• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 26፣2009

5 ሺ ሰዎችን የቀጠፈው “ታላቁ ጭጋግ”

ያኔም የነበረ ቢሆንም ፤ የአየር ብክለት ነገር የአገሮችም የዓለማችንም የዕለት ተለት ስጋትና አጀንዳ ሳይሆን የእንግሊዟ ርዕሰ ከተማ ለንደን ችግሩን ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት አንስቶ አሳምራ ታውቃለች፡፡

በአየር ብክለት ምክንያት በ5 ቀናት ውስጥ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ያለቁበት ታላቁ ጭጋግ የጀመራት የዛሬ 64 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነው፡፡

በጊዜው ለንደን ለኢንዱስትሪዎቿ መዘወሪያ በአብዛኛው ድንጋይ ከሰልን ማንደድ አብዩ የኃይል ምንጯ ነበር፡፡

የባቡሮቿም ቀለብ፣ ከክረምቱ ከፍተኛ ቅዝቃዜ ለማምለጥ በዚሁ የኃይል ምንጭ ላይ ተማምና ኖራለች፡፡

ታላቁ ጭጋግ ከመከሰቱ በፊት በለንደን ቅዝቃዜው በረታ፡፡

ለንደንም ቅዝቃዜውን ለመከላከል የምታነድ የምታጫጭሰውን የድንጋይ ከሰል አበዛች፡፡

በተለይም ከ2ኛው የዓለም ጦርነት በመለስ በነበሩት የችግር ዓመታት ለኢንዱስትሪዎች ማንቀሳቀሻም ሆነ ለቅዝቃዜ መከላከያ የሚማገድ የድንጋይ ከሰል ጥራቱ ዝቅተኛ ነበር፡፡

ጭሱ እንደጉድ ይትጐለጎላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 22፣2009

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ኃያላኑ አንዳቸው አጥቂ ሌሎቹ ተከላካይ ሆነው እየተቧደኑ ጐራ ፈጠሩ፡፡

የዘመኑ የጃፓን ንጉሰ ነገሥት ሂሩሂቶ አሜሪካንን ለመውጋት የመጨረሻውን ማረጋገጫ የሰጡት የዛሬ 75 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

በአዶልፍ ሂትለር ይመሩ የነበሩት የጀርመን ናዚዎች ዓለምን አንበርክከውና በተፅዕኗቸው ሥር እንደፈቃዳቸው አዳሪ ለማድረግ ባሰቡ ጊዜ ተባባሪዎች አላጡም፡፡

ከአውሮፓ የጣሊያን ፋሽስቶች አጋሮቻቸው ሆኑ፡፡

ከወደ ሩቅ ምሥራቅም የጃፓን ወራሪዎች በዓላማቸው ተባባሪነት ተሰለፉ፡፡ ይሄ ሦስትዮሽ የጥፋት ጥምረት አክሲስ ተሰኘ፡፡

ከ75 ዓመታት በፊት የጃፓን ከፍተኛ መኮንኖች በጦርነቱ ይዞታ ላይ ሲመክሩ፣ ሲያወጡና ሲያወርዱ ሰነበቱ፡፡ የጦር መኮንኖቹ በሸንጓቸው አሜሪካን ለመውጋት ቁርጥ ኃሳብ አደረጉ፡፡

ንጉሰ ነገሥት ሂሩሂቶም ይሁን እንዳላችሁት ሲሉ ለአሜሪካ መወጋት ፈቃደኝነታቸውን አረጋገጡ፡፡ ቡራኬያቸውን ሰጡ፡፡ ጃፓን አሜሪካን ለመውጋት ያቀደችው የደቡብ ምሥራቅ እስያን ክፍል ለመያዝ የነበራትን ዕቅድ እንዳታሰናክልባት አስባ ነው፡፡

ንጉሰ ነገሥቱ ለዕቅዱ ቡራኬያቸውን በሰጡ በሳምንቱ ጃፓን በሐዋይ የሚገኘውን የአሜሪካ የፐርል ሐርበር የባሕር ኃይል መደብ እንዳልነበረ አድርጋ ምንቅርቅሩን አወጣችው፡፡ ከ2 ሺህ 400 በላይ የአሜሪካ ባሕር ሐይል ወታደሮችና መኮንኖች ተሰዉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 21፣2009

ሰር ዊኒስተን ቸርችል

በመዲናችን አዲስ አበባ በማዘጋጃ ቤቱና በባቡር ጣቢያው ትይዩ የተዘረጋው ባለ ሁለት ተካፋይ ሰፊ መንገድ የቸርቺል ጐዳና ተብሎ ተሰይሟል፡፡

በአፄ ኃይለስላሴ የአስተዳደር ዘመን ጐዳናው በስማቸው የተሠየመላቸው በሙሉ መጠሪያቸው ሰር ዊኒስተን ሊዮናርድ ስፔንስር ቸርቺል በአገራቸው የጦርና የፖለቲካ መሪነታቸው ታላቅ አሻራ ያኑሩና በዓለም አቀፍ ደረጃም ስብዕናቸው የገዘፈ እንግሊዛዊ ናቸው፡፡

ዊንስተን ቸርቺል በእንግሊዝ ኦክስፎርድ-ሻየር ከመስፍናዊ ቤተሰብ የተወለዱት የዛሬ 142 ዓመት በዛሬዋ እለት ነው፡፡

ቸርቺል ከዘመነ ወጣትነታቸው አንስቶ ከዚህ ዓለም በሞት እስከተለዩ ድረስ እንኳን ተወለዱ የሚያሰኙ ታላላቅ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡

ዊንስተን ቸርቺል በ1ኛው የዓለም ጦርነት የጀርመንና የተባባሪዎቿን እኩይ ዓላማ ለማጨናገፍ በጦር መሪነት አዋግተዋል፡፡

የ2ኛው የዓለም ጦርነት ባንዣበበት ሰዓት የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡

ጦርነት አልለቀቃቸውም፡፡

በዚህም ጊዜ የናዚ ጀርመንንና የጦር ተባባሪዎቿን የጥፋት ዓላማ ለመቀልበስ ታላቅ ኃላፊነት ትከሻቸው ላይ ወደቀ፡፡

አሜሪካን፣ ሶቪየት ህብረትንና ፈረንሳይን ከጐናቸው በማሰለፍ ለህብረቱ ኃይሎች በአንድነት መቆም ታላቅ ድርሻ ተወጡ፡፡

መከራውን ገፉት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 20፣2009

የኮርያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 858

የዛሬ 29 ዓመት በዛሬዋ እለት ከኢራቅ ባግዳድ ተነስቶ ወደ ሴኡል በማምራት ላይ የነበረው የኮሪያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 858 ወደ መዳረሻው ተቃርቧል፡፡

አብራሪው ሁለተኛው ማረፊያው ወደነበረችው ባንኮክ እንደተቃረበ በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በሰላም እንደሚያርፍ የሬዲዮ መልዕክት ተለዋውጧል፡፡ ሁሉም ነገር አማን ነበር፡፡  አማን ሆኖ ግን አልዘለቀም፡፡

በዚያው ቅፅበት በአንዳማን ባሕር አናት ሲበር አየር ላይ ፈነዳ፡፡ ብትንትኑ ወጣ፡፡

በአውሮፕላኑ ተሳፍረው የነበሩ 113 ኮሪያውያንና ሁለት የሌሎች አገር ዜጐች በሙሉ አለቁ፡፡

አውሮፕላኑ በአየር ላይ ብትንትኑ የወጣው አስቀድሞ በተጠመደበት ፈንጂ ነበር፡፡

ግን ይሄን ያረገው ማን ይሆን ? ሲባል ነገሩ ወደ ሁለት ወንድና ሴት የሰሜን ኮሪያ የደህንነት ምልምሎች አመራ፡፡

ሁለቱ ኮሪያዎች ከታላቁ የኮሪያ ጦርነት አንስቶ የጐሪጥ ሲተያዩ፣ ሲጐነታተሉ ሲፎካከሩ ሲዛዛቱ ቆይተዋል፡፡

የአውሮፕላኑ ፍንዳታ ጉዳይም የሁለቱ አገሮች የባላንጣነትና የጠላትነት ቅጥያ ነበር፡፡

በጃፓን ፖስፖርት ሲዘዋወሩ የነበሩት ሰሜን ኮሪያውያን የደህንነት ምልምሎች አውሮፕላኑ በባግዳድ ሳዳም ሁሴን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንዳለ በትራንዚስተር ሬዲዮ ተመስሎ የተዘጋጀውን ፈንጂ በመንገደኛች እቃ ማስቀመጫ አኖሩ፡፡ ለፈንጂው ኃይል መጨመሪያ በመጠጥ አስመስለው ያዘጋጁትን ንጥረ ነገር አብረው እዛው ተው፡፡

አቡዳቢ ላይ ወረዱ፡፡ ከአቡዳቢ በአማን በኩል ወደ ሮም ለማምለጥ አሰቡ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 19፣2009

የሴቶች የመምረጥና መመረጥ መብት ጉዳይ

የዛሬ 123 ዓመቷ የዛሬዋ ዕለት በዓለምም ሆነ በኒውዚላንድ ታሪክ የተለየ ቦታ አላት፡፡

የአገሪቱ ሴቶች ከወንዶች ዕኩል የሕዝብ እንደራሴዎችንና የአካባቢ ምክር ቤቶችን ተወካዮች የመምረጥ መብታቸው ስራ ላይ የዋለው የዛሬ 123 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ይህም የኒውዚላንድን ሴቶች በዘመናዊት ዓለማችን የመምረጥ መብትን በመጎናፀፍ የመጀመሪያዎቹ አድርጓቸዋል፡፡

አሁንም ድረስ በአንዳንድ የዓለማችን ክፍሎች ሴቶች እንደ መምረጥና መመረጥ ያሉ ፖለቲካዊ መብቶችን ተነፍገው የሚገኙትን ያህል ከ123 ዓመታት በፊት የኒውዚላንድ ሴቶችም የዚሁ ዕጣ ተጋሪ ነበሩ፡፡

ነገሩ ግን የብሪታንያ የቅኝ አገር በነበረችዋ ኒውዚላንድ የሴቶች የመምረጥ መብት የተረጋገጠው የዛሬ 123 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ቢሆንም ሴቶችን ለዚህ መብት ለማብቃት ጥረቱ የተጀመረው ከዚያ ጊዜ 20 ዓመታት ቀደም ብሎ ነው፡፡

እስከዚያን ጊዜ ድረስ ሴቶች ከማጀት አልፎ በአደባባይ ፖለቲካዊ ተግባራት መካፈል ዕድሉ አልነበራቸውም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers