ሆኗል ተባለ

ይህም በመሆኑ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች አሁንም በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ለኑሮ በማይመች ሁኔታ ኑሮአቸውን እንዲገፉ ተገደዋል ብሏል የፌዴራልና አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስቴር፡፡በሁለቱ ክልልች አዋሳኝ አካባቢ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ምክንያት ከተፈናቀሉ 1 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች መካከል ወደ ቀድሞ ቀያቸው የተመለሱት 277 ሺ ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡
ለመልሶ ማቋቋሚያ 15 ሺ ቤቶች እየተገነቡ መሆኑንም ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ዛሬ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው የመስሪያ ቤታቸውን የ11 ወር እቅድ አፈፃፀም ሲያቀርቡ እንደተናገሩት በኦሮሚያ ክልል 11 ከተሞች ተፈናቃዮችን መልሶ ለማስፈር 11 ሺ ቤቶች እየተገነቡ ነው፡፡ከመካከላቸው 6 ሺ ያህሉ ተጠናቀው 33 ሺ ሰዎች ወደ መጠለያዎቹ ገብተዋል ብለዋል፡፡በሶማሌ ክልልም 4 ሺ ቤቶች እየተገነቡ ሲሆን የ1 ሺ ቤቶች ግንባታ መጠናቀቁን ከሚኒስትሩ ሰምተናል፡፡

ይህም ቢሆን ግን የመልሶ ማቋቋም ስራው አዝጋሚ በመሆኑ ለኑሮ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ተፈናቃዮቹ ለመኖር መገደዳቸውን የፌዴራልና አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ለምክር ቤቱ አብራርተዋል፡፡በመሆኑም የፌዴራል መንግስት በሁለቱ ክልሎች ያጋጣሙ ችግሮችን በፍጥነት መፍታት ይጠበቅበታል ሲሉም አሳስበዋል፡፡ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መቀመጫ ካላቸው 547 የህዝብ ተወካዮች መካከል የዛሬውን 31ኛ መደበኛ ስብሰባ የተካፈሉት 305 ያህሉ ብቻ ናቸው፡፡ ከ240 በላይ የእንደራሴዎቹ ወንበሮች ባዶ ሆነው ታይቷል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት በምርቶችና አገልግሎቶች ላይ ዋጋ የጨመሩ ነጋዴዎችን ለመለየት ጥናት ተጀምሯል ተባለ

መረጃውን ከንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ሠምተናል፡፡በባለስልጣኑ እና በንግድ ሚኒስቴር ትብብር የሚካሄድ ጥናት ነውም ተብሏል፡፡የጥናቱን ውጤት መሰረት በማድረግ እርምጃ እንደሚወሰድ በባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አልቃድር ኢብራሂም ነግረውናል፡፡

ሸቀጦችን በመደበቅ እና እጥረት እንዲፈጠር በማድረግ የዋጋ ጭማሪ እንዲከሰት ምክንያት የሚሆኑ ነጋዴዎች አሉ ያሉት አቶ አልቃድር እነዚህም ተለይተው ተገቢው እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ነግረውናል፡፡ፍትሃዊ ያልሆነ የመሸጫ ዋጋ ወስነው የሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎች እንዳሉም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ነጋዴዎቹ ፍትሃዊ ያልሆነ የመሸጫ ዋጋ ወስነው እየሰሩ ያሉት ያለምንም ኢኮኖሚያ ምክንያት ነውም ብለዋል፡፡ጥናቱን እያካሄደ ያለው ግብረ ሃይል ስራውን ከጀመረ ሶስት ሣምንት አንዳለፈው ሠምተናል፡፡

በቀጣዩ ሣምንት ስራውን አጠናቆ ውጤቱን እንደሚያስረክብ አቶ አልቃድር ነግረውናል፡፡በጥናቱ ህግ መተላለፋቸው የሚረጋገጥ ነጋዴዎች በባለስልጣኑ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ክስ ይመሰረትባቸዋል ብለዋል፡፡ህብረተሰቡም በግብይት ወቅት የሚያስተውላቸውን ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶች በነጻ የስልክ ቁጥር 8478 እና 8077 ጥቆማ መስጠት ይችላል ተብሏል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በወልቂጤ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በወልቂጤ ከሕዝቡ ጋር ባደረጉት ውይይት የመንግሥት ኃላፊዎች ለግጭቶቹ ሰበብ በመሆን እንዲሁም ግጭቶቹን ባለማስቆማቸው ሙሉ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል፡፡ የሲዳማ፣ የወላይታ፣ የጉራጌ እንዲሁም የቀቤና የዞን እና የወረዳ ከፍተኛ ሃላፊዎችም በአፋጣጭ ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ጠይቀዋል፡፡

“የዲሞክራሲ፣ የፍትህ እና የልማት ውጥኖቻችን ሊሳኩ የሚችሉት እንደ ኢትዮጵያዊነታችን በጋራ ከተባበርን ብቻ ነው…” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ “የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ከብሄር ልዩነቶቻችን አልፈን መሄድ አለብን፡፡ ሲዳማ፣ የወላይታው፣ የጉራጌው እና የቀቤናው ጠባቂ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ሌላውም በፋንታው እንዲሁ ሌላኛው ወንድሙን ሊጠብቅ ይገባል” ብለዋል…
...
ባለፈው ሳምንት የ2 የሰው ሕይወት የጠፋባት እና ብጥብጥ ነግሶባት የነበረችው ወልቂጤ ነዋሪዎች ችግሮቻቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው፡፡ትላንት ከሰዓት በፊት በሐዋሳ ከሰዓት በኋላ ደግሞ በወላይታ ተገኝተው ነዋሪዎችን አነጋግረዋል፡፡ 

በሐዋሳው ንግግራቸው የሰው ሕይወት የጠፋበትን ረብሻ ሕዝቡ ከፍተኛ ትኩረት በሚሰጠውን የጫንባላላ በዓል ላይ እንዲፈፀም ያደረገው ሀይል ለህግ የማቅረቡን አስፈላጊነት ተናግረዋል፡፡ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀረቡላቸው በርካታ ጥያቄ ውስጥ ክልል የመሆን ጥያቄ አንዱ ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ማንኛውንም ጥያቄ ማቅረብ ሕገ መንግስታዊ መብት መሆኑን ነገር ግን ጊዜና ውይይት እንደሚፈልግ ተናግረዋል፡፡ጥያቄውም በህገ መንግስቱ መሰረት የሚመለስና እሳቸው ወዲያው መልስ ሊሰጧቸው እንደማይችሉ በትዕግስት እንዲጠብቁም ነግረዋቸል፡፡

በወላይታ የነበረው ውይይት በዝግ እንደነበር አብረዋቸው የሄዱት የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የወልቂጤ ቆይታቸው ፈፅመው ወደ አዲስ አበባ ዛሬ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ ከኢትዮጵያ የቀረበውን የሰላም ሐሳብ የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ መቀበላቸውን አስመልክተው ለፕሬዝደንት ኢሳያስ ምስጋናቸውን አቅርበው እንኳን ደስ ያለን ብለዋቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የኤርትራን ልዑካን በፍቅርና በሞቀ አቀባበል ለመቀበል ዝግጁነታቸውን ገልፀውላቸዋል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሚነጋገር ልዑክ ወደ አዲስ አበባ እልካለሁ አሉ

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሚነጋገር ልዑክ ወደ አዲስ አበባ እልካለሁ አሉ፡፡አቶ ኢሳያስ መንግስታቸውን ወክሎ የሚነጋገር ልዑክ እንደሚልኩ የተናገሩት ዛሬ የሰማዕታት በዓል አከባበር ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በንግግራቸው በጦርነቱና ከዚያም ወዲህ ባለው ፍጥጫ ሁለቱም ሀገሮች አለመጠቀማቸውን ጠቅሰዋል፡፡በቅርቡ የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑ መናገሩ ይታወሳል፡፡

እሸቴ አሰፋ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት መሰናዶ ሰኔ 12፣2010

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አንዳንዴ አያድርስ የሚባለው ነገር ሲደርስ የሕይወት ፈተናው ከአለትም የከበደ ሊሆን ይችላል...

አንዳንዴ አያድርስ የሚባለው ነገር ሲደርስ የሕይወት ፈተናው ከአለትም የከበደ ሊሆን ይችላል፡፡ ሸክሙን ማቅለል የሚቻው በፅናት በመታገልና በመተጋገዝ ቢሆንም የመጀመሪያው ሸክም አቅላይ መሆን ግን ሊከብድ ይችላል፡፡ እነሆ የእናትነት ሕይወት አቅላይ ምሳሌ ሲል ዮሐንስ የኋላወርቅ የአንዲትን እናት ታሪክ ይነግረናል

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ትላንት በተከሰተ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት ሲጠፋ በፀጥታ ሐይሎችም ላይ ጉዳት ደርሷል ተባለ

በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ትላንት በተከሰተ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት ሲጠፋ በፀጥታ ሐይሎችም ላይ ጉዳት ደርሷል ተባለ…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያደረጉላቸውን ግብዣ ተከትሎ ነገ የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ መሪዎች ነገ በአዲስ አበባ የገፅ ለገፅ ንግግር ያደርጋሉ ተባለ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያደረጉላቸውን ግብዣ ተከትሎ ነገ የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ መሪዎች ነገ በአዲስ አበባ የገፅ ለገፅ ንግግር ያደርጋሉ ተባለ፡፡ሸገር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት እንደሰማው የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዘዳንት ሳልቫኪርና የዋነኛው አማፂ ቡድን መሪ ዶ/ር ሪያክ ማቻር ነገ በአዲስ አበባ የሚገናኙት ስለ ሰላም ለመነጋገር ነው፡፡

ሁለቱ ተቀናቃኞች በግንባር ተገናኝተው ልዩነታቸውን በማጥበብ ለሰላም እድል ሰጥተው የደቡብ ሱዳናውያን ሞትና እንግልት እንዲያበቃ እንዲወያዩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ግብዣ ያቀረቡላቸው በቅርቡ ነበር፡፡

ይሄንኑ ግብዣ ተከትሎም ነገ በአዲስ አበባ የሁለቱ ተቀናቃኞች መሪዎች ፊት ለፊት ተገናኝተው በደቡብ ሱዳን ሰላም እንዲወርድ ይወያያሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡የዋነኛው አማፂ ቡድን መሪ ዶ/ር ሪያክ ማቻር ባለፉት 2 አመታት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከቁም እስር ባልተናነሰ ሁኔታ ውስጥ መቆየታቸው ሲነገር ቆይቷል፡፡ከ4 አመት ከመንፈቅ በላይ ያስቆጠረው የደቡብ ሱዳኑ የእርስ በርስ ጦርነት በ10 ሺ ዎችን የሚቆጠሩ ሰዎችን ጨርሷል፡፡ በሚሊየን የሚቆጠሩትን ደግሞ ለስደትና መፈናቀል ዳርጓቸዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers