• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 8፣2009

ዓለም ያወደሰው የናይጄሪያ የፖለቲካ ጉዞ - ከወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ወደ ዲሞክራሲ

ናይጄሪያ እንዲህ እንዳሁኑ በአፍሪካ የሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተምሳሌት ከመሆኗ አስቀድሞ ታሪኳ በወታደራዊ የመንግስት ግልበጣ የተሞላ ሆኖ ቆይቷል፡፡

አገሪቱ ከ17 ዓመት በፊት ከወታደራዊ ግልበጣ ጣጣ እስከወጣች ድረስ አገሪቱ ቢያንስ ዘጠኝ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስቶች ተካሂደውባታል፡፡

ጄኔራል ሳኒ አባቻ ወር ተረኛው ሆነው የአርነት ሾኔካን የሽግግር አስተዳደር ገልብጠው የመንግስት ስልጣኑን የጨበጡት የዛሬ 23 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ያኔ ኧርነስት ሾኔካን የሽግግር አስተዳደሩ መሪ የሆኑት ናይጄሪያ የወታደራዊ አምባገነን መሪዎች ፍርርቅ ባንገፈገፋት ጊዜ ነው፡፡

ናይጄሪያውያን ከእንግዲህስ እንዲህ ዓይነቱ አገዛዝ ይብቃን ባሉ ጊዜ ወደ ዴሞክራሲያዊ ዘይቤ ለመሻገር ቁርጥ ኃሳብ አደረጉ፡፡ የጊዜውን ወታደራዊ መሪ ጄኔራል ኢብራሂም ባባንጊዳ ሰልጣኑን ለተመራጩ ሕጋዊ መንግስት እንዲያስረክቡ አስገደዷቸው፡፡

ባባንጊዳም እንደተጠየቁት ስልጣኑን አንካችሁ አሉ፡፡

ለሰላማዊ የስልጣን ማስተላለፉን ለማቀለጣጠፍ የሽግግሩን አስተዳደር እንዲመሩ ሕግ አዋቂ ናቸው የሚባሉት ኧርነስት ሾኔካን ተሰየሙ፡፡

ሾኔካን በሽግግሩ መሪነት የተሰየሙት ሂደቱን ለማቀለጣጠፍ በፖለቲካ ገለልተኝነታቸው ሁነኛው ሰው ሆነው በመገኘታቸው ነበር፡፡ ሽግግሩን ሌላኛው ወታደራዊ መሪ ጄኔራል ሳኒ አባቻ ቀደሙት፡፡

አባቻ የሾኔካንን አስተዳደር በመፈንገል ወር ተረኛው ገልባጭ ሆኑ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 7፣2009

ቤናዚር ቡቶ

ቤናዚር ቡቶ ሴቶች በማኅበራዊ፣ በምጣኔ ሐብትና በፖለቲካው ዝቅ ተደርገው በሚታዩበት ፓኪስታን አንፀባራቂ ኮከብ ሆነው ሲታዩ ቆይተዋል፡፡

እሳቸውም ወር ተረኝነቱ ደርሷቸው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተመረጡት የዛሬ 28 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

የቤናዚር ቡቶ አባት ዙልፊካር ዓሊ ቡቶ የፓኪስታን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትርም ሆነው ሰርተዋል፡፡

ነቀፋውና ሙገሳው እንዳለ ሆኖ አሁንም ድረስ ሥማቸው ከፓኪስታን ተፅዕኖ አሳዳሪዎች አንዱ ሆኖ ይነሳል፡፡

የቤናዚር ቡቶ አባት ዙልፊካር ዓሊ ቡቶ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመመረጣቸው 10 ዓመታት አስቀድሞ በጄኔራል ዚያ ኡል ሃቅ በተፈፀመባቸው ወታደራዊ ግለበጣ ሥልጣናቸውን አጡ፡፡

ሥልጣናቸውን ብቻ ሳይሆን ለጄኔራል ዚያ ኡል ሃቅ ቅርበት የነበራቸው ዳኞች ተሰይመውበታል በተባለ ችሎት ይሙት በቃ ተፈርዶባቸው ሕይወታቸውንም ተቀሙ፡፡

ይሄ ሁሉ ሆኖ ሴት ልጃቸው ቤናዚር ቡቶ ከፖለቲካው ሰፈር እንዲያፈገፍጉ አላደረጋቸውም፡፡

ቤናዚር ቡቶ ከለንደን ከነ ቤተሰባቸው ወደ ፓኪስታን ሲመለሱ ታላቅ ምርጫ ጠበቃቸው፡፡

የፖለቲካ ማኅበራቸውን በወጉ መርተው ለድል አበቁት፡፡

ለፓኪስታን ከዚያ ቀደም ባልተለመደ ሁኔታ የዛሬ 28 ዓመት በዛሬዋ ዕለት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጥ ታሪክ ሰሩ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ጥቅምት 30፣2009

የጀርመን ግምብ መፍረስ

የበርሊን ግምብ በፍልስፍናና በአስተዳደር ዘይቤ የአንድ አገር ሰዎችን ለሁለት በመክፈል የቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን የጥላቻ ግድግዳ ተደርጐ ይቆጠራል፡፡

ለዓመታት ጀመርኖችን ከፋፍሎ የቆየው ግንብ ክፍት ሆኖ ምሥራቅ ጀርመናውያን ወደ ምዕራቡ እንዲሻገሩ የተፈቀደላቸው የዛሬ 27 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

የጀርመን ናዚዎች ዓለምን በመዳፋችን ውስጥ እናውላለን ብለው ከ77 ዓመታት በፊት ጦርነት አቀጣጠሉ፡፡ የኋላ ኋላ በተነሱበት ፍጥነት መቀጠል ተሳናቸው፡፡

በሌሎች ላይ የለኮሱት እሳት ራሳቸውን ማቃጠሉን ያዘው፡፡

የህብረቱ ኃይሎች ከየአቅጣጫው መጡባቸው የአንግሎ አሜሪካ ኃይል ከምዕራብ፤ የሩሲያ ሠራዊት ከምስራቅ አቅጣጫ መጡባቸው፡፡

መፈናፈኛ አጡ፡፡

አገራቸው በህብረቱ ኃይሎች ተፅዕኖ ስር ወደቀች፡፡

ከጦርነቱ በኋላ ምዕራባዊ ክፍሏ በአሜሪካ እንግሊዝና ብሪታንያ አስተዳደር ስር ሆነ፡፡
በምስራቃዊው ክፍል ደግሞ የሶቪየት ህብረት ተፅዕኖ ሰፈነ፡፡

ምዕራባዊው ክፍል የጀርመን ፌዴራል ሪፐብሊክ ተሠኝቶ ራሱን ቻለ፡፡

የምስራቁም ግዛት ምስራቅ በርሊንን ርዕሠ ከተማው በማድረግ በሶቪየት ተቀጥላነት የጀርመን ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ተባለ፡፡

በዚያን ጊዜው የሶቪየቶች መሪ ኒኪታን ኩርቺየቭ ቀጭን ትዕዛዝ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት በአንድ ሌሊት ምስራቅ በርሊን ዙሪያዋን በ155 ኪሎ ሜትር መጠነ ዙሪያ የማገጃ አጥር ተገጠገጠባት፡፡

የድንበር ጠባቂ ፖሊሶችም የተኩሰህ ግደል ፈቃድ ተሰጣቸው፡፡ በዘመኑ ግንቡን ዘለው ወደ ምዕራብ በርሊን ለመሻገር የሞከሩ ብዙዎች የአልሞ ተኳሾች ጥይት ዒላማ ሆነዋል፡፡
በዚህ አይነቱ ሙከራ የተገደሉት ከ200 እንደማያንሱ ይነገራል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ጥቅምት 28፣2009

የሶቭየቶች ሰላይ ሪቻርድ ሶርጌ

ሪቻርድ ሶርጌ ከ2ኛው የዓለም ጦርነት መዳረሻ አንስቶ እስከ መፋፋሚያው ከነበሩ ስመ ገናና ቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት የስለላ አቀላጣፊዎች አንዱ ሆኖ ይነሳል፡፡

ሶርጌ በዚሁ ሚስጥራዊ ተልዕኮ ላይ እንዳለ ጃፓን ውስጥ ተይዞ ከታሰረ በኋላ በስቅላት የተቀጣው የዛሬ 72 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ሶርጌ ከጀርመናዊ አባቱና ከሩሲያዊት እናቱ የተወለደው በአዘርባጃን ባኩ ነው፡፡

ገና ሕፃን ሳለ ከቤተሰቡ ጋር ወደ ጀርመን በርሊን አመራ፡፡

በ1ኛው የዓለም ጦርነት ሂደት በውትድርና ተመልምሎ በጀርመን ጦር ውስጥ አገልግሏል፡፡
እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ዘልቋል፡፡

የወላጅ አባቱ ግራ ዘመም የፖለቲካ አቋም ተፅዕኖ በእሱም ላይ አድሮ የሕቡዕ የጀርመን ኮሚኒስቶች የፖለቲካ ማህበር አባል ሆነ፡፡

በዚህም የተነሳ በዓይነ ቁራኛ መታየቱና ክትትሉ ቢበዛበት ከስራውና ከማስተማር ተግባሩ እንደታገደ ወደ ሩሲያ ሞስኮ ተሰደደ፡፡

የዚያ ጊዜው የሶቪየቶቹ ወታደራዊ የስለላ ተቋም /ግሩ/ ባልደረባው አድርጎ መለመለው፡፡
በጋዜጠኛነት ሽፋንም በሰላይነት ወደተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ያሰማራው ያዘ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ጥቅምት 24፣2009

የዌልሄልም ሻቬን መደብደብ

በ2ኛው የዓለም ጦርነት በተፋላሚ ወገኖቹ ዘንድ ከፍተኛ ውድመትና ጥፋት ደርሷል፡፡

ጃፓኖች በአሜሪካ ሐዋይ የፐርል ሐርበርን የባሕር ኃይል መደብ በአየር ጥቃት ምንቅርቅሩን በማውጣት በሺህዎች የሚቆጠሩትን ገድለውና ከባድ ውድመትና ጥፋት በማድረስ አገሪቱን ወደ ጦርነቱ እንድትሳብ ማድረጋቸው አንዱ አጋጣሚ ሆኖ ይነሳል፡፡

የሕብረቱ ኃይሎች በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የጦር አውሮፕላኖቻቸውን በማሰማራት ዌልሄልም ሻቬን የተሰኘውን የጀርመን የወደብ ከተማ አንዳልነበረ ያደረጓት የዛሬ 73 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ወደ ሰሜናዊ ባሕር ተጠግቶ የሚገኘው ዊልሄልም ሼቨን ወደብ የከተማዋን ስያሜ የሚጋራና ከጥንት ጀምሮ በምጣኔ-ሐብታዊ ማቀለጣጠፊያ ሆኖ ዘልቋል፡፡

ራሱን የቻለ የመርከብ ግንባታና ምህንድስናም የወደቡ መታወቂያ ነው፡፡

ወደ 2ኛው የዓለም ጦርነት መቃረቢያ አድሚራል ግራፍ ስፒ የተሰኘው ግዙፍ የጀርመኖች የጦር መርከብ ተገንብቶ ለአገልግሎት የበቃው ከዚሁ ወደብ ተነስቶ ነው፡፡

ዓለምን በጦር ኃይል አንበርክኮ የማስገበር ክፉ ኃሳብ ያደረባቸው የጀርመን ናዚዎች የጃፓን ወረራዎችንና የጣሊያን ፋሽስቶችን በግብረ አበርነት ከጐናቸው አሰለፉ፤ የአክሲስ ኃይሎች ተሰኙ፡፡

እነ አሜሪካና እንግሊዝ ከቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት ጋር በፀረ አክሲስነት አንድ ላይ ሆኑ፡፡

የኅብረቱ ኃይሎች ተባሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers