• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት: መስከረም 30,2006

መስከረም 30,2006

ካሪቢያን ተብሎ የሚታወቀው የዓለማችን ክፍል በየጊዜው የሚነሱ አውሎ ነፋሶች ይጐበኙታል፡፡ አካባቢውን የመታውና በታሪክ ‹‹ታላቁ›› የሚል ቅፅል ያፈራው አውሎ ነፋስ በአጥፊነቱና ደምሳሽነቱ እስካሁን ተወዳዳሪ የለውም ይባላል፡፡ አውሎ ነፋሱ ታላቅ ጥፋትና ታላቅ ውድመት አስከተለ፡፡ በታሪክም ታላቁ የአውሎ ነፋስ አደጋ ተሰኘ፡፡ በካሪቢያን ታላቁ የአውሎ ነፋስ አደጋ ከደረሰ ዛሬ 233ኛ ዓመቱን ደፈነ፡፡ ድንገት ደራሹ ታላቁ አውሎ ነፋስ መነሻው ይሄ ነው ተብሎ አልተለየም፡፡ ነገር ግን እንደ ብዙዎቹ የአትላንቲክ ውቅያኖስ አውሎ ነፋሶች መነሻው  ከምዕራብ አፍሪካ ከኬፕቬርዴ የባሕር ዳርቻ ሊሆን እንደሚችል መላ ምቱ የሰፋ ነው፡፡

አውሎ ነፋሱ ወደ ባርባዶስ ግዛት ሲጠጋ ኃይሉም የመምዘግዘግ አቅሙም ጨመረ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: መስከረም 28,2006

መስከረም 28,2006

አርጀንቲናዊው ኤርኔስቶ ቼጉቬየራ፣ በትምህርቱም፣ በሙያውም፣ ሐኪም ቢሆንም፣ ዓለም በብዙ የሚያወቅው በግራ ክንፈኛ ተዋጊነቱ ነው፡፡ ኤርኔስቶ ቼ ጉቬየራ፣ በዓለም ዙሪያ፣ በነፃነት አላሚ ወጣቶች፣ ልቦና ውስጥ እንዳደረ ቦሊቪያ ውስጥ በዓላማ ተፃራሪዎቹ እጅ የገባውና የተማረከው የዛሬ 46 ዓመት በዛሬዋ እለት ነው፡፡ ቼ-ጉ- ቬየራ፣ የቤተሰብ መሠረቱም ሆኖ ሲበዛ ለድሆች ለተገፉና ለተጨቆኑ ተቆርቋሪ ሆኖ አደገ፡፡ በወጣትነት ዘመኑ፣ በብዙ የላቲን አሜሪካ አገሮች ተዘዋውሯል፡፡ ይህም በዘመኑ፣ በየአገሩ መንግስታት ጭቆና የሚፈፀምባቸውን የተገፉ፤ ፍትህ የራቃቸውና የተበደሉትን ዜጐች በቅርበት ለማየት አስችሎታል፡፡ቼ፣ይሄን ካየ በኋላ፣ የጭቆናው ቀንበር መሠባበር እንዳለበት አመነ፡፡  

በዚያን ዘመን በሜክሲኮ በሙያው እየሠራና በዩኒቨርስቲ እያስተማረ በነበረበት ወቅት ከኩባውያኑ ወንድማማቾቹ ራውልና ፊደል ካስትሮ ጋር ተዋወቀ፡፡

እነሱም፣ በአገራቸው የተንሠራፋውን ጭቆና መታገያ፣ መላ ለመፈለግ በሜክሲኮ መገኘታቸውን ነገሩት፡፡

የቼጉቬየራና የካስትሮ ወንድማማቾች እውቂያቸው ወደ ዓላማ አጋርነት ተሸጋገረ፡፡
ወደ ኩባ ለመዝመት፣ የወታደራዊና የሸምቅ ውጊያ ልምምድ ውስጥ ገቡ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: መስከረም 27,2006

መስከረም 27,2006

ለአሜሪካና አሜሪካውያን የመስከረም አንዱ የሽብር ጥቃት ዘግናኝ ትውስታቸው ሆኖ እንደዘለቀ ነው፡፡የአልቃይዳ የሴራ ዱለታ ውጤት የሆነውና 3 ሺህ ገደማ ሰዎች ያለቁበት የመስከረም አንዱ የሽብር ጥቃት የፅንፈኝነት ክፋት እስከምን እንደሚደርስ አሳይቷል፡፡አሜሪካና ምዕራባዊያን አጋሮቿ በታሊባን አልቃይዳ ጥምረት ላይ በአፍጋኒስታን የፀረ ሽብር ዘመቻቸውን የከፈቱት የዛሬ 12 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡የሶቪየት ኃይሎች አፍጋኒስታንን ለቀው እንዲወጡ የአንበሳውን ድርሻ የተወጡት ሞጃኸዲኖች ከ20 ዓመታት በፊት በሞስኮ ሳምባ ይተነፍስ የነበረውን የኘሬዝዳንት ናጂቡላህን አስተዳደር ከነበሉት፡፡ሙጃኸዲኖቹ ለስልጣን ቢበቁም በመካከላቸው ስምምነት ጠፋ፡፡በየአንጃውና በጐበዝ አለቃ እየተቧደኑ ወደ መተጋተጉ ገቡ፡፡ብዙም ሳይቆዩ መንግሥታዊ አቋማቸው ተዳከመ፡፡                  

ታሪክን የኋሊት: መስከረም 24,2006

መስከረም 24,2006

ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት ሩሲያ ሕገ-መንግስታዊ ቀውስ ገጠማት፡፡ ፖለቲካዊ ቀውሱ ፖለቲካዊ መፍትሄ አጣ፡፡ ፖለቲካዊ መፍትሔ በመታጣቱ ታንኮችና ታንከኞች ለመፍትሄ ተሰለፉ፡፡ የዛን ጊዜው የሩሲያ ፌዴሬሸን ፕሬዝዳንት ቦሪስ የልሲን በሞስኮ የሚገኘውንና ነጩ ቤት የተሰኘውን የፓርላማ ሕንፃ በታንክ ያስቀጠቀጡት የዛሬ 20 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ ጊዜው ለሩሲያ ጥሩ አልነበረም፡፡ የሕዝቡ የኑሮ ደረጃ ከቀዳሚዎቹ ጊዜያት ሲነፃፀር አሸቆለቆለ ምጣኔ ሐብቷ ላሸቀ፡፡የኑሮ ውድነቱ እንደ ሮኬት ተወነጨፈ፡፡ ሙስና ጣራ ነካ፡፡ በዚህ ላይ የፓርላማው የሕግ መምሪያ ምክር ቤትና ፕሬዝዳንቱ በእኔ አበልጥ እኔ እበልጥ ትንቅንቅ ውስጥ ገቡ፡፡

ፕሬዝዳንቱ አንዳች ውሳኔ ሲያሳልፉ ፓርላማው ተቃራኒ ሕግ ያወጣል፡፡
አንዱ አንድ ውሳኔ ሲያሳልፍ፤ ሌላኛው ያን ውሳኔ ይሸራል፡፡ ይገለብጣል፡፡
መቻቻል ጠፋ፡፡ መፍትሄ ታጣ፡፡
ሕጉ ባይፈቅድላችውም ፕሬዝዳንቱ ፓርላማውን በትኛለሁ አሉ፡፡
ፓርላማው በበኩሉ ፕሬዝዳንቱን ከኃላፊነታቸው አንስቻለሁ፤ ምክትላቸውን አሌክሳንደር ሩስኮይን ሹሜያለሁ ሲል አወጀ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: መስከረም 23,2006


መስከረም 23,2006

በ19ኛው ክፍለ ዘመን፣ 2ኛ አጋማሽ፣ ኦቶ ቮን ቢስማርክ የተበጣጠቁ ግዛቶችን በመሠብሰብ የተዋሐደችና የጠነከረች ጀርመንን ፈጠረ፡፡ ጀርመን፣ ከ2ኛው የዓለም ጦርነት በኋላ፣ የደረሰባት የምስራቅ ምዕራብ መከፋፈል አብቅቶ እንደገና የተዋሐደችው  የዛሬ 23 ዓመት በዛሬዋ እለት ነው፡፡ በ20ኛው ክፍል ዘመን የመጀመሪያ ሩብ፣  ወደ ስልጣን የመጣው ኦዶልፍ ሂትለርና የናዚዎች የፖለቲካ ማህበር፣ ዓለምን በጦር ኃይል ለማንበርከክና ለማስገበር ፈለጉ፡፡ የኋላ ኋላ፣ የጫሩት የጦርነት እሳት፣ እነሱንም አቃጠለቸው፡፡ መራራ ሸንፈትን ተጐነጩ፡፡ መዘዛቸው ለአገራቸውም ተረፋት፡፡

ጀርመን፣ በአሸናፊዎቹ የህብረቱ ኃይሎች ተፅዕኖ ስር ወደቀች፡፡ በምዕራብና በምስራቅ ሸነሽኗት፡፡ አንዷ አገር ለሁለት ተከፈለች፡፡

በአሜሪካ፣ ብሪታንያና ፈረንሳይ፣ የተፅዕኖ ክልልነት የቆየው  ምዕራባዊ ግዛት፣ ምዕራብ ጀርመን ወይም የጀርመን ፌዴራላዊ ሪፖብሊክ ተባለ፡፡
በሶቪየቶች ይዞታነት የቆየው ምስራቃዊ ክፍል ምስራቅ ጀርመን ወይም የጀርመን ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ሆነ፡፡ በሞስኮ ሳምባም ሲተነፍስ ቆየ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers