• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ሐምሌ 18፣2009

የኮንኮርድ አውሮፕላን ነገር…

ኮንኮርድ የተሠኘው ከድምፅ የፈጠነ ሱፐር ሶኒክ የመንገደኞች አውሮፕላን በ27 ዓመት የአገልግሎት ዘመኑ አንዳችም የደህንነት እንከን አልታየበትም ነበር፡፡

የዛሬ 17 ዓመት  የዛሬዋ እለት ለኮንኮርድ መራራ እለት ሆነች፡፡

በእለቱ ኤር ፍራንስ ኮንኮርድ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር 4590 ከፓሪስ በኢኳደር በኩል ወደ ኒውዮርክ ለመብረረር አኮብኩቦ ተነሳ፡፡

አየር ላይ ብዙም አልቆየ፡፡

የሚትጐለጐል የእሳት ኳስ መትፋት ጀመረ፡፡

ከአንድ ሆቴል አቅራቢያም ተከሰከሰ፡፡

በውጤቱም ከ100 መንገደኞችና ከዘጠኙ የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ለወሬ ነጋሪ የተረፈ አልነበረም፡፡ በአደጋው በመሬት ላይ የነበሩ ሌሎች አራት ሰዎችም ሞቱ፡፡

ኮንኮርድ የብሪታንያና የፈረንሳይ ትብብር የታየበት፤ የሁለቱ ሀገሮች የአውሮፕላን እነፃ ኢንጂነሮች የተጠበቡበት በዘመኑ ዘመን አፈራሽ ተብሎ የተደነቀ የተጨበጨበለት ነበር፡፡

ይህ ከድምፅ የፈጠነ ከተፎ አውሮፕላን ኢኮኖሚያዊ አዋጭነትና አትራፊነቱ ተመሠከረለት፡፡

በመንገደኞች አውሮፕላን ታሪክ በፍጥነቱ አቻም፤ ወደርም አጣ፡፡

ከፈጣንነቱ የተነሳ የአትላንቲክ ውቅያኖስ ማዶ ለማዶውን በረራ ከየትኛውም ሌላ ስሪት አውሮፕላን ባነሰ ጊዜ ማቋረጥ መቻሉ ትርፋማነቱን አሳደገው፡፡

ኤር ፍራንስንም ሆነ ብሪቲሽ ኤርዌይስን አኮራቸው፡፡ ካዝናቸውም በትርፍ ሞላው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ሰኔ 8፣2009

ጆርጅ ዋሽንግተን

የአሜሪካ ባለ አንድ ዶላር ኖት አንድ ገፅ ላይ ምስላቸው ሰፍሯል፡፡ ከግንባር ቀደሞቹ የአሜሪካ መስራች አባቶች በቀዳሚነት ይነሳሉ፡፡ እኚህ የታላቋ ሀገር መስራች አባት ጆርጅ ዋሸንግተን ናቸው፡፡

ጆርጅ ዋሸንግተን ለአሜሪካ ያልሆኑላት የለም፡፡ ድንቅ ፖለቲከኛና ቆፍጣና የጦር መሪ የተዋጣላቸው የአስተዳደር ሰውና የመጀመሪያውም የአገሪቱ ኘሬዝዳንት ነበሩ፡፡

ጆርጅ ዋሸንግተን አሜሪካ እንደ አገር ሕልውና ከማግኘቷ በፊት ለነፃነት የተነሳሳውን ጦር በአዛዥነት እንዲመሩ የተመረጡት የዛሬ 242 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

አሜሪካ የራሷ ነፃ ሀገር መሆን አለባት ለብሪታንያ ቅኝ ገዢዎች መገበሩ ይብቃን ብለው የተነሱት ኃይሎች ጆርጅ ዋሸንግተንን የጦሩ የበላይ አርገው ሲያስቀምጡ መልካምም ትክክለኛም ውሳኔ ወሰኑ፡፡

በጦር ሜዳ ሽንፈትን ጭምር የሚያውቁት ዋሸንግተን ለሕሊናቸው ግን ሽንፈትን አይነግሩትም፡፡

የጦር መለኛው፣ ቆፍጣናውና ልበ ሙሉው ዋሸንግተን ከጦር-ዘዴ አዋቂነታቸው በተጨማሪ የነፃነት አላሚውን የአሜሪካ ሠራዊት ልዩ ልዩ ክፍሎች በማስተባበር፣ በማቀናጀት በኩል ከማንም በላይ ተሳካላቸው፡፡

ጆርጅ ዋሸንግተን የመሩትን የነፃነት ጦርነት በድል ደመደሙት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ግንቦት 16፣2009

“የሄሊኮፕተር ጅማሮ”

የኛ ሀገር ወታደሮች ከእናት ያመሳስሏታል፡፡ “እናት” በሚል ቁልምጫም ይጠሯታል፡፡

ይሄ ይጐረብጠኛል ያኛው ቦታ ይቆረቁኛል ሳትል በየአስቸጋሪው መልክዓ ምድር ሳይቀር በማረፍ እጅግ አስፈላጊያቸው ነች፡፡

ስንቃቸውን፣ ትጥቃቸውን፣ ውሃቸውን ታቀርባለች፡፡ ተዋጊያቸውም ተከላካያቸውም ሆና ታግዛለች፡፡

የወታደሮቹ “እናት” ሂሊኮፕተር ነች፡፡

ትውልደ ሩሲያ አሜሪካዊው ኢጐር ኢቫኖቪች ሲኮርስኪ የመጀመሪያውን የተሳካ የሂሊኮፕተር በረራ ሙከራ ያከናወነው የዛሬ 77 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ሂሊኮፕተር ለጐማዎቿ ወይም ለብረት ክናዷ ማሳረፊያ እስካገኘች ድረስ ለማረፍ የግዴታ ሰፊ ደልዳላ ሜዳ ይሁንልኛ አትልም ስትነሳም መንደርደርም ሆነ ማኮብኮብ አያሻትም፡፡ ያው ካለችበት ቀጥ ብላ ወደላይ አየሩን ትቀዝፋለች፡፡

በአየር ላይ በአንድ ቦታ ሚዛኗን ጠብቃ መቆየት ከአውሮፕላን የምትልቅበት ቴክኒካዊ ብቃቷ ነው፡፡

በየገደላ ገደሉ በየሸለቆው መካከል መሹለክለክ ሽር ማለቱ ኧረ ስንቱ ይሄ ሁሉ የሂሊኮፕተር ገድል ነው፡፡

እንደ አውሮፕላን ሁሉ የሂሊኮፕተር መፈልሰፍ በሰው ልጅ አዕምሮ የተፀነሰው በቀደመውና በራቀው ዘመን ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ታሪክን የኋሊት፣ግንቦት 15፣2009

የቦኒ ፓርከር ነገር

በአሜሪካ ሉዚያና ቦኒ ፓርከር ‹‹ጉዞው ተፈፀመ›› ስትል ግሩም የሆነ ግጥም ፃፈች፡፡ ግጥሟንም ለእናቷ  ላከችላት፡፡ እናትየዋም ለጋዜጦች ሰጠቻቸው፡፡ ጋዜጦቹም አትመው አወጡት፡፡

ፓርከር የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በነበረችበት ወቅት የነበራት የስነ-ፅሁፍ ዝንባሌ እንዴት ያለች ታላቅ ደራሲና ግሩም ባለቅኔ ይወጣታል ተብሎላት ነበር፡፡

በመጨረሻ ግን መታዋቂያዋ ግጥምና ስነ-ፅሁፍ መሆኑ ቀርቶ ክላይድ ባሮው ከተባለ የዘራፊ ቡድን አለቃ ጋር የፍቅርም የውንብድናም ባልንጀራ ሆኖ ታሪኳ የውንብድና ሆነ፡፡

በውንብድናዋ የገጣሚነት ተስፋዋ በአጭሩ ተቀጭቶ ከነ ግብር አበሯ የተገደሉት የዛሬ 83 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

በ1930ዎቹ መጀመሪያ በታላቁ የዓለም የምጣኔ ሐብት ቀውስ አገሩን አመሰው፡፡ በዚያ ላይ የነቦኒ ፓርከር መጠነ ሰፊ ዝርፊያና ውንብድና ለአገር ምድሩ አስቸገረ፡፡

ዘራፊው ቡድን በማዕከላዊ የአሜሪካ ግዛቶች ከስፍራ ስፍራ በመዘዋወር ገጠር ከከተማ  አራቁቷል፡፡

ከትናንሽ መደብሮች እስከ ታላላቅ የገበያ ማዕከሎች ድረስ ዘርፏል፡፡ በደርዘን የሚቆጠሩ ባንኮችን ካዝና ገልብጧል፡፡

ዘጠኝ ፖሊሶች ገድሏል፡፡ የጨረሳቸው ሲቪሎች ብዛት ቤቱ ይቁጠራቸው የተሠኘላቸው ናቸው፡፡

የሕዝቡ ምሬትና እምባው በዛ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ግንቦት 14፣2009

የአሜሪካ ባሕር ሰርጓጅ መርከብ ዩ.ኤስ.ኤስ ስኮርፒዮ

ስኮርፒዮን ቃኚም ሰላይም ተዋጊም ነበረች፡፡

በሙሉ መጠሪያ ስሟ ዩ.ኤስ.ኤስ ስኮርፒዮን የተሠኘችዋ የአሜሪካ ባሕር ሰርጓጅ መርከብ  10ኛ አመት ልትደፍን አንድ አመት ሲቀራት ጥገና ተከናወነላት፡፡

የጦር መሳሪያ ስርዓቷ ሁሉም አካሎቿ በወግ በውጉ ስለመሆናቸው ፍተሻ ተደረገላቸው፡፡ ልምምድም ተካሄደባት፡፡

ከዚያም ለተልዕኮ ወጣች፡፡ ማዳረስ ያለባትን አዳረሰች፡፡ ማካለል የነበረባትን ቦታዎች አካለለች፡፡

መርከቧ ከወራት ተልዕኮ በኋላ ወደ ማረፊያዋ እየተመለሰች ሳለ በአትላንቲክ ውቅያኖስ በሳራጋሶ ባሕር ምሠራቃዊ ዳርቻ የሰጠመችው የዛሬ 49 ዓመት በዛሬው እለት ነበር፡፡

ከ99 ባሕረኞቿ ጋር መኖሪያዋን ከጥልቁ የውቅያኖስ ስርቻ አደረገች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers