• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት: ህዳር 02,2006

ህዳር 02,2006

በፍልስጤማውያን የነፃነት ትግል ታላቅ አሻራቸውን ያኖሩት ያሴር አረፋት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የዛሬ 9 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ አራፋት ከለጋ ወጣትነታቸው አንስቶ ራሳቸውን የፍልስጤም ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ እንዲወስን ያልሆኑት ፤ ያላደረጉት የለም፡፡የፍልስጤም ነፃ አውጭ ድርድት /PLO/ የትጥቅና የፖለቲካ አንጃ የሆነውን የፋታህ ንቅናቄ በመመሥረት ከእሥራኤል ጋር በጦር መሣሪያ ሲተጋተጉ በፖለቲካ ሲተናነቁ ኖረዋል፡፡ዓላማቸውን ዳር ለማድረስ ብዙ ላይ ታች ብለዋል፡፡ ስደትን ደጋግመውታል፡፡እሥርን አይተውታል፡፡  የቁም እሥር ተደጋግሞባቸዋል፡፡አንዱ ሲያቀርባቸው ሌላው ፊቱን አዙሮባቸዋል፡፡ ብዙ መከራና ብዙ ወጣ ወረድ ተፈራርቆባቸዋል፡፡ነፃይቱን ፍልስጤም ለማየት የነበራቸውን ሕልም ዕውን ለማድረግ ዕድሜ ዘመናቸውን ሰውተዋል፡፡ከ20 ዓመታት በፊት የተፈረመው የኦስሎው ስምምነት ሕልማቸውን ወደ ዕውንነት አቅርቦት ነበር፡፡
                                                         
የኦስሎው ስምምነት መሬት ለሰላም ተባለ፡፡
ከእሥራኤል ጋር ቅርሾ ፣ ጠላትነቱና ቁርቁሶው ማብቃቱን ጠየቀ፡፡
ፍልስጤምን ደረጃ በደረጃ ወደ ነፃ አገርነት የሚያሸጋግረውን መሠረት ጣለ፡፡
ለዚህም ፍልስጤማውያን የከፊል ራስ ገዝ የአስተዳደር መብት አገኙ፡፡
የፍልስጤም ነፃ አውጭ ድርጅት /PLO/ የእስራኤልን ሕልውና በይፋ አውቃለሁ አለ፡፡
እስራኤልም ለPLO እውቅና ሰጠችው፡፡

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 29,2006

ጥቅምት 29,2006
በጀርመን የናዚዎቹ መሪ አዶልፍ ሂትለር ዓለምን ወደ ጦርነት ሲመራና  ሊያንደረድራት በአዕምሮው ክፉ ኃሳብ ፀንሶ ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ ከነ ክፉ ኃሳቡ እንዲጠፋ የበረከቱ የግድያ ሙከራዎች ተደርገውበታል፡፡ ከሙከራዎቹ አንዱ በሙኒክ የተቃጣበት የዛሬ 74 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ ሂለትር በሙከራው ወቅት በሙኒኩ አዳራሽ የተገኘው ከዚያን ጊዜ 16 ዓመታት ቀደም ብሎ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያካሄደበትን 16ኛ ዓመት ከጥፋት እድምተኞቹና ደቀ መዝሙሮቹ ጋር ለማክበር ነበር፡፡ ከዚያ በፊት ሲያደርገው እንደነበረው ሁሉ በቀስቃሽ ስብከቱ ስለ ወደፊቱ እኩይ ዓለማው ስለጀርመን የታላቆች ታላቅነት ሰበከ፡፡ ደስኮረ፡፡ በዚህን ጊዜ በአዳራሹ አስቀድሞ የተጠመደው ቦንብ መፈንጃው ጊዜ ተቃርቦ ሰዓቱ ጢቅ ጢቅ እያለ ነበር፡፡

በጥብቅ የጊዜ ሰሌዳ ከወዲያ ወዲህ ይል የነበረው ሂትለር ንግግሩን ገትቶ ለሚጠብቀው የሽቱትጋርት ጉዞ አዳራሹን ለቆ እንዲወጣ በአጃቢዎቹና ረዳቶቹ ምልክት ተሰጠው፡፡

ሂትለር በአጅብ ተጉዞ ባቡር ጣቢያ እንዲደረሰ ንግግር ያደረገበት አዳራሽ በ12 ደቂቃ ልዩነት በፈንጂ መጐኑ ተሠማ፡፡

በአደጋው ስምንት ሰዎች ተገደሉ፡፡ 60 ያህሉ ደግሞ ክፉኛ ቆሰሉ፡፡

ፈንጂውን አጠመደ የተባለው ጆርግ ኢለር የተባለው ጦርነት ተቃዋሚ ግለሰብ ነው ይባላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 28,2006

ጥቅምት 28,2006
ዶክተር ሪቻርድ ሶርጌይ ከቀንደኛዎቹ የሶቪየት ሰላዮች አንዱ ተደርጐ ይቆጠራል፡፡ ሰላዩ በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ለዓመታት የጃፓንንና የጦር ተባባሪዎቿን መረጃ እያነፈነፈና እየመነተፈ ለሞስኮ ሲያቀብላት ቆየ፡፡ዶክተር ሶርጌይ በጃፓኖች ተነቅቶበት ከተያዘ በኋላ በስቅላት የተቀጣው የዛሬ 69 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ ሶርጌ ወደ ለየለት የሶቪየት ሰላይነት ከመምጣቱ አስቀድሞ በ1ኛው የዓለም ጦርነት በጀርመን ሠራዊት ውስጥ በውትድርና አገልግሏል፡፡ ከጦርነቱ በኋላ ከሃምቡርግ ዩኒቨርስቲ በዶክትሬት ዲግሪ የተመረቀው ሪቻርድ ሶርጌ በ1920ዎቹ መጀመሪያ በሚስጥር ወደ ሶቪየቶች ገባ፡፡ የስለላውን ድርጅት ተቀላቀለ፡፡ የቅድሚያ የሰላይነት ተልዕኮውን በቻይና ተወጣ፡፡

ከቻይና ተልዕኮው በኋላ ለፍራንክፈርት ዛይቱንግ መፅሔት በመስራት ለስለላ ስራው እንዲመቸው የናዚ ፓርቲ አባል ሆነ፡፡

በፍራንክፈርት ዛይቱንግ ጋዜጠኝነቱ ዝነኛና ስመ-ገናና እየሆነ የመጣው ሶርጌ በዚሁ ሙያ አዘጋጁ  ወደ ጃፓን ቶኪዮ እንዲልከው ጠየቀ፡፡
በጥያቄውም መሠረት አዘጋጁ የሰርጌን ጥያቄ ለመመለስ አላመነታም፡፡
በመፅሔቱ ዓለም አቀፍ ወሬ አቀባይነት በቶኪዮ እንዲመደብ አደረገው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 27,2006

ጥቅምት 27,2006
ኩዌትን ወርረው የነበሩት የቀድሞው የኢራቅ መሪ ሳዳም ሁሴን በአገሪቱ ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳት ማድረሳቸው ይነገራል፡፡ከ600 በላይ የነዳጅ ጉድጓዶች ላይ በለቀቁት እሳት ያስነሱትን ቃጠሎ ማስቆም የተቻለው የዛሬ 22 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ ኢራቅ ኩዌትን እስከወረረችበት ጊዜ ድረስ በነበሩት 10 ዓመታት ከኢራን ጋር  ንብረት ደምሳሽና ሕዝብ ጨራሽ ጦርነቶችን አካሄደች፡፡ የዘመኑ የኢራቅ ፕሬዝዳንት ሳዳም ሁሴን በነዳጅ ዘይት የምርት መጠንና ኮታ የተነሳ ከትንሿ ጐረቤታቸው ኩዌት ጋር አተካሮ ውስጥ የገቡት ወዲያውኑ ነበር፡፡ ኩዌት ከተቀመጠላት ኮታ በላይ ነዳጅ ለዓለም ገበያ እያቀረበች ነው ብለው በንዴት ጦፉ፡፡ ሳዳም ሌላም ሰበብ ፈጠሩ፡፡ በድምበር አካባቢ ከሩማይላ ጉድጓዳችን ነዳጃችንን እየዘረፈች ነው ሲሉ ነገር ፍለጋው ከፍ አደረጉት፡፡

ኩዌትን በነብር አየኝ ዛቱባት፡፡ ጦር ሠበቁባት፡፡
እንዳዛቱትም አልቀሩም ኩዌትን አጭር በሚባል ጊዜ ወርረው ያዟት፡፡
ሳዳም በዚህ ብቻ ሳይወሰኑ ኩዌትን 19ኛ ክፍለ ሃገሬ ነች ብለው ከኢራቅ መቀላቀላቸውን አወጁ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: ጥቅምት 26,2006

ጥቅምት 26,2006
ሲድኒ ጆርጅ ራይሊ በተባለው ልውጥ ስሙ የሚታወቀው ሰላይ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ምትሐተኛ ሰላይ ነበር ይባልላታል፡፡ የሰላዮች ቁንጮ በሚል ቅፅል የሚጠሩት አሉ፡፡ ከወዲህ ወዲያ እያምታታ ቢያንስ ለ4 አገሮች ሰልሏል፡፡ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የቭላድሚር ኤሊች ሌኒንን የቦልሼቪኮች መንግስት ከማለዳው ለመገለበጥ ያደረገው ሙከራም ልዩ መታወቂያው ነው፡፡ ራይሊ በዚሁ ሰበብ ሩሲያ ውስጥ የተገደለው የዛሬ 88 ዓመት በዛሬ እለት ነው፡፡ ውልደቱ የሩሲያ ግዛት አፄ አካል በነበረችዋ ዩክሬይን ነው፡፡ ጆርግ ሬሴምብለም ይባል ነበር፡፡ ስሙን ለውጦ ወደ ብራዚል ተሻገረ፡፡ ፔድሮ ተባለ፡፡ ከብሪታንያውያን ጋር ወደ ብሪታንያ ገባ፡፡ ሲድኒ ጆርጅ ራይሊ ተሠኘ፡፡

ወደ ሩሲያ ተሻገረ፡፡ በዚያ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ሩሲያና ጃፓን ሲዋጉ የአርቱርን ወደብ ካርታ መንትፎ  ለጃፓኖች ሸጠ፡፡

ጃፓኖች በካርታው እየተረዱ በሩሲያዎች ላይ ብርቱ ጉዳት አደረሱባቸው፡፡ ወደ ምዕራብ አውሮፓ ተሸጋግሮ በሚስጥራዊ ምጣኔ ሐብታዊ አሻጥሮችና በወታደራዊ ስለላዎች ሰርቷል፡፡

ዋነኛ አሳዳሪዎቹ የብሪታንያ የሰለላ ተቋማት የነበሩ ቢሆንም ጥቅም ያስገኝልኛል ብሎ ባሰበው ጉዳይ ወዳጅና ጠላት ሳይለይ የሠራባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ፡፡
ከባለ ሁለት ቢላነትም የዘለለ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers