• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 16፣2009

የአሜሪካ ምስረታ ጅማሮ

ከአሜሪካ ግዛቶች የነፃነት ትግል ስኬት በኋላ የመጨረሻው የብሪታንያ ቅኝ ገዢ ኃይል ወታደር ከኒውዮርክ የወጣው የዛሬ 233 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

በዘመኑ የብሪታንያ ፖርላማ በዚያ ላሰማራው ጦር ወጪ መሸፈኛው በ13ቱ የአሜሪካ የቅኝ አካባቢዎች ላይ የግብር ጫናውን አሸከማቸው፡፡

ግዛቶቹ ይሄ ከአቅማችን በላይ ነው ሲሉ አንገራገሩ፡፡

የብሪታንያ አካሎች ናችሁ እየተባልን እየተሸነገልን በፖርላማው ተገቢ ውክልና ሳይኖረን የምታሸከሙን ግብር ምን የሚሉትን ነው ብለው አምርረው ተከራከሩ፡፡ ተቃወሙ፡፡

እምቢታቸው ጉልበት እያበጀ መጣ፡፡ ለንደን ፍፁማዊ የቅኝ ገዢነት የበላይነቷን ለማፅናት ተነሳች፡፡

የማሳቹሴትሱን የራስ ገዝ አስተዳደር አፈራርሳ በጦሯ ሥር አዳሪ እንዲሆን አደረገችው፡፡

እምቢታቸውን ያበረቱት የአሜሪካ የቅኝ አካባቢዎች ብሪታንያን በብቃት ለመገዳደር እንዲያስችላቸው ኮንትኔንታል ኮንግረስ ያሉትን የጋራ ሸንጓቸውን መሠረቱ፡፡

ብቁ የሰለጠነ የጦር ኃይል አልነበራቸውም፡፡

በብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ላይ እመቢታቸው ሲያይል የሚሊሺያ ታጣቂ ጦሮቻቸውን አስታጠቁ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 15፣2009

የሉሲ (ድንቅነሽ) መገኘት

በዓለም ዙሪያ ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር ለመጐብኘት፣ መሬቷንም ለመርገጥ እንደ ዋና ምክንያትነት ትቆጠራለች - ሉሲ ወይም ድንቅነሽ፡፡

እማማ ሉሲ ከኢትዮጵያ ምድር እነሆ የሰው ዘር መገኛ የተባለችው የዛሬ 42 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

የመጀመሪያዋ የሰው ቅሪት አካል የሆነችው ሉሲ /ድንቅነሽ/ የተገኘችውም በአፋር ክልል ሀዳር በተባለ ቦታ ነው፡፡

የድንቅነሽ ፈላጊዎች አሰሳቸውን ያካሄዱት በስመ ጥሩ የሮክ ሙዚቃ ባንድ ዘ ቢትልስ ጆን ሌንን እና ፖል ማካርቲ የፃፉትና ያዜሙትን ዘፈን እያደመጡ ነበር፡፡

ዘፈኑም “ሉሲ ኢን ዘ ስካይ ዊዝ ዳይመንድስ” ይባላል፡፡

በዚያ የምርምር ካምፕ ሰርተው ነበርና ዘፈኑ እጅጉን ጮክ እያለ እየተመላለሰና እየተደገመ እንዲጫወት አደረጉት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 14፣2009

የ60 የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት ባለስልጣኖችና ወታደራዊ መኰንኖች ያለፍርድ በግፍ መገደል

በኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ አሰቃቂ የግፍና የግድያ ትውስታዎች ተመዝግበዋል፡፡

ነገር ግን ከዛሬ 42 ዓመታት በፊት ወታደራዊው መንግስት ደርግ በንፁሃን ዜጎች ላይ የፈፀመው ግድያ በአስቃቂነቱ በነውረኛነቱ ቀዳሚ ሆኖ ይጠቀሳል፡፡

በ1967 ህዳር 14 ቀን ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ አምባገነኑ ወታደራዊ መንግስት 60 የሚሆኑ የቀድሞው መንግስት ባለስልጣኖችንና ወታደራዊ መኰንኖች ያለፍርድ በግፍ ገደላቸው፡፡

በጥቂት መኮንኖችና በአብዛኛው የበታች ሹማምንት ስብሰብ የተዋቀረው ደርግ በእጃቸው መከላከያ የሌላቸውንና በቁጥጥሩ ስር ያደረጋቸውን ባለስልጣናትና ወታደሮች ገድሎ በቀድሞው የአዲስ አበባ ወህኒ ቤት ግቢ ውስጥ በጅምላ ቀበራቸው፡፡

ደርግ የ66ቱን አመፅ በጠለፋና በአዝጋሚ ለውጥ ነጥቆ መስከረም 2 ስልጣኑን ከያዘ በኋላ አብዛኛው ታሪኩ የጭፍጨፋ ነው፡፡

የቀድሞ ባለስልጣኖች በአመፅ ግፊት ምክንያት በወታደሮች ቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

አብዛኛዎቹ ሹማምንት ሃገራቸውን በጠላት ወረራ ጊዜ በአርበኝነት ደማቸውን ያፈሰሱ በዲፕሎማሲ ትግል ለሃገራቸው ክብርና ጥቅም የሰጡ፣ በሃገር ውስጥና ዓለም ዓቀፍ ወታደራዊ ተልዕኮ በክብር የተመሰገኑ ነበሩ፡፡

በአብዛኛው የመንግስት ፖለቲካ አስተዳደር ጨርሶ ግንዛቤ ያልነበራቸው የደርግ አባላት “ሕዝብ በድለዋል” በሚል የግል ስሜታቸው እየተነዱ አሰሩዋቸው፡፡

በባለስልጣናቱ ላይ አንዳችም ክስ አልተመሰረተባቸውም፡፡ እነሱው ከሳሽ እነሱው ፈራጅ በሆነው ስልጣናቸው የግድያ ውሳኔ ያሳለፉባቸው በዋዜማው በአንድ ቀን ስምምነት ነበር፡፡

ሁለት ጠቅላይ ሚኒስትሮችን ጨምሮ ሃገረ ገዥዎች የጦር ጄኔራሎች፣ ሚኒስትሮች የመገደላቸው ምክንያት የወቅቱ የደርግ ሊቀመንበር የሌተና ጄነራል አማን ሚካኤል አንዶም ማመፅና ተታኩሰው መገደላቸው ነው የሚሉ ፅሁፎች ታትመዋል፡፡

አቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤት ባቀረበው ማስረጃ ግን ግድያው እንዲፈፀም የቀደመ ዝግጅት መኖሩን አረጋግጧል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 11፣2009

ዘመቻ ሙሴ

እስራኤል ዘሮቼ ናቸው ደማቸው ከደሜ ይቀዳል ያለቻቸውን የኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላውያንን ኑ ወደቤታችሁ ስትል ስትሰበስባቸው ቆይታለች፡፡

በዘመቻ ሙሴ ሚስጥራዊ ጉዞ የመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላውያን ከሱዳን በአውሮፕላን ወደ እስራኤል የተጓጓዙት የዛሬ 31 ዓመት በዛሬዋ ቀን ነበር፡፡

ወቅቱ ለኢትዮጵያም ሆነ ለኢትዮጵያውያን እጅጉን አስቸጋሪ ጊዜ ነበር፡፡

ሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ከጫፍ ጫፍ በእርስ በርስ ጦርነት እየጋየ፤ መሞት መግደሉና እልቂቱ የእለት ተዕለት አስቃቂ ትዕይንት ነበር፡፡

በዚህ የአገር ክፍል ችግሩ በረታ፡፡ ረሃቡ ጠና፡፡

እስራኤል በዚህ ጊዜ የኔ ናቸው ያለቻቸውን ቤተ እስራኤላውያን ከጐንደር ገጠሮች አስወጥታ ልትወስዳቸው ሚስጥራዊውን የሙሴን ዘመቻ ጀመረች፡፡ 

ቤተ እስራኤላውያኑን ወደ እስራኤል በማጓጓዙ ተግባር የእስራኤል ጦር፤ የአሜሪካው ማዕከላዊ የስለላ ድርጅት /ሲ.አይ.ኤ/፤ በካርቱም የአሜሪካ ኤምባሲና የሱዳን የደህንነት ተቋም በትብብር መሠለፋቸው ይነገራል፡፡

ቅጥረኞችም ሳይቀሩ የዚህ ዘመቻ ተባባሪ ነበሩ፡፡

ቤተ እስራኤላውያኑ በሱዳን ወደ ተዘጋጁላቸው ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ለመድረስ ከጐንደር ገጠሮች ተነስተው ድንበር አቋርጠው የሱዳንን በረሃማ መሬት በእግር መኳተን ነበረባቸው፡፡ ጉዞው እጅግ አድካሚ፣ አታካችና አለፍ ሲልም መስዕዋትነት ጠያቂ ነበር፡፡

የበረቱት ኳትነው ከጊዚያዊ መጠለያቸው ደረሱ፡፡ አቅም ያጡትና ያላደላቸው ካሰቡት ሳይደርሱ በየዱሩና በየበረሃው የቀሩም ብዙዎች ናቸው ይባላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 9፣2009

የኢራቅ ነገር

በሳዳም ሁሴን ትመራ የነበረችዋ ኢራቅ ከአሜሪካ ጋር ጠላትነቷ ሲበረታ ከዋሽንግተን በኩል የሕዝብ ጨራሽ መሣሪያዎችን ታጥቃለችና ትፈተሽልኝ የሚለው ግፊቱ በርትቶባት ነበር፡፡

በዶክተር ሐንስ ብሌክስ የተመራው የተባበሩት መንግሥታት የኒኩሊየር ጦር መሣሪያዎች ተቆሪጣጣሪ አካል ለመጀመሪያ ጊዜ ኢራቅ የገባው የዛሬ 13 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ከዚህ ጊዜ 10 ዓመታት በፊት ኢራቅ ትንሿ ጐረቤቷን ኩዌትን ወረረች፡፡

የወቅቱ የኢራቅ መሪ ሳዳም ሁሴን ኩዌትን ለቀው እንዲወጡ ዓለም ተማፀናቸው፡፡

እነ አሜሪካ አስፈራሯቸው፡፡ ወዳጆቻቸው አባበሏቸው፡፡

የፀጥታው ምክር ቤት ቢገስፃቸውና ማስጠንቀቂያም ቢሰጣቸው በጄ አላሉም፡፡

አሜሪካ ወዳጅ ደጋፊዎቿን አሰልፋ በበረሃው ማዕበል ዘመቻ የኢራቅን ጦር ከኩዌት ነዳችው፡፡

የበረሃው ማዕበል ዘመቻ ኩዌትን ነፃ በማውጣት ቢደመደምም አሜሪካ በሣዳም አስተዳደር ላይ ቂም እንደቋጠረችባት ዘለቀች፡፡                                                      

ኘሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ ትልቁ ያዳከሙትን የኢራቅ ጦር ለማሽመድመድ ጆርጅ ቡሽ ትንሹ ቁርጥ ውሳኔ ላይ ደረሱ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers