• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣መጋቢት 2፣2009

የሱዳን የመሐዲስቶች ንቅናቄ

ሱዳናውያን ራሳቸውን ከብሪታንያና ከግብፅ ጥምር ቅኝ ገዢዎች ለማላቀቅ ታላቅ ተጋድሎ አድርገዋል፡፡ 

ከሱዳናውያኑ ተጋድልዎች፤ የመሐዲስቶች ንቅናቄ፤ በአገሪቱ ታሪክ ታላቅ ስፍራ የተሠጠው ነው፡፡

የመሐዲስቶቹ ጦር በካርቱም በነበሩት የግብፅና የብሪታንያ የቅኝ ገዢ ወታደሮችን መክበብ የጀመሩት የዛሬ 133 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ 
ከዚህ ጊዜ ሁለት ዓመታት ቀደም ብሎ ግብፅ በብሪታንያ ሞግዚትነት ስር ብትውልም እሷም በተራዋ ሱዳንን በስሯ አሳዳሪ ነበረች፡፡

እናም የብሪታንያ ቅኝ ገዢዎችና ግብፃውያን ሱዳንን በጥምር ሲያስተዳድሯት ቆይተዋል፡፡ 
የኡምዱርማኑ ተወላጅ ሙሐመድ ሃማድ ሱዳንን ከባዕዳን ገዢዎቿ ለማላቀቅ ቁጥር ሃሳብ አድርጐ ተነሳ፡፡

ራሱንም ‹‹መሐዲ›› ወይም ‹‹አዳኙ›› ሲል ጠራ፡፡ 
ሱዳንን ከባዕዳን ለማላቀቅ የመሠረተው የአገሬው አርበኞች ስብስብ የማሐዲስቶች ንቅናቄ ተባለ፡፡

ማሐዲ ብዙ ተከታዮችን አፈራ፡፡

ጦሩን አደረጀ፡፡

የማሐዲስቶቹ ንቅናቄ በተመሠረተ በጥቂት ዓመታት ውስጥ በባዕዳኑ ላይ የበረከቱ ድሎችን ጨበጠ፡፡ 
በጥቂት ዓመታት ጊዜ፤ በካርቱም ከተማ የሠፈሩትን የብሪታንያና የግብፅ ወታደሮች ከበባቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣የካቲት 29፣2009

የMH 370 ጉዳይ

የማሌዥያ አየር መንገድ ከጥቂት ዓመታት በፊት ሁለት ዘግናኝ አደጋዎች አጋጠሙት፡፡

ከሁለቱ ቀዳሚውና ከእንቆቅልሽም በላይ የሆነው የበረራ ቁጥር MH 370 በረራ በጀመረ 1 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ግንኙነት አቋርጦ እምጥ ይግባ ስምጥ ሳይታወቅ ከተሰወረ ዛሬ ልክ 3ኛ ዓመቱን ደፈነ፡፡

አውሮፕላኑ የዛሬ 3 ዓመት በዛሬዋ ዕለት 12 ሠራተኞችና የ15 አገሮች ዜጐች የሆኑ 227 መንገደኞችን ይዞ ከማሌዥያዋ መዲና ኳላላምፑር ተነሳ፡፡

መዳረሻው የቻይናዋ ርዕሰ ከተማ ቤጂንግ ነበረች፡፡

አውሮፕላኑ የማላያን ልሣነ ምድር እስኪያቋርጥ ወታደራዊ ራዳር ሲከታተለው ነበር፡፡

ልሣነ ምድሩን እንዳቋረጠ ከራዳሩ እይታ ተሰወረ፡፡

ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችም ጋር ግንኙነቱ ተቋረጠ፡፡

በአጣዳፊም በታይላንድ ባሕረ ሰላጤና በደቡብ ቻይና ባሕር ሕብረ ብሔራዊ ፍለጋ ተጀመረ፡፡

ፍለጋው መና ሆነ፡፡

ቀጥሎ ደግሞ የሳተላይት ግንኙነት ተንታኞች አውሮፕላኑ ደቡባዊውን አቅጣጫ ይዞ ወደ ሕንድ ውቅያኖስ ሳያመራ አይቀርም አሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣የካቲት 21፣2009

አር-ኪው አራት ግሎባል ሃውክ

ዓለማችን በአቪየሽን ታሪክ አይነታቸው አገልግሎታቸውና ስሪታቸው የበዛ አውሮፕላኖችን ታውቃለች፡፡

ዛሬ አብራሪ ለምኔ የሆኑ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ሰማዩን የሚቀዝፉበት ዘመን ላይ ተደርሷል፡፡

በሰው አልባ አውሮፕላኖች ታሪክ አር-ኪው አራት ግሎባል ሃውክ የተሠኘው ሰው አልባ አውሮፕላን ቅድምናውን ይወስዳል፡፡

አውሮፕላኑ በአሜሪካ ሰማይ እንዲበር ፈቃድ የተሠጠው የዛሬ 19 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

አውሮፕላኑ የተለያዩ መረጃዎችን የመሠብሰብና የማጠናቀር ተልዕኮ ያለው ቀልጣፋ የስለላና የቅኝት አገልግሎት ይሰጣል፡፡ 

አር-ኪው ግሎባል ሐውክ እጅግ በከፍተኛ የአየር ክልል መብረሩ አንዱ መለያው ነው፡፡

በስለላና በቅኝት አገልግሎቱም የልብ አድርስ ነው ይሉታል፡፡

አውሮፕላኑ እጅግ ከራቀው ሰማይ ምድር ላይ ያሉ መረጃዎችን ልቅም ምንጥር አድርጐ በመለየት በአንጀት አርስነቱ ይሞካሻል፡፡

ከራቀው ከፍታ ከዳመና በላይ ሆኖ በ100 ኪሎ ሜትር መጠነ ዙሪያ ሆኖ የጠላትን የመሳሪያ አቀማመጥ ምንጥር አድርጐ የመለየት ችሎታ አለው፡፡

አስገራሚው ነገር የመሳሪያዎቹ ከቦታ ቦታ ዝውውር እንኳ ቢያጋጥም ከዚህ ባለ ንስር ዓይን አውሮፕላን መሠወር የማይሞከር ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

ታሪክን የኋሊት፣የካቲት 17፣2009

በረራ 811

በዓለማችን ለቁጥር የበዙ የአውሮፕላን አደጋዎች ሲደርሱ ቆይተዋል፡፡

ንብረትነቱ የዩናይትድ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 811 የሆነው ቦይንግ 747 የመንገደኞች አውሮኘላን ለየት ያለ አደጋ የገጠመው የዛሬ 28 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

አውሮፕላኑ ከአሜሪካዋ ሐዋይ ሆነሉሉ ወደ ኒውዚላንድ ኦክላንድ ለማምራት 337 መንገደኞችንና 15 ሠራተኞችን አሣፍሮ ከመነሳቱ አስቀድሞ ሁሉም አማን ነበር፡፡

አውሮፕላኑ አኮብኩቦ ወደ ሰማይ ከፍታውን ሲያያዘው አንዳች ነጐድጓዳማ ድምፅ መሰማቱ ለአውሮኘላኑ አብራሪዎች፣ ለኢንጂነሩም ሆነ መላ መንገደኞቹን አስደነገጠ፡፡

አውሮፕላኑ ለ16 ደቂቃዎች ከበረረ በኋላ ወደ 23 ሺህ ጫማ ከፍታ ተጠጋ፡፡

ከዚህ ከፍታ ሲደርስ ቢዝነስ ክላስ ተብሎ በተከለለው የአውሮኘላኑ ክፍል አንዳች ድንገተኛ ንቅናቄና የፍንዳታ ድምፅ ተሰማ፡፡

በዚያ ቅፅበት የአውሮፕላኑ የእቃ መጫኛ ክፍል በር እንደ ወረቀት ተበጭቆ በረረ፡፡

የአውሮፕላኑ ቢዝነስ ክላስ ተሽነቋቆረ፣ ተቦተራረፈ፡፡ ትልቅ ቀዳዳም አበጀ፡፡

በዚያ የነበሩ ዘጠኝ ሰዎች በሽንቁሩ በተፈጠረው ከፍተኛ የአየር ግፊት ተስበው ወደ ውጭ ተምዘገዘጉ፡፡ ዕጣቸውም ሞት ሆነ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣የካቲት 20፣2009

የምዕራብ ሰሐራ ጉዳይ

በዓለማችን በአወዛጋቢ ግዛትነታቸው ከሚታወቁት መካከል ምዕራብ ሰሐራ አንዷ ነች፡፡

ለግዛቲቱ የተማላ ነፃነት የሚታገለውና የፖሊሳሪዮ ግንባር የተሰኘው የጦርና የፖለቲካ ድርጅት ግዛቲቱን ሳሐራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ በሚል ስያሜ ነፃ አገር ነች ሲል ያወጀው የዛሬ 41 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነው፡፡

የአውሮፓ አገሮች አፍሪካን እንደ ቅርጫ ለመካፈል ከ133 ዓመታት በፊት በዶለቱበት የበርሊኑ ሸንጓቸው በአፍሪካ ሰሜናዊ ምዕራብ ጫፍ የምትገኘው ምዕራብ ሰሐራ የስፔን ትሁን ተባለ፡፡

ስፔን ምዕራብ ሰሐራን ቅኝ ግዛቷ አደረገቻት፡፡

ጊዜው ደረሰና በአፍሪካ ቅኝ አገዛዝ ፍፁም እየተዳከመ ሲመጣ ስፔን ከ42 ዓመታት በፊት ምዕራብ ሰሐራን ለቅቃ ወጣች፡፡

ስፔን ለቅቃ እንደወጣች በግዛቲቱ ላይ የይገባናል ጥያቄ የሚያነሱት ሞሮኮና ሞሪታንያ በየፊናቸው ምዕራብ ሰሐራን ተቀራመቷት፡፡

ከ2 ሦስተኛው በላይ የምዕራብ ሰሐራ ክፍል በሞሮኮ ስር ገባ፡፡ የተቀረውን ሞሪታንያ ያዘችው፡፡

ሞሪታንያ በይዞታዋ ብዙ አልገፋችበትም፡፡

ለግዛቲቱ ነፃነት በተቋቋመውና የፖሊሳሪዮ ግንባር በተሰኘው የጦርና የፖለቲካ ድርጅት ግፊት በአጭር ጊዜ ለቅቃ ወጣች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers