• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት: መስከረም 22,2006

መስከረም 22,2006

ሐይቲ በምዕራቡ ንፍቀ ክበብ በብዙ መመዛኛዎች ኋላ ቀርና የድሆቹ ድሃ ተብላ የምትፈረጅ ነች፡፡ ይህቺን የካሪቢያን አገር ከድህነቷ ጋር በታላላቅ የተፈጥሮ አደጋዎች ስትመታ መኖሯ መለያዋ ነው፡፡ ፍሎራ የተሰኘው አውሎ ነፋስ በሃይቲ ላይ የጥፋት ውርጅብኙን ያወረደባት የዛሬ 50 ዓመት በዛሬዋ እለት ነው፡፡በታሪኳ ታላላቅ የመሬት ነውጦችና አውሎ ነፋሶችን አስተናጋዳለች፡፡ በበርካታ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጐቿም በተፈጥሮ አደጋዎቹ ሕይወታቸው ተቀጥፏል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት እንኳ የደረሰባት ታላቅ ርዕደ መሬት በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጐቿን ሕይወት በልቷል፡፡

በሐይቲ ላይ ከደረሱት በደርዘን ከሚቆጠሩ የተፈጥሮ አደጋዎች ፍሎራ የተባለው አውሎ ነፋስ አንዱ ነው፡፡

ፍሎራ የዛሬ 50 ዓመት ሐይቲን ከመምታቱ በፊት ጥፋቱን ያሟሸው ትሪንዳንድና ቶባጐ በተባለችው አገር ላይ ነበር፡፡
እዛ ሲደርስ የማጥፋትና የመደምሰስ አቅሙ ደረጃ ሁለት ተባለ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: መስከረም 21,2006

መስከረም 21,2006

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት፣ በሕዝብ ጨራሽነቱ፣ በአውዳሚነቱና በጥፋቱ፣ በጦርነት ታሪክ የሚስተካከለው የለም፡፡ ይሄን ጦርነት በመጫር፣ በመቆስቆስና በማቀጣጣል የጀርመን ናዚዎች፣ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ በቁንጮዎቹ የናዚ የጦርና የፖለቲካ መሐንዲሶች ላይ፣በኑምበርጉ ችሎት የፍርድ ውሳኔ የተላለፈው የዛሬ 67 ዓመት በዛሬዋ እለት ነው፡፡ ናዚዎቹ የአረያን ዘር ነን፡፡ የአረያን ዘር  ከማንም በላይ ነው፣ የሚል ኃሳብ ተጠናወታቸው፡፡ ዓለምን በወታደራዊ ኃይል ለማንበርከክ ተነሱ፡፡ የጣሊያን ፋሽስቶችንና  ጃፓንን በሸሪክነት አሠለፉ፡፡ ናዚዎችና የጥፋት ተጓዳኞቻቸው፣ ባቀጣጠሉት ጦርነትና ተያያዥነት ባላቸው ፍጅቶች፣ 60 ሚሊዮን ሰዎች አለቁ፡፡

የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት ብቻ የ27 ሚሊዮን ዜጐቿን ሕይወት ገብራለች፡፡
ከ6 ሚሊዮን የማያንሱ አይሁዳውያን፣ በናዚዎች የማጐሪያ ሠፈሮች ዘግናኝ እልቂት ተፈፅሞባቸዋል፡፡

ስላቮች፣ ሮማኒያውያን ጂፕሲዎችና ሌሎችም ዝርያዎች የተመሳሳይ ጭፍጨፋ ሰለባ ሆነዋል፡፡
 
በ1937 አጋማሽ የናዚዎችና የፋሽስት ሸሪኮቻቸው የጥፋት ጀምበር ጠለቀች፡፡

በእብሪት ዓለም ለመቆጣጠር የተነሱት ናዚዎች፣ እንዳሰቡት ሳይሆን ውጥናቸው በመራራ ሽንፈት ተደመደመ፡፡ ድል ተመቱ፡፡ አገራቸው በድል አድራጊዎቹ፣ የህብረቱ ኃይሎች፣ ቁጥጥር ስር ወደቀች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ታሪክን የኋሊት: መስከረም 14,2006

መስከረም 14,2006

ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ጊጊ ቢሳዎ ከፖርቱጋል ቅኝ አገዛዝ መላቀቋን በተናጠል ያወጀችው 40 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ ጊኒ ቢሳዎ በጥንት ዘመን ታሪኳ የጋቡና ኋላም የማሊ ግዛተ- አፄ አካል ነበረች፡፡ ይሄ ቢሆንም ከ16ኛው ክፍለ ዘመን አንስቶ የተወሰነ ክፍሏ በፖርቱጋል ሠፋሪዎች ይዞታ ስር ቆይቷል፡፡ አካባቢው በአውሮፓውያን አይንና ቀልብ ውስጥ መግባት የጀመረው አስቀድሞ ከ15ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ አንስቶ ነበር፡፡ አውሮፓውያን ከመካከለኛው ዘመን አንስቶ በጊኒቢሳዎ ላይ አይናቸውን ቢጥሉባትም ጠረፉን አልፈው ወደ መሐል አገር መዝለቅ የጀመሩት ዘግይቶ በ18ኛ ክፍለ ዘመን ነበር፡፡

ፖርቱጋሎች በግምብ የተጠናከሩ የመነገጃ ማዕከሎችን በመቆርቆር ከየትኞቹም አውሮፓውያን የተሳካላቸው ያህል እንደነበሩ በታሪክ መዛግብት ሠፍሮ ይገኛል፡፡

በፖርቱጋል ቅኝ ገዢዎች መዳፍ ስር የወደቀው የቢሳዎ ሕዝብ ቅኝ አገዛዝን አሜን ብሎ የተቀበለበት ጊዜ ባይኖርም ጥራኝ ዱሩ ብሎ የደረጃ የትጥቅ ተቃውሞውን ያነሳው ግን ከ50 ዓመታት በፊት ነበር፡፡

የጊኒና የኬፕቬርዴ ነፃነት ንቅናቄ የተሠኘው የጦርና የፖለቲካ ማህበር የነፃነት ውጊያውን መምራት ጀመረ፡፡

በሌሎች የፖርቱጋል ቅኝ ግዛቶች ባልታየ ሁኔታ የጦርና የፖለቲካ ድርጅቱ በጦር ሜዳ በለስ ቀናው፡፡ የበረከቱ አካባቢዎችን ነፃ ማውጣት ቻለ፡፡  

ኩባ፣ቻይናና የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት እስከ አፍጢሙ አስታጠቁት፡፡ አቅሙ ደረጀ፡፡ ጐለበተ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: መስከረም 16,2006

መስከረም 16,2006

የምርጫ ባሕላቸው በጐለመሰ አገሮች፣ በተፎካካሪ የፖለቲካ ማህበሮችና እነሱን በሚወክሉ  ግለሰቦች መካከል፣ የጦፈ ቅድመ ምርጫ ክርክር ማካሄድ የተለመደ ነው፡፡ የምረጡኝ ዘመቻው አካልም ሆኖ ይታያል፡፡ አሜሪካውያን፣ ከ53 ዓመታት በፊት፣ 35ኛ ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ ዝግጅት ላይ ነበሩ፡፡ ለዚያን ጊዜው ፉክክር የቀረቡት፣ የዲሞክራቲክ የፖለቲካ ማህበሩ ጆን ኤፍ ኬኔዲና ሪፖብሊካዊው ምክትል ፕሬዝዳንት ሪቻርድ ኒክሰን ነበሩ፡፡ የምርጫ ክርክር ሲነሳ፣ የኬኔዲና ኒክሰን የዚያን ጊዜው ክርክር በታሪክ ልዩ ቦታ አለው፡፡የሁለቱን እጩዎች፣ የምርጫ ክርክር ልዩ ያደረገው፣  እስከዚያን ጊዜ ድረስ ባልተለመደ ሁኔታ የመጀመሪያው የቴሌቪዥን ክርክር የተካሄደበት መሆኑ ነው፡፡ኬኔዲና ኒክሰን፣ በቺካጐ ሲ.ቢ.ኤስ ስቱዲዮ በቀጥታ ስርጭት የመጀመሪያውን የቴሌቪዥን ሙግት ያደረጉት የዛሬ 53 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

የኒክስንና ኬኔዲ የዚያን ጊዜው ሙግት፣ በቴሌቪዥን የምርጫ ክርክር ታሪክ፣ ፈር ቀዳጅ ለመሆን በቅቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: መስከረም 15,2006

መስከረም 15,2006

መኪኖች፣ በምድር ላይ እንደሚጋጩት ሁሉ፣ አውሮፕላኖችም አልፎ አልፎ፣ በአየር ላይ እየተላተሙ አሰቃቂ አደጋዎች ያገጠማቸው ጊዜዎች አሉ፡፡ ከነዚህ የበረከቱ አደጋዎች አንዱ የሆነው፣ የአሜሪካው ሳንዲያጐ፣ የአውሮፕላኖች መላተም፣ አደጋ የደረሰው፣ የዛሬ 35 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡
የአየር ላይ ግጭቱ የደረሰው፣ የፖሲፊክ ሳውዝዌስት አየር መንገድ ንብረት በነበረው  ቦይንግ 727 እና በልምምድ በረራ ላይ በነበረችው፣ አነስተኛ ሴሲና አውሮፕላኖች መካከል ነው፡፡ በልምምድ ላይ የነበረችዋ ሴሲና፣ በሳንዲያጐ ሰሜን ምሥራቅ ወደሚገኘው ሞንቶጐሞሪ አየር ማረፊያ እያመራች ነበር፡፡ በዚያው ጊዜ፣ በበረራ ቁጥር -182 በአገር ውስጥ በረራ ላይ የነበረው፣ ቦይንግ 727፣ ወደ ሳንዲያጐ ተቃረበ፡፡ ግጭት እንዳይፈጠር፣ ለመንገደኞቹ ጄት አብራሪዎች፣ ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች፣ ስለ ሴሲናዋ አውሮፕላን ተነገራቸው፡፡ ከሩቁ አይዋት፡፡ ይሁንና ወዲያውኑ ከእይታቸው ተሰወረች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers