• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት: መስከረም 13,2006

መስከረም 13,2006

የጀርመን ናዚዎች ዓለምን የመቆጣጠር ክፉ ኃሳብ ባደረባቸው ጊዜ የወረራቸው ማሟሻ ያደረጉት የዛን ጊዜዋን ቼኮዝሎቫኪያ ሱዴትን ግዛት በወረራ በመያዝ ነው፡፡ የቼኮዝሎቫኪያ ጦርም ለመከላከሉ ተግባር ተነስ ‹‹!ታጠቅ!›› የተባለው የዛሬ 75 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡ ሱዴትን በዛን ጊዜው ስታክስቲካዊ መረጃ 3 ሚሊዮን ገደማ ጀርመንኛ ተናጋሪዎች መኖሪያ ብትሆንም ከ1 ኛው የዓለም ጦርነት በኋላ እንደ አዲስ የተመሰረተችው ቼኮዝሎቫኪያ አካል ነበረች፡፡ ናዚና ተከታዮቹ ሱዴትን ላንድ ወደ ጀርመን መቀላቀል አለበት ብለው ቆርጠው ተነሱ፡፡ፕሮፖጋንዳውን አፋፋሙት ጥያቄው በመጀመሪያ የሱዴትን ላንድ ጀርመንኛ ተናጋሪዎች ከቼኮቹ ጋር እኩልነታቸው ይረጋገጥ በሚል ተነሳ፡፡ ነገር ፍለጋው ሲጠናከር ለጀርመኖች የተሟላ የራስ ገዝ መብት የሚለውን አስከተለ፡፡የዚያ ጊዜው የቼኮዝሎቫኪያ መንግስት በሱዴትንላንድ ጀርመንኛ ተናጋሪዎች ላይ ጭቆና እየፈፀመ ነው የሚለው የናዚዎቹ ውንጀላ የፕሮፖጋንዳው ማጠንጠኛ ሆነ፡፡የጀርመን ናዚዎች የሱዴትን ላንድ ግዛት በእጃቸው ለማስገባት ቋመጡ፡፡ዲኘሎማሲውን አጧጧፉት፡፡በዚህም ሆነ በዚያ ወረራው የማይቀርላት መሆኑን የተረዳችው ቼኮዝሎቫኪያ ራሷን ለመከላከል ‹‹ተነስ! ታጠቅ!›› አለች፡፡

ይሄ ከሆነ ዛሬ 75ኛ ዓመቱን ደፈነ፡፡
ከቼኮዝሎቫኪያ መንግሥት የተጠንቀቅ ጥሪ በኋላ በወቅቱ ኦስትሪያን ወደ ግዛቱ በመቀላቀል የልብ ልብ እየተሰማው የነበረው የናዚዎቹ መሪ አዶልፍ ሂትለር የእንግሊዝ ፣ የፈረንሳይና ሌሎችም የአውሮፖ ኃያላንን በሱዴትን ጉዳይ በሙኒክ ስብሰባ ጠራቸው፡፡
ምዕራባዊያኑ የናዚዎችን ነገር ፍለጋ የራቁና የሸሹ መስሏቸው በተከላካይዋ አገር ቼኮዝሎቫኪያ ላይ ፈረዱባት፡፡
የሂትለርን ወረራ ይሁን ይሁን አሉለት፡፡
በዘመኑ ቼኮዝሎቫኪያና ፈረንሳይ በአንዷ አገር ላይ የሚፈፀም ወረራ በሌላኛዋ ላይ የደረሰ ያህል የሚቆጠርበት የጋራ የመከላከያ ስምምነት ነበራቸው፡፡

ታሪክን የኋሊት: መስከረም 10,2006

መስከረም 10,2006
ፖርቱጋላዊው አሳሽ፣ ፈርዲናንድ ማጂላን፣ ምዕራባዊውን የባሕር መስመር ተከትሎ፣ ከአትላንቲክ ወደ ሰላማዊ ውቅያኖስ በማቋረጥ ፋና ወጊ ነው፡፡ ማጄላን፣ 270 ባሕረኞችን ያካተተና አምስት መርከቦችን ያቀፈውን አካል እየመራ፣ ለታላቁ ተልዕኮ፣ ከስፔን ባሕር ዳርቻ የተነሳው፣ የዛሬ 494 ዓመት በዛሬው እለት ነው፡፡አሳሹ፣ ውጥኑን ለዘመኑ የስፔን ንጉስ ቻርልስ አምስተኛ፣ አሳውቃቸው፡፡ ንጉሱም እንዳልከው ይሁን፤ አሉት፡፡ አምስት መርከቦችንና አስፈላጊ ቁሳቁሶችና ስንቅም ፈቀዱ፡፡ ከፖርቹጋል፣ከስፔን፣ከጣሊያን፣ከጀርመን፣ ከግሪክ ከእንግሊዝና ከፈረንሳይ የተውጣጡ 270 ባሕረኞች፣ ለታላቁ የባሕር መስመር አሰሳ  ተነሱ፡፡ በመጀመሪያ ጉዟቸው፣ ካናሪ ደሴት ደርሰው፣ ወደ ምዕራብ አፍሪካ የባሕር ዳርቻ፣ ተሻገሩ፡፡ ኬፕቬርዴን አገኙ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 06,2006:ታሪክን የኋሊት

መስከረም 06,2006

የዛሬ 37 ዓመት የዛሬዋ እለት ለአርመንያዋ ርዕሠ ከተማ ይሪቫን አሳዛኝ ነበረች፡፡ በከተማዋ አንዳች እክል የገጠመው የሕዝብ ማመላለሻ የኤሌክትሪክ አውቶብስ /ትሮሌባስ/ መንገድ ስቶ ከነተሳፋሪዎቹ በይሪቫን ሐይቅ ውስጥ ይገባል፡፡ በዘመኑ የተዋጣላት ዝነኛና ታዋቂ የነበረው የዋና ስፖርት ተወዳዳሪ ሻቫርሽ ቭላድሚሮቪች ካርፓቲያን ይሄን ዘግናኝ ክስተት ተመለከተ፡፡ ካርፓቲያን በወቅቱ ለዋና ስፖርቱ እንዲያግዘው ከጓደኛው ጋር በሩጫ ልምምድ ላይ ነበር፡፡ በየእለቱም በዚህ አይነቱ ልምምድ የ20 ኪሎ ሜትር ርቀት ይሸፍኑ ነበር፡፡ የዛሬ 37 ዓመትም በዛሬዋ እለት ይህንኑ ለሟሟላት ልምምዱን ጀመረ፡፡ ልምምዱን ቢጀምርም ሐይቅ ውስጥ የመግባት አደጋ የገጠመውን የኤሌክትሪክ አውቶብስ በማየቱ አንቱ በተሰኘበት የዋና ልምዱ ተጠቅሞ ኃይቅ ውስጥ የሰመጡ ወገኖቹን ነፍስ ለመታደግ ወሰነ፡፡ ዘሎም ከሃይቁ ጥልቀት ገባ፡፡ ከሰመጠው አውቶብስ የበረከቱ ሰዎችን ማውጣት ቻለ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ፗግሜ 01,2005:ታሪክን የኋሊት

ፗግሜ 01, 2005

ታንክ አይነቱ በዝቶ፤ ቅልጥፍናው ጨምሮ፣ ዘምኖ ዘመኖ፣ አሁን ከደረሰበት ምጡቅ የቴክኖሎጂ ጫፍ ተጠግቷል፡፡ የዘመኑ ትላላቅ የምድር ውጊያዎች፣ በአመዛኙ ያለ ታንክ አይታሰቡም፡፡ታንክ፣ በውጊያ ላይ መዋል የጀመረው በ1ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ነበር፡፡ ውልደቱም በዚያው ጊዜ ነው፡፡ በብሪታንያ፡፡ሊትል ዊሊ ወይም ‹‹ትንሹ ዊሊ›› የተሠኘ ስም የተሰጠው የመጀመሪያው ታንክ ተመርቶ የወጣው የዛሬ 98 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ የታንክ አስፈላጊነት የተፀነሰው የጉድባና ሠበርባራ መሬት ውጊያዎችን ለመቋቋም ሲባል ነው፡፡

በዚህ የውጊያ መሳሪያ ግንባር ቀደም ኃሳብ አፍላቂነት የዛን ጊዜው የብሪታንያ የመከላከያ ኮሚቴ አባሎች የነበሩት ኮሎኔል ‰ርኒስት ስዊንቶንና ዊሊያም ሄንኬይ ይነሳሉ፡፡

የባሕር ኃይል ሚኒስትር የነበሩት ዊንስተን ቸርችልም በኃሳቡ ተስማሙ፡፡ - የትንሹ ዌሊ ስራ ተጀመረ፡፡
የብሪታንያ የመከላከያ ሹሞች፣ የትንሹ ዌሊ ስራ እንዲጀመር ትዕዛዝ ሲሰጡ፣ በስራው ላይ ተሳታፊ ከነበሩ ሠራተኞች አንዳቸውም ምን እየሠሩ እንደሆነ እንዳያውቁ ሚስጥሩ ተሸሸጓጋቸው፡፡
ሚስጥሩ ከሠራተኞቹ ሳይቀር እንዲሸሸግ የተደረገው ጠላቶች ስለ መሳሪያው ምንነት እንዳያውቁ፤እንዳይደርሱበትም ነበር፡፡ ለሠራተኞቹ የተነገራቸው የሚሰሩት የጦር መሳሪያ ሳይሆን፣ በጦር ሜዳ ውሃ የሚያቀብል ተሸከርካሪ ስለመሆኑ ነው ይባላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 29, 2005:ታሪክን የኋሊት

ነሐሴ 29, 2005

ማርክ ስፒትዝ የተባለው አሜሪካዊ ስፖርተኛ፣ በዘመኑ በዓለማችን የወጣለት ዋናተኛ ነበር፡፡

ስፒትዝ፣ በሙኒክ ኦሎምፒክ ሰባት የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ታሪክ የስራ ነው፡፡ ዋናተኛው ሰባተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ የወሰደው የዛሬ 41  ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

እስከ ሜክሲኮ ኦሎምፒክ መዳረሻ፣ በውሃ ዋና የተለያዩ ዘርፎች በርከት ያሉ ክብረ ወሰኞች በእጁ ላይ ነበሩ፡፡

ሜክሲኮ ሲገባ፣ ቢያንስ ቢያንስ በውሃ ዋና፣ ስድስቱን የወርቅ ሜዳሊያዎች በእጄ አስገባለሁ አለ፡፡ በከፊል ግን ማሳካት ቻለ፡፡

ሁለት የወርቅ፣አንድ የብርና አንድ የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘት ወደ አገሩ ተመለሰ፡፡
ውጤቱ ቀላል ባይሆንም ውጥኑን ባለማሳካቱ ቁጭት አደረበት፡፡

ከ41 ዓመት በፊት፣ ለቀጣዩ የሙኒክ ኦሎምፒክ አጠንክሮና በርትቶ ተዘጋጀ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers