• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 25,2006

ጥቅምት 25,2006
የእሥራኤል የፖለቲካና መንግሥታዊ መሪ እንዲሁም ከፍተኛ የጦር መኮንን የነበሩት ይስሃቅ ራቢን ከተገደሉ ዛሬ ልክ 18 ዓመት ሆናቸው፡፡ ይስሃቅ ራቢን እስራኤል ከ65 ዓመት በፊት መንግሥታዊ ሕልውና ከማግኘቷ በፊት ጀምሮ ከአረቦች ጋር በተደረጉ ጦርነቶችና ትንቅንቆች ጉልህ ድርሻ ነበራቸው፡፡እስራኤል መንግሥታዊ ሕልውና ባገኘችበት ወቅት በኔጌቭ በረሃ በብርጌድ አዛዥነት ተዋግተዋል፡፡ኢየሩሳሌምና የዚያን ጊዜዎቹ የተለያዩ የፍልሚያ ሜዳዎች የራቢን ወታደራዊ መላና ጀግንነት የጠየቁ ሥፍራዎች ናቸው፡፡እስራኤል በአጭር ጊዜ በተለያዩ የጦር ግንባሮች አስደናቂ ድል በተቀናጀችበት የስድስቱ ቀን ጦርነት የራቢን የወታደራዊ መሪነት ድርሻ የተመሰገነ ነበር፡፡ የንጊዜ የእስራኤል ጦር ኃይል በግብፅ ፣ በሶሪያና በዮርዳኖስ ድል ሲቀዳጅ ራቢን የጦሩ ራስ ነበሩ፡፡ራቢን ከ45 ዓመታት በፊት ከእስራኤል ጦር በጡረታ ከተገለሉ በኋላ በአሜሪካ የአገራቸው አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡
                                                       
ክንሴት የተሰኘው የአገሪቱ ፖርላማ እንደራሴም ነበሩ፡፡
ከአንድም ሁለት ጊዜ የእሥራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ከመሆናቸው አስቀድሞ በሠራተኞች ጉዳይና በመከላከያ ሚንስትርነት ሰርተዋል፡፡
ራቢን ለዳግም ጠቅላይ ሚኒስትርነቱ በበቁበት አጋጣሚ የኦስሎው የሰላም ስምምነት ተፀነሰ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 21,2006

ጥቅምት 21,2006
በሕንድ ታሪክ ውስጥ፣ አንፀባራቂ ኮከብ ሆነው ያለፉ፣ ስመ ገናናዋ መሪ ኢንዲራ ጋንዲ በጠባቂዎቻቸው ከተገደሉ ዛሬ 29ኛ ዓመቱን ደፈነ፡፡ አባታቸው፣ ጃሐዋራላ ኔሩ ፣የህንድ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡ ኢንድራ ጋንዲም፣ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ጨብጠው አገር መርተዋል፡፡ ልጃቸው ራጂብ ጋንዲም እንደዚያው፡፡ እናትና ልጁ፣ ኢንድራና ራጂብ ሕይወታቸውን በግድያ በማጣታቸው፣ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ሁሉ ያመሳስላቸዋል፡፡ ኢንድራ ጋንዲ የሕንድ፣ የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆኑ፣ በዚህ የኃላፊነት ቦታ፣ ረዘም ላለ ጊዜ የመሪነት ድርሻ በመወጣት ይታወቃሉ፡፡ በኢንድራ ጋንዲ የመጨረሻ ዘመን፣ የሲክ ፖለቲከኛች ከራስ ገዝም አልፎ ከሕንድ የተነጠለ ነፃ መንግስት ይኑረን፤ የሚለውን ጥያቄ ማራገብ ያዙ፡፡

እንዲያውም ጠመንጃ አንግበው፣ ፈቃዳቸውን በአፈሙዝ ለማሟላት ተነሱ፡፡
የተወሰኑ የተገንጣዩ ክፍል ታጣቂዎች፣ ወርቃማው ቤተ መቅደስ በተሠኘው፣ የሲኮች ቤተ አምልኮ፣መሸጉ፡፡ ዋነኛ ማዘዣ ጣቢያቸውን በዚያው አደረጉ፡፡ የጦር መሳሪያ ማከማቸቱን ተያያዙት፡፡ የሐገሪቱን ሰላም፣ መረጋጋትና ደህንነት የማረጋገጥ ከፍተኛው ኃላፊነት ስላለባቸው፣ ኢንድራጋንዲ አማፂያኑ ትጥቅ እንዲፈቱ አዘዙ፡፡
ንግግሩ ፍሬ አላፈራ አለ እንጂ ለመደራደርም ምክረው ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 22,2006

ጥቅምት 22,2006

የአውሮፕላን የቦምብ ድብደባ፣ ዛሬ ላይ፣ መጠኑም አይነቱም በዝቶ ይገኛል፡፡ የአጥፊነትና የደምሳሽነት አቅሙም በከፍተኛ ደረጃ አድጓል፡፡ ዒላማን አነፍንፎ፣ በትክክል መርጦና መንጥሮ፣ ማደባየት ላይ ደርሷል፡፡አሁን አሁን፣ ሰው አልባዎቹ አሻቸው ሥፍራ ደርሰው፣ በርቀት መቆጣጠሪያ በቦምብ ጣይነቱንም ሆነ በሚሳየል ተኳሸነቱም  እየተወጡ ነው፡፡ የአውሮፕላን የቦምብ ድብደባ፣ እዚህ ከመድረሱ በፊት፣ አንድ ብላ ስራ ላይ ያዋለችው፣ ጣሊያን ነች፡፡ ሊቢያን ከኦቶማን ቱርኮች አስልቅቆ፣ የመያዝ ኃሳብ ያደረባት ጣሊያን፣ በዓለማችን የመጀመሪያው የሆነውን፣ የአውሮፕላን የቦምብ ድብደባ የፈፀመችው፣ የዛሬ 102 ዓመት፣ በዛሬዋ እለት ነው፡፡  

በዘመኑ ነቃ ነቃ ማለት የጀመረችው ጣሊያን፣ እንደነ እንግሊዝና ፈረንሳይ የቅኝ ግዛቶችን  የመያዝ ፍላጐት አደረባት፡፡

በወቅቱ ፣የሰሜን አፍሪካንና የመካከለኛው ምስራቅን ተቆጣጥረው የነበሩት፣ የኦቶማን ቱርኮች እየተዳከሙ ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 20,2006

ጥቅምት 20,2006

በዛሬዋ አሜሪካ አፍሪካ አሜሪካዊው ባራክ ኦባማ, በምርጫው አሸንፈው, ወደ ዋይት ሐውስ ገብተው በ2ኛው ፕሬዝዳንታዊ የስራ ዘመናቸው ላይ ናቸው፡፡የባራክ ኦባማ ስኬት፣ ከአራት አስርት ዓመታት በፊት የማይሞከርም የማይታስብም ነበር፡፡ የቅርብ እስከሚባሉ ጊዜዎች ድረስ፣ አፍሪካ አሜሪካውያን፣ በዘር መድልኦ ሲጨቆኑና ሲበደሉ፣ የቆዩባቸው ጊዜያት እንደነበሩ፣ ታሪክ ያስታውሳል፡፡ በራቁ ዘመኖች ደግሞ፣ የአፍሪካ አሜሪካውያኑ ህይወት፣ ከአሠቃቂ ባርነት ጋር የተቆራኘ ነበር፡፡በአሜሪካ ቨርጂንያ ‹‹ናት ተርነር›› የተሰኘው ባሪያ የመራው አመፅ፣ ከባሮች እምቢታዎች አንዱ ሆኖ፣ በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡በተርነር የተመራው አመፅ ከሽፎ፣ ሰውየው በባሪያ አሳዳሪዎቹ የተያዘው፣ የዛሬ 181  ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 19,2006

ጥቅምት 19,2006

ዓለማችን፣ በተለያዩ ጊዜዎች ከፍተኛ የምጣኔ ሐብት ፈተናዎች ገጥመዋታል፡፡ እንደጐርጐሮሳዊው የዘመን ቆጠራ ከ1920ዎቹ መጨረሻ አንስቶ፣ ለተወሰኑ ዓመታት የዘለቀውን ታላቁን ምጣኔ ሐብታዊ ምስቅልቅል /ዘ ግሬት ዴፕሬሸንን/ የሚስተካከል የለም፡፡ አስቀድሞ፣ ባልታሰበ አውሎ ነፋስና ማዕበል የተመታ ያህል፣ የኒውዮርክ የአክሲዮን ገበያ፣ በታሪክ ታላቅ የተባለ ውድቀት የደረሰበት፣ የዛሬ 84 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ የኒውዮርክ የአክሲዮን ገበያ፣ ታላቁን ውድቀት ያስተናገደው፣ ያን ጊዜ በእለተ ማክሰኞ ስለነበር፣ በታሪክ ‹‹ጥቁሩ ማክሰኞ›› የሚል ቅፅልን አፍርቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers