• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት: ህዳር 06,2006

ህዳር 06,2006

በአሜሪካ ቦይንግ 727 የመንገደኞች አውሮፕላን መንገደኞቹን እንዳሳፈረ በ35 ሺህ ጫማ ከፍታ ከቺካጐ ወደ ዋሽንግተን እየበረረ ሳለ ከተጠመደበት የፈንጂ አደጋ የተረፈው የዛሬ 35 ዓመት በዛሬ እለት ነበር፡፡ በእለቱ በአውሮፕላኑ ላይ አንዳች የድምድምታ አይነት ድምፅ ተሠማ፡፡አውሮፕላኑ በጭስ ታፈነ፡፡ መንገደኖች በጭስ መታፈንና፣በመለብለብ ስሜት ምቾታቸውን አጡ፡፡ መንገደኖችን ምቾት የነሳቸውና በአየር ላይ ስጋት ላይ የጣለቸው ጭስ የተትጐለጐለው በፖስታ ቤት አድራሻ በተላከ ጓዳ ሰራሽ ፈንጂ የባሩድ ጭስ ነበር፡፡ ነገሩ አስጊ ስለነበረ አውሮፕላኑ በአስገዳጅ ሁኔታ ቨርጂኒያ ውስጥ ለማረፍ ተገደደ፡፡ በምንድነው ነገሩ የቀጠለው ምርመራ ሚስጥራዊው ቦምበኛ በሚል ቅፅል ወደሚታወቀው ቴድ ካዜንስኪ ያመራው ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው፡፡

ቴድ ካዜንስኪ የቦምቡ መልዕክተኛ ፤ማህበራዊ ነቃሹና ስርዓተ አልበኛው በመባል ይታወቃል፡፡
ከዚህ በፊት ግን ካዚንስኪ ከተከበረው ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: ህዳር 05,2006

ህዳር 05,2006

ዛሬ ወር ተረኛ ሆነው ዳግም አማፂ የሆኑት የአፍታኒስታን ታሊባኖች ከካቡል መንግስታዊ መንበራቸው ከተባረሩ ዛሬ 12 ዓመት ሆናቸው፡፡ አፍጋኒስታን ከ3 አስርት ዓመታት በላይ  ሰላም የላትም፡፡ ሶቪየት ህብረት በተደረገልኝ የእርዳታ ጥሪ ነው በሚል ሽፋን ወደዛች አገር ጦሯን ላከች፡፡ እምቢ ላገሬ ያሉ ሙጃኸዲኖች ጥራኝ ዱሩ አሉ፡፡ የሶቪየት ጦር እየገደለና እየሞተ ለ10 ዓመታት ቆይቶ ወጣ፡፡ በሶቪየቶች ሳምባ የሚተነፍሰው የዶክተር ናጂቡላ አስተዳደር ሲገረሰስ የሞጃኸዲን የጦር አበጋዞች ወደስልጣን መጡ፡፡ አንዱ የጐበዝ አለቃ በሌላው ላይ እንደተነሳ፤ አገር እንደታመሠ ፓኪስታን ትደግፋቸው ነበር የሚባሉት ታሊባኖች ከደቡብ አቅጣጫ ተነሱ፡፡ በፍጥነት ድል በድል ተረማምደው የሙጃኸዲኖቹን አስተዳደር አሸቀንጥረው ጣሉት፡፡ በአብዛኛው የአፍጋኒስታን ክፍል ሸሪአዊ አገዛዛቸውን አሰፈኑ፡፡
ከአልቃይዳ ጋር መለየት በሚያስቸግር ሁኔታ ከአሸባሪው ቡድን ጋር አንድ አካል አንድ አምሳል ሆኑ፡፡
የአልቃይዳው መስራች ኦሳማ ቢን ላዴንም ዋነኛ የጥፋት ማዘዣውን እዛው አፍጋኒስታን ውስጥ አደረገ፡፡
የአልቃይዳ የእጅ ስራ ነው በተባለው የመስከረም አንዱ ጥቃት የኒውዮርክ የዓለም የንግድ ድርጅት መንትያ ሕንፃዎችን ወደ ትቢያነት ቀየራቸው፡፡
ጥቃቱ ከ3 ሺህ የማያንሱ  ሰላማዊ ሰዎችን ነፍስ በላ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት: ህዳር 03,2006

ህዳር 03,2006

የ20ኛው ክፍለ ዘመን የግራ ክንፈኞች ፖለቲካዊ ጉዳይ ሲነሳ ሊዮን ትሮትስኪም አብሮ ይነሳል፡፡ከቮልሼቪኮቹ መሪ ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን ጋር በሚያሳምነው እያመነ የማያምንበትን ፊት ለፊት እየተቃወመ በስምምነትም በልዩነትም ሠርቷል፡፡ ራሱን የሌኒን አልጋ ወራሽ ካደረገው ጆሴፍ ስታሊን ፍፀማዊ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ጋር ስምምነት አልነበረውም፡፡ ሊዮን ትሮትስኪ የጆሴፍ ስታሊንን ሴራና ደባ መቋቋም አልቻለም፡፡ ስታሊን በግራ ክንፈኞቹ ፖለቲካ የገዘፈ ስም ታላቅ ምሁራዊ ተንታኝና የንድፈ ኃሳብ ቀማሪውን ሊዮን ትሮትስኪን ከቮልሼቪክ የኮሚኒስቶች የፖለቲካ ማህበሩ ከእንግዲህ ከኛ ጋር ጉዳይ የለህም ብሎ ያባረረው የዛሬ 86 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡የሩሲያ ሶሻል ዲሞክራቶች የፖለቲካ ማህበር ፖለቲከኞች ኃሳባቸው ለየቅል ሲሆን ለሁለት ተከፈሉ፡፡በሌኒን የሚመሩት ቮልሼቪኮች ተሠኙ፡፡ ትሮትስኪ ሜንሼቪክ ከተሠኙት ጋር ሆነ፡፡

ኃላም ወደነሌኒን መጣ፡፡
በቮልሼቪኮች የተመራው የጥቅምት አብዮት አፄያዊውን ስርዓተ ሲያስወግድ ትሮትስኪ የጦር ሚኒስትር ሆኖ ተሰየመ፡፡
የጦር ሠራዊቱና የባሕር ኃይሉ የበላይ ሆነ፡፡ በታሪክ ቀዩ ጦር የተሠኘውን የሶቪየት ሠራዊት በሁለት እግሩ አቁመው፡፡ ብዙም ሳይዛገይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ሆኖ ሠርቷል፡፡
ከሌኒን ሞት በኋላ በእግሩ የተተካው ጆሴፍ ስታሊን ትሮትስኪንና ሌሎች ሻል ሻል ምሁራንና ንድፈ ኃሳብ ቀማሪዎችን ጥርስ ነከሰባቸው፡፡  
በሴራው ወጥመድ ውስጥ ከተታቸው፡፡

ታሪክን የኋሊት: ህዳር 04,2006

ህዳር 04,2006
ኔቫዶ ዴላ ሩዊዝ ከጥንት ጀምሮ የኮሎምቢያ ክፉ ጠላቷ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ኔቫዶ ዴላ ሩዊዝ አደገኛ እሳት ገሞራ ነው፡፡ በየዘመኑ በየጊዜው በአካባቢው ጥፋት ሲያደርስ  ኖሯል፡፡ የአሁንም የወደፊትም ስጋትነቱ አልቀነሰም፡፡ የሩቁን ትተን የቅርቡን ብንጠቅስ እንኳ ኔቫዶ ዴል ሩዊዝ ፈንድቶ አካባቢውን በማዳረስ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የጨረሰውና የከፋ ቁሳዊ ውድመት ያደረሰው የዛሬ 28 ዓመት በዛሬዋ እለት ነው፡፡ የኮሎምቢያ ጠላት የሆነው ኒቫዶ ዴላ ሩዊዝ ከርዕሠ ከተማዋ ቦጐታ በስተምዕራብ በ129 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኙ ሠንሰላታማ ተራሮች ስር ተኝቶ ሲንፈቀፈቅ ሲከፋም እየፈነዳ ጥፋት ሲያደርስ በርካታ ዘመናትን አስቆጥሯል፡፡  
የዛሬ 28 ዓመት በዛሬዋ እለት የፈነዳው እሳተ ገሞራ ሰማይ ምድሩን በቁጣው አዳረሰ፡፡
የእሳተ ገሞራው ትፍና አመድ ሽቅብ ወደ ሰማይ እስከ 30 ኪሎ ሜትር ድረስ ጐነ፡፡
የእሳት ትፍ አመድና ቅላጩ 35 ሚሊዮን ቶን እንደሚጠጋ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
ከዚህ ውስጥ ሌላው ሌላውን ሳይጨምር 700 ሺህ ቶኑ ሰልፈር ዳይ ኦክሳይድ የተሰኘው መርዛማ ንጥረ ነገር ነው፡፡

ታሪክን የኋሊት: ህዳር 02,2006

ህዳር 02,2006

በፍልስጤማውያን የነፃነት ትግል ታላቅ አሻራቸውን ያኖሩት ያሴር አረፋት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የዛሬ 9 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ አራፋት ከለጋ ወጣትነታቸው አንስቶ ራሳቸውን የፍልስጤም ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ እንዲወስን ያልሆኑት ፤ ያላደረጉት የለም፡፡የፍልስጤም ነፃ አውጭ ድርድት /PLO/ የትጥቅና የፖለቲካ አንጃ የሆነውን የፋታህ ንቅናቄ በመመሥረት ከእሥራኤል ጋር በጦር መሣሪያ ሲተጋተጉ በፖለቲካ ሲተናነቁ ኖረዋል፡፡ዓላማቸውን ዳር ለማድረስ ብዙ ላይ ታች ብለዋል፡፡ ስደትን ደጋግመውታል፡፡እሥርን አይተውታል፡፡  የቁም እሥር ተደጋግሞባቸዋል፡፡አንዱ ሲያቀርባቸው ሌላው ፊቱን አዙሮባቸዋል፡፡ ብዙ መከራና ብዙ ወጣ ወረድ ተፈራርቆባቸዋል፡፡ነፃይቱን ፍልስጤም ለማየት የነበራቸውን ሕልም ዕውን ለማድረግ ዕድሜ ዘመናቸውን ሰውተዋል፡፡ከ20 ዓመታት በፊት የተፈረመው የኦስሎው ስምምነት ሕልማቸውን ወደ ዕውንነት አቅርቦት ነበር፡፡
                                                         
የኦስሎው ስምምነት መሬት ለሰላም ተባለ፡፡
ከእሥራኤል ጋር ቅርሾ ፣ ጠላትነቱና ቁርቁሶው ማብቃቱን ጠየቀ፡፡
ፍልስጤምን ደረጃ በደረጃ ወደ ነፃ አገርነት የሚያሸጋግረውን መሠረት ጣለ፡፡
ለዚህም ፍልስጤማውያን የከፊል ራስ ገዝ የአስተዳደር መብት አገኙ፡፡
የፍልስጤም ነፃ አውጭ ድርጅት /PLO/ የእስራኤልን ሕልውና በይፋ አውቃለሁ አለ፡፡
እስራኤልም ለPLO እውቅና ሰጠችው፡፡
Leza Vote Banner
Sheger 102.1 AudioNow Numbers