• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 08,2006

ጥቅምት 08,2006
አላስካ በስፋቷ ከአሜሪካ ግዛቶች የሚያስተካከላት የለም፡፡ከ52 የአሜሪካ ግዛቶች አርባ ስምንቱ በአንድ ቢጠቃለሉ አላስካን አያህሏትም፡፡ በጣሙን ሰፊ ነች፡፡ ግዛቲቱ እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን 2ኛ አጋማሽ መጀመሪያ የሩሲያ የግዛት አካል ሆና ቆይታለች፡፡ አሜሪካ ይህችን ሰፊ ግዛት ከሩሲያ ላይ የገዛችው በ7 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ ከሽያጭና ግዢው ስምምነት በኋላ በሩሲያ አስረካቢነት በአሜሪካ ተረካቢነት አላስካ በይፋ ወደ አሜሪካ ከተላለፈች ዛሬ 146ኛ ዓመቷን ደፈነች፡፡ እንደሚባለው በዘመኑ ሩሲያውያኖቹ የራቀች ግዛታችንን አንድ አቅሙ የበረታ ኃያል ቢቀማንስ የሚል ስጋት አደረባቸው፡፡ሰዶ ማሳደድ ሆኖብን እንዳንቆጭ ሸጠን ብንገለገልስ ብለው አሰቡ፡፡

የወቅቱ የአሜሪካ የፖለቲካ መሪዎች ደግሞ የዚያን ጊዜዋን ዱር ግዛት አላስካን ለመግዛት አላቅማሙም፡፡ 7 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላራቸውን ለሩሲያውያኖቹ ለመክፈል አይናቸውን አላሹም፡፡  

አንዱን ሄክታር መሬት ከአራት የአሜሪካ ሳንቲም ባልበለጠ ዋጋ  አሜሪካውያኑ አላስካን በእጃቸው አስገቧት፡፡

ዛሬ ላይ ታሪኩ ሌላ ሆኖ ቢታይም በዚያን ዘመን አላስካ እንድትገዛ የተዳራዳሩና ግዢውን የፈቀዱ መሪዎችገንዘባችንን ዱር በተኑት ተብለው ከተቃዋሚዎቻቸው መብጠልጠላቸው መነቀፋቸው አልቀረም፡፡

እነኛ የግዢው ተቃዋሚዎች ዛሬ ቢኖሩ ኖሮ በውሳኔያቸውና በእርምጃቸው የነቀፉ ያዋረዱአቸውን መሪዎች ምን ያህል ምስጋና ክብርና ሞገስ በቸሯቸው ነበር፡፡

ሌላው ሌላው ቢቀር እንኳ አሜሪካ ካላት የነዳጅ ዘይት ክምችት 25 በመቶ ያሕሉን  ክምችት የታቀፈው የአላስካ ማህፀን ነው፡፡

እንደ አሳ ካሉ የአሜሪካ የባሕር ውስጥ ምግቦች ከግማሽ በላይ የሚሆነው የአላስካ በረከት ነው፡፡
አላስካ ለአሜሪካውያን የፀጋ ምድር መሆኗን ማስመስከር የጀመረችው ከሽያጩ ብዙም ባልራቀ ጊዜ ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 07,2006

ጥቅምት 07,2006

እስራኤልና አረቦች አነስተኛዎቹን ቁርቋሶዎች ሳይጨምር በታሪክ በታላቅነታቸው የሚጠቀሱ ቢያንስ ሦስት ጦርነቶችን አካሂደዋል፡፡ የአረብ የነዳጅ አምራችና ላኪ አገሮች ማህበር ከአይሁዳውያን በዓል በተቀዳው ስም የዮም ኪፑር ጦርነት ተብሎ ከሚታወቀው ውጊያ በኋላ በምዕራባዊያን አገሮች ላይ ያነጣጠረ ማዕቀብ የጣለው የዛሬ 40 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ እስራኤል ከ65 ዓመት በፊት እንደ አገር እንደተመሠረተች ከአረቦች ጋር ተዋግታ አሸንፋለች፡፡ ከዚያም በኋላ ከ46 ዓመት በፊት በተካሄደው ጦርነት ከአረቦች ጋር ተዋግታለች፡፡
በታሪክም የስድስቱ ቀን ጦርነት ተብሎ ይታወቃል፡፡ እስራኤል በስድስቱ ቀን ጦርነት ከፍልስጤማውያን ምስራቅ እየሩሳሌምን ቀማች፡፡ ወደ ጋዛ ሰርጥና ዌስት ባንክም ተስፋፋች፡፡  

ከግብፅ የሲናይ ልሳነ ምድርን በእጇ አስገባች፡፡
ከሶሪያ የጐላን ኮረብታን ቀማች፡፡
ከ6ቱ ቀን ጦርነት ስድስት ዓመታት በኋላ በግብፅና ሶሪያ አስተባባሪነት አረቦች በእስራኤል ላይ ጦርነት ከፈቱባት፡፡ ጦርነቱ በታሪክ የዮም ኪፑር ጦርነት ተብሎም ይታወቃል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 06,2006

ጥቅምት 06,2006

ከ26 ዓመት በፊት በዚህ ሰሞን የዛን ጊዜዋን ‹‹ሕፃን ጄሲካ›› ከአሜሪካም አልፎ መላው ዓለም አወቃት፡፡ ወሬዋ ከአድማስ አድማስ ተዳረሰ፡፡ ዝነናዋ ናኘ፡፡ጄሲካ ዝነኛ የሆነችው ዝና ፈልጋ አልነበረም፡፡ የዝናን ጣዕም መረዳትና የዝናን ጣጣ መሸከም በማትችልበት ጨቅላ እድሜ ላይ ነበረች፡፡ የዛን ጊዜዋን ሕፃን ጄሲካ በሚድላንድ በሚገኝ ቤታቸው አቅራቢያ ባለ ሜዳ ከእድሜ እካዮቿ ጋር ስትጫወት ከገባችበት ከ6 ሜትር በላይ ጥልቅ በሆነ ጠባብ ጉድጓድ ከሁለት ቀናት እልህ አስጨራሽ የነፍስ አድን ጥረት በኋላ በሕይወት የወጣችው የዛሬ 26 ዓመት በዛሬዋ እለት ነው፡፡ ከመጥፎው አጋጣሚ ሁለት ቀናት አስቀድሞ ጄሲካ በእናቷ የቅርብ እይታ ውስጥ ሆና ከአራት ሌሎች የሷ ብጤ ሕፃናት  ጋር እየተጫወተች ነበር፡፡

ከወደ ቤት የስልክ ጥሪ ሲንጫረር የሰማችው የጄሲካ እናት ልጆቹን እዛው ትታ ወደ ቤት ትዘልቃለች፡፡  

ወዲያውኑ ከጄሲካ ጋር ሲጫወቱ የነበሩ ሕፃናት እየተጯጯሁ  ወደ ጄሲካ እናት ተሯሩጠው ገቡ፡፡  ልጆቹ የተጯጯሁት ጄሲካ 20 ሴንቲ ሜትር መጠነ ዙሪያና ከ6 ሜትር በላይ ጥልቀት ካለው ጠባብ ጉድጓድ በመግባቷ ነበር፡፡

እናት በጄሲካ መጥፎ እጣ የምትሆነው አጣች፡፡ ለፖሊስ ደወለች፡፡
ፖሊሶች በ3 ደቂቃ ውስጥ ከተፍ አሉ፡፡ ግን ፓሊሶቹ ምንም  ነገር አላመጡም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 04,2006

ጥቅምት 04,2006

በቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን አሜሪካና ሶቪየት ኅብረት በየፊናቸው ተባባሪና ተቀጥላዎቻቸውን ከየጐናቸው በማሰለፍ እርስ በርስ በወዮልህ ሲዛዛቱ ፣ ሲጠላለፉ ፣ ሲሻኮቱ ኖረዋል፡፡በዚያ ዘመን ወደ ከፋ የኒኩሊየር ፍጥጫና ቀውስ የገቡት ልክ የዛሬ 51 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡በታሪክም የኩባው የሚሳየል ቀውስ ተብሎ ይታወቃል፡፡ከቀውሱ ጥቂት ዓመታት በፊት የቀድሞው የኩባ መሪ ፊደል ካስትሮ ከትጥቅ ጓዶቻቸው ጋር ባካሄዱት አመፅ የጄኔራል ባቲስታን መንግሥት አሸቀነጠሩት፡፡የአስተዳዳር ዘይቤያችን ሶቫሊስታዊ ነው አሉ፡፡
አሜሪካ የማይዋጥላት ሶቫሊስታዊ የአስተዳዳር ዘይቤ ከደቡባዊ ግርጌዋ ባለችው በኩባ ሥር መስደዱ አደጋው ገዝፎ ታያት፡፡

ከመጀመሪያዎቹ ቀናት አንስቶ በኩባ የካስትሮን አስተዳደር መንግሎ ለመጣል ያልፈነቀለችው ድንጋይ የለም፡፡
በአሜሪካ የሚኖሩ ኩባዊያንን በጦር አሠልጥና ዴሴቲቱን ለመውረር ሞክራለች፡፡
ይሄ ሙከራ ቢከሽፍባት ኩባን በራሷ ኃይል ለመውረር ተዘጋጀች፡፡
በዚህ የሰጉት ካስትሮ ከዋሽንግተን ወረራ እንድታስጥላቸው ከሞስኮ ጋር ተሻረኩ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 01,2006

ጥቅምት 01,2006

የሰሜናዊ ሶሪያዋ ከተማ አሌፖ ዛሬ ላይ ወደ ጦር ሜዳነት ተለውጣለች፡፡እንዳሁኑ የርዕደ መሬት መለኪያ /ሬክተር ስኬል/ ባልነበረበት ዘመን  አሌፖን ያርገፈገፋት እጅግ ከፍተኛና ዘግናኝ የመሬት ነውጥ የደረሰው የዛሬ 875 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ነፃነታችንን፤ መብታችንን  ያሉ የሶሪያ አማፂያንና የፕሬዝዳንት ባሻር አል አሳድ ወታደሮች ከፍተኛ ትንቅንቅ እያደረጉባት ነው፡፡ሞትና ግድያ ከእለት እለት እየባሰና እየከፋባት  ነው፡፡ ከዚህም ቀደምም የአሁኑ ፕሬዝዳንት የባሻር አል አሳድ አባት ሐፌዝ አል አሳድ ከተማይቱን በጦር ቀጥተዋታል፡፡አሌፖና አካባቢዋ ከ870 ዓመታት በፊትም ከአውሮፓውያን ጋር ይካሄድ በነበረ ውጊያ የጦር አውድማ ነበረች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers