• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ታህሳስ 19፣2009

የሜሲናው የመሬት ነውጥ

ዓለማችን ለቁጥር የሚያታክቱ የመሬት ነውጦችን አሳልፋለች፡፡

የደቡባዊ ጣሊያኖቹን የሜሲናና ሬጂዮ ካላብሪያ ከተሞችን ሙሉ ለሙሉ እንዳልነበሩ አድርጎ ያጠፋቸው አስከፊ ርዕደ መሬት የደረሰባቸው የዛሬ 108 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

አስከፊው የሜሲና ርዕደ መሬት ዋነኛ የንቅናቄ ማዕከሉን የሲሲሊዋን ሜሲና ከተማን አደረገ፡፡

በርዕደ መሬት መለኪያ /ሬክተር ስኬል/ 7 ነጥብ 1 ተመዘገበ፡፡

አካባቢውን ከ30 እስከ 40 ሰኮንድ ክፉኛ አርገፈገፈው፡፡ ግልብጥብጡን አወጣው፡፡ እንደ ኳስ አነጠረው፡፡

የንቅናቄ ማዕከሉ የሲሲሊ ደሴቷ ሜሲና ብትሆንም በዋናዋ ጣሊያን ደቡባዊ ጫፍ የምትገኘውንም ሬጂዮንም መታት፡፡

በዚያ ላይ እዚህም እዚያም እሳት ተቀስቅሶ ቃጠሎ ሆነ፡፡

ጥፋቱና ውድመቱ በሜሲና  እና ሬጂዮ ካላብሪያ ከተሞች ላይ ቢከፋም በ300 ኪሎ ሜር መጠን ዙሪያ የተለያየ ደረጃ ጉዳት አስከትሏል፡፡

ርዕደ መሬቱ ከ108 ዓመታት በፊት የነበረችዋን የሜሲና ከተማን እንዳልነበረች አደረጋት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ታህሳስ 17፣2009

ታላቁ ነውጥ

ታላቁ የሕንድ ውቅያኖስ ነውጥ የደረሰው የዛሬ 12 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

የታላቁ ነውጥ መነሻ ከኢንዶኔዥያዋ ሱማትራ በስተሰሜን በ160 ኪሎ ሜትር ርቀት ከሴሜውሉ ደሴት በ30 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ከሚገኝ የውቅያኖስ ክፍል ነው፡:

መነሻው ከሲሜውሉ ደሴት ጥልቅ የውቅያኖስ አካል ቢሆንም እንቅጥቃጤው ሰፊ የዓለማችንን ክፍሎች አካልሏል፡፡

በርዕደ መሬት መለኪያ /ሬክተር ስኬል/ 7 ነጥብ የሚመዘገብ ነውጥ አደገኛ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡

በኢንዶኔዥያ ነውጥ ግን ከዚያ በላይ 9 ነጥብ 3 ሆኖ መመዝገቡ ከአደገኛ ይበልጥ አደገኛ እንደነበር ያስረዳል፡፡

ነውጥ በሬክተር ስኬል መለካት ከጀመረበት አንስቶ እስከዚያን ጊዜ በነበሩ 100 ዓመታት ውስጥ ከደረሱት በ3ኛው ከባድ ነውጥነት ተመዝግቧል፡፡

ነውጡ ሌላም ባህሪ ነበረው፡፡ እግጅ አደገኛ የተባሉት አብዛኞቹ ነውጦች ከፍተኛ ጥፋት የሚያደርሱት በጥቂት ሰኮንዶች ቅፅበት ሲሆን የዛሬ 12 ዓመት የደረሰው እስከ 10 ደቂቃ የዘለቀ ነበር፡፡

በዚያው ቅፅበት ኢንዶኔዥያን ብቻ ሳይሆን ባንግላዴሽን፣ ሕንድን ሲሪላንካን፣ ማያንማርን፣ ታይላንድን ሲንጋፖርንና የማልጂቭስ ደሴቶችንም ክፉኛ አርገፍግፏቸዋል፡፡

ነውጡ ከእስያ አገሮች አልፎ እስከ አሜሪካዋ አላስካ ድረስ ተሰምቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ታህሳስ 14፣2009

የአፍጋኒስታን ነገር

አፍጋኒስታን እንዲህ እንዳሁኑ ከ30 ዓመታት በፊትም ሰላም አልነበራትም፡፡

የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት ጦር ተባባሪዎቼ ናቸው ያላቸውን የአገሪቱን የፖለቲካ ወገኖች ለመደገፍ ወደ መዲናዋ ካቡል የዘለቀው የዛሬ 37 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ከወረራው ቀድሞ በነበሩ ዓመታት በአፍጋኒስታን በተለያየ ደረጃ ለሶቪየቶች ቅርበት የነበራቸው የአገሬው ፖለቲከኞች ሥልጣን ላይ የነበሩ ቢሆንም እርስ በርሣቸው ሽኩቻ ያዙ፡፡

በዚያ ላይ እዚህም እዚያም በአስተዳደሩ ላይ ብረት ያነሱ አማፂያን እንደ አሸን ፈሉ፡፡

የዘመኑ የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት ሐፊዙላህ አሚን የሶቪየቶቹ ግልፅ ጠላት ባይሆኑም በሥልጣን ላይ ከነበረው የፖለቲካ ማኅበር የሶቪየቶች ታማኞችን ማባረር መግደላቸው በሞስኮ ቂም አስቋጠረባቸው፡፡

ለሞስኮ ያላቸውም ታማኝነት ጥርጣሬ ውስጥ ገባ፡፡

ከዘመኑ የአሜሪካ ጉዳይ ፈፃሚ ጋር በሚስጥር መምከራቸውን ሶቪየቶቹ ደረሱበት፡፡

አሚን የአሜሪካ ማዕከላዊ የስለላ ድርጅት /CIA/ ምልምል ናቸው ከሚል ድምዳሜ አደረሳቸው፡፡

አቄሙባቸው፡፡

በቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት ገናና የስለላ ድርጅት /KGB/ የሚደገፉ የሶቪየት አልፋ ኮማንዶ ክፍል ልዩ ኃይል ወታደሮች የአፍጋኒስታንን መደበኛ ሰራዊት የደምብ ልብስ በመልበስ ርዕሰ ከተማዋ ካቡልን ከተቀረው የአገሪቱ ክፍል ቆርጠው ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠሯት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ታህሳስ 10፣2009

የሆልት ነገር

ሃሮልድ ኤድዋርድ ሆልት 17ኛው የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡

ሆልት በቼቪዮት የባሕር ዳርቻ በመዋኘት ላይ በነበሩበት ወቅት ሰምጠው እስከወዲያኛው ተሰወሩ፡፡ ከ3 ተከታታይ ቀናት ፍለጋ በኋላ በቃ ሆልት መሞታቸውን መቀበል አለብን የተባለው የዛሬ 49 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ሃሮልድ ኤድዋርድ ሆልት በወጣትነታቸው ወቅት ከ80 ዓመታት በፊት በሕግ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመረቁ፡፡

ዘመኑ የታላቁ ዓለም አቀፍ የምጣኔ-ሐብት ምሥቅልቅል /ዘ-ግሬት ዴፕሬሽን/ ወቅት ስለነበር በተመረቁበት መሥክ ሥራ ማግኘት አልቻሉም፡፡

በዚህ ሁኔታ አስገዳጅነት በአንድ ቡና ቤት በሻይና በቡና አፍይነት ለመቀጠር ተገደዋል፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ ብዙም ሳይዘገዩ ዩናይትድ አውስትራሊያ የተሰኘውን የፖለቲካ ማኅበር ተቀላቀሉ፡፡

የፖለቲካ ማኅበራቸው ኋላ የሌብራል የፖለቲካ ፓርቲ ተሰኝቷል፡፡ ሆልት የፖለቲካ ማኅበሩን በተቀላቀሉ በጥቂት ዓመታት ውስጥ በሹመት ላይ ሹመት ይነባበርላቸው ያዘ፡፡

በርካታ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን በበላይነት መርተዋል፡፡

በመጨረሻም የአውሥትራሊያ የሥልጣን ጣራ ወደሆነው ጠቅላይ ሚኒስትርነትም ደርሰዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

ታሪክን የኋሊት፣ታህሳስ 5፣2009

የባንግላዲሽ ነገር

የዛሬ 45 ዓመት የዛሬዋ ዕለት ባንግላዴሽ የተሰኘችዋን አገር ነፃነት በማረጋገጥ ረገድ ልዩ ቀን ተደርጋ ትቆጠራለች፡፡

ባንግላዴሽ በጊዜው ከጥቂት ወራት በፊት ያወጀችውን ነፃነት ለማስቀልበስ ወደ አገሪቱ የዘመቱት 90 ሺህ የፓኪስታን ጦር ወታደሮች አጃቸውን የሰጡት የዛሬ 42 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

በብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ሥር ያሣለፈችው ሕንድ ከ69 ዓመት በፊት ለነፃነት ስትበቃ ሕንድና ፓኪስታን በተባሉ ሁለት ነፃ አገሮች ተከፋፈለች፡፡

የአሁኒቱ ፓኪስታን በስተምዕራብ ሆና ዘመናዊቷ ባንግላዴሽ ደግሞ ምሥራቃዊ ማዶ ሆና በአንድ ፓኪስታን ሥር ቢጠቃለሉም በሁለንተናዊ ጉዳዮች ሥምምነት ራቃቸው፡፡

ምሥራቆቹ በምጣኔ-ሐብቱም በአስተዳዳራዊ ዕልቅናውም፣ በሹመት ድልድሉም በፖለቲካዊ ተሰሚነቱም ተበድለናል ተጨቁነናል ሲሉ ምሬት እሮሯቸውን ማሰማት ጀመሩ፡፡

ከ42 ዓመት በፊት ራሳችንን ከፓኪስታን ነጥለናል እሉ፡፡ ነፃ አገር መሆናቸውን አወጁ፤ አዲሲቱ አገራቸውንም ባንግላዴሽ ሲሉ ሰየሟት፡፡

ፓኪስታን ይሄ የማይሞከር ነው አለች፡፡

እጅግ ግዙፍ የሆነ ጦርና በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ወደ ባንግላዴሽ አዘመተች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers