• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 15,2006

ጥቅምት 15,2006

የቻይና ሪፐብሊክ ተብላ ትታወቅ በነበረችው ታይዋን፣ ተይዞ የቆየው የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባልነት፣ መቀመጫዋ ተነጥቆ፣ ማዕከሏን ቤጂንግ ላደረገችው የቻይና ሕዝባዊት ሪፖብሊክ ከተሰጠ፣ ዛሬ 42ኛ ዓመት ሆነው፡፡የነገሩ ስረ መሠረት፣ የዛሬ 63 ዓመት፣ በሊቀ መንበር ማኦ ዜዱንግ የሚመሩት የቻይና ኮሚኒስት ሸምቅ ተዋጊዎች፣ የብሔረተኛውን የሻንጋይ ሼይክ አስተዳደር መነገሉት፡፡ በኦፊሴላዊ መጠሪያዋ፣  የቻይና ሕዝባዊ ሪፖብሊክ የምትባለዋን አገር መሠረቱ፡፡በኮሜንታንግ የፖለቲካ ማህበር ይመራ የነበረው ፣ተሸናፊው የብሔረተኞች መንግስት፣ ከነ ጓዙ፣ ወደ ታይዋን ደሴት ተሰደደ፡፡ በዚያም የቻይና ሪፖብሊክ የሚል መጠሪያ የሰጣትን አገር ፈጠረ፡፡እንደተባበሩት መንግስታት ባሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ቻይና የምትወከለው መቀመጫውን ታይዋን ባደረገው፣ የቻንጋይ ሼይክ መንግስት ሆነ፡፡ የቻይና ሕዝባዊት ሪፖብሊክ የተሠኘችው፣ የዛሬይቱ ታላቋ ቻይና፣ ይፋዊ እውቅና ተነፍጓት ቆየች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 14,2006

ጥቅምት 14,2006

ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች ሲነሱ፣ የተባበሩት መንግስታት ከነዘርፍ ቅርንጫፎቹ  በምድራችን፣ የድርጅቶች አውራ ሆኖ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ፣ ሕልውና አግኝቶ፣ በይፋ ስራውን ከጀመረ፣ ዛሬ 68ኛ ዓመቱን ደፈነ፡፡ መልካም ልደት አንጋፋው ድርጅት፡፡ ምድራችን ካስተናገደቻቸው ዘግናኝ፣ደምሳሽና ሕዝብ ጨራሽ ጦርነቶች መካከል የ1ኛው የዓለም ጦርነት  አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡በዚያ ዘግናኝ እልቂት ውስጥ ያለፉ አገሮች፣ እንዲህ አይነቱን እልቂት የሚያስቀር የሰላም ደጋፊ ማህበር ያሻናል አሉ፡፡ ማህበር አቋቋሙ፡፡ ስሙንም ሊግ ኦፍ ኔሽን፣ የመንግስታት ማህበር አሉት፡፡ የመንግስታቱ ማህበር ግን ስለ ሰላም መቆም ስለ ሰላም መስራት ተሳነው፡፡ አፍሪካዊት አባሉ ኢትዮጵያ በፋሸስቶች ስትወረር ቸልተንነትን አሳየ፡፡ ለተኩላዎች አሳልፎ ሰጣት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 13,2006

ጥቅምት 13,2006
የዛሬ 11 ዓመት፣ በዛሬው እለት ፣በሞስኮ የዱብሮቭካ አካባቢ ቲያትር ቤት፣ ጢም ብሎ ሞልቷል፡፡ዕድምተኞች፣ አገር አማን ብለው ኖርድ ኦስት የተሰኘውን ሙዚቃዊ ትያትር ይከታተላሉ፡፡ ተዋንያኑም ሙሉ  ትኩረታቸውን ትያትሩ ላይ አድርገው ትውናቸው ላይ ነበሩ፡፡ ሙዚቀኞቹም በየድርሻቸው፡፡ 2ኛው ገቢር ላይ፣ ትያትር ቤቱ ወደ አሰቃቂና አስፈሪ የትዕይንት ስፍራነት ተለወጠ፡፡ ከ40 የማያንሱ እስከ አፍጢማቸው የታጠቁ የቼችኒያ ደፈጣ ተዋጊዎች ተመልካቾቹን፣ተዋንያኑን ሙዚቀኞቹን፤ እገሌ ከእገሌ ሳይመርጡ በእገታ ስር አዋሉ፡፡ በ2ኛው የቼችኒያ ዘመቻ፣ ወደ ግዛቲቱ የዘመቱ የሩሲያ ወታደሮች፣ በ1 ሳምንት ጊዜ ለቀው እንዲወጡ ጠየቁ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 12,2006

ጥቅምት 12,2006

ቻርልስ አርተር ፍሎይድ፣ በዘረፋና በውንብድና ድርጊቱ፣ በዘመኑ አሜሪካን መከራዋን አሳይቷታል፡፡ መልከመ- መልካምነቱ የሚነገርለት ፍሎይድ፣ በታሪክም መልከ ቀናው ልጅ፣ በሚል ቅፅሉ ይታወቃል፡፡ መልከ ቀናው ልጅ፣ አሜሪካን በዘረፋ፣ በውንበድናና በግድያ ወንጀል መከራዋን ሲያሳያት ቆይቶ፣ በፀጥታ ኃይሎች የተገደለው፣ የዛሬ 79 ዓመት  በዛሬዋ እለት ነበር፡፤ ሎይድ በልጅነቱ በምንተፋ ተለከፈ፡፡በ18 ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእስር ቤት ጋር ተዋወቀ፡፡ ያኔ ለእስር የበቃው ከአንድ ፖስታ ቤት የ3 ዶላር ተኩል ሳንቲሞችን በመመንተፍ ነበር፡፡ ከእስር ቤት ቢወጣም አልታረመም፡፡ እንዲያውም ባሰበት፡፡ ከ3 ዓመታት በኋላ፣ በሚዙሪ ለአንድ ድርጅት ሠራተኞች፣ ሊከፈል የተዘጋጀን ደሞዝ ጥርግርግ አደርጐ ዘረፈ፡፡ የአምስት ዓመት እስር ተፈረደበት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 11,2006

ጥቅምት 11,2006
የዛሬዋ ዕለት በሶማሊያ ታሪክ ልዩ ሥፍራ ካላቸው ቀኖች አንዷ ነች፡፡በሜጄር ጄኔራል ሲያድ ባሬ የተመሩ ወታደሮች ሥልጣን የጨበጡበት የዛሬ 44 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡ከመፈንቅለ መንግሥቱ ቀደም ብሎ በአገሪቱ ታሪክ 2ኛው ፕሬዝዳንት በነበሩበት አብድረሺድ ዓሊ ሸርመርኬ ላይ ፖለቲካዊ ግድያ ተፈፀመባቸው፡፡በሜጄር ጄኔራል ሲያድ ባሬ የተመራው ወታደራዊ ስብስብ ላዕላይ አብዮታዊ ምክር ቤት ያለውን አካል ሰየመ፡፡ሲያድ ባሬ የአድራጊ ፈጣሪው ምክር ቤት የበላይና የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆኑ፡፡ራሳቸውን “ጓድ” ያሰኙት ሲያድ ባሬ የምንከተለው ፖለቲካዊ መስመር ሳይንሳዊ ሶሻሊዝም ነው አሉ፡፡ኢንዱስትሪዎች ፣ ባንኮችና ታላላቅ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ተወርሰው ወደ መንግስት ይዞታነት ተዛወሩ፡፡

ሲያድ ባሬ ከኢትዮጵያ የኦጋዴን ግዛት ፣ ከኬንያ ሰሜን ምሥራቅ ክፍሏንና ጂቡቲን እንዳለ ወደ ሶማሊያ የማጠቃለል ‹‹የታላቋ ሶማሊያ›› ክፉ ኃሳብ አደረባቸው፡፡   
           
በኢትዮጵያ ከአፄ ኃይለ ስላሴ ሥርዓት መወገድ በኋላ በአገሪቱ የተፈጠረው ፖለቲካዊ ግርግርና የእርስ በርስ ጦርነት ባሬ ለክፉ ውጥናቸው ዳር መድረስ የምቹ ምቹ ሆኖ አገኙት፡፡
የታላቋ ሶማሊያ ቅዠታቸውን ሥራ ላይ ለማዋል በኢትዮጵያ ላይ መጠነ ሰፊ ወረራ ፈፀሙ፡፡
ወረራው እንደ ጅምራቸውም እንደ ኃሳባቸውም አልሆነም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers