• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣መጋቢት 18፣2009

የካናሪ ደሴቱ የአውሮፕላን አደጋ

በስፔን ካናሪ ደሴት በዓለማችን እጅግ አሰቃቂ ነው የተባለው የአውሮፕላን አደጋ ከደረሰ ዛሬ ልክ 40ኛ ዓመቱን ደፈነ፡፡

በዕለቱ በግራን ካናሪያ ኤርፖርት የመንገደኞች ማስተናገጃ ውስጥ ቦምብ ፈንድቶ 1 ሰው ገደለ፡፡

በዚህ ብቻ ሳያበቃ 2ኛው ቦምብ እንደተጠመደ የሚያስጠነቅቅ የስልክ መልዕክት መድረሱ የኤርፖርቱን ሹሞች ማስደንገጥ ማሳሰቡ አልቀረም፡፡

ግራን ካናሪያ ኤርፖርት የቦንቡ ጉዳይ እስኪጣራ ለጊዜው ተዘጋ፡፡

ወደ ካናሪ ደሴት የሚመጡ ገቢ አውሮፕላኖች ማረፊያቸውን በደሴቲቱ ወደ ሚገኘው ሌላኛው ኤርፖርት ሎስ ሮዴዮስ እንዲቀይሩ ታዘዙ፡፡

በእለቱ የክፉ እጣ ሰለባ የሆኑ የአሜሪካው የፓን አምና የኔዘርላዱ KLM አየር መንገድ ንብረት የሆኑ ቦይንግ 747 ጃምቦ ጄቶች በሎስ ሮዲዮስ ኤርፖርት በተለዋጭነት አረፉ፡፡

በግራን ካናሪያ ኤርፖርት ተጠምዷል የተባለው ቦምብ ስጋት ከተወገደ በኋላ በሎስ ሮዲዮስ ያረፉት ሁለቱ የመንገደኞች አውሮፕላኖች በየፊናቸው ወደ ግራን ካናሪያ ለመብረር ተዘጋጁ፡፡

ሁለቱ አውሮፕላኖች ለበረራ በተሰናዱበት ወቅት ጭጋጋማው የአየር ክስተት ዕይታን ማወኩ አልቀረም፡፡

ሁለቱም አብራሪዎች ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር የሬዲዮ ግንኙነት ነበራቸው፡፡

ከዕይታ መጋረድ በተጨማሪ ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎቹ ጋር የመልዕክት መለዋወጫው ሬዲዮ የሞገድ መምታታት አስከተለ፡፡

በዚያ ላይ ኤርፖርቱ በምድር ያሉ አውሮፕላኖችን መከታተያ ራዳር አልነበረውም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣መጋቢት 15፣2009

አሁን ታሪክ ለመሆን የበቃው የአንጎላው የእርስ በርስ ጦርነት

አንጐላ ከ40 ዓመታት በፊት በከፍተኛ ተጋድሎና ትንቅንቅ ከፖርቱጋል ነፃነቷን ብትቀዳጅም ለረጅም ጊዜ የነፃነቷን ትሩፋት ሳታጣጥም ቆይታለች፡፡

ለአንጐላ ነፃነት ድርሻ የነበራቸው ኤም.ፒ.ኤል.ኤ ና ዩኒታ የተሠኙት የጦርና የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ እርስ በርስ ቁርቋሶ የገቡት ከነፃነቱ ጊዜ አስቀድሞ ነበር፡፡

ከነፃነት በኋላ ኤም.ፒ.ኤል.ኤ በአንጐላ ፈላጭ ቆራጭ ዩኒታ ደግሞ አማፂ ቡድን ሆኖ ለ30 ዓመታት ገድማ ሲተጋተጉ ኖረዋል፡፡

የዩኒታ አማፂ ቡድን መሪ የነበሩት ጆናስ ሳቪምቢ የአንጐላ መንግሥት ጦር በወሰደባቸው እርምጃ ከተገደሉ በኋላ ለአገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ማብቃት ምክንያት የሆነውን ክስተት ዓለም የሰማው የዛሬ 15 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ሳቪምቢ በወጣትነት ዕድሜቸው ወደ ቻይና አቀኑ፡፡ በዚያ የቻይናን ቀይ ጦር የሸምቅ ውጊያ ስልቶች ቀስሙ፡፡

አንቱ የተሰኙ የጦር መላ አዋቂ ሆኑ፡፡ የቻይኖቹን የኮሚኒስታዊ ፍልስፍና ዝንባሌ እርግፍ አድርገው ትተው የውጊያ ስልታቸውን ብቻ ቀሰሙ፡፡

ሳቪምቢ የሶቪየቶች ተቀጥላ ነበር የሚባለውን የኤም. ፒ. አል. ኤን መንግስት ለመውጋት ሁነኛው ሰው ሆነው ስላገኗቸው ምዕራባዊያን አይዞዎት ከጐንዎ ነን እንደግፎታለን አሏቸው፡፡

እጃቸው ከገቡ ግዛቶች የሚያፍሱትን አልማዝ በኮንትሮባንድ እየቸበቸቡ የሸምቅ ውጊያ ቡድናቸውን ዩኒታን እስከ አፍንጫው አስታጠቁት፡፡ በአንጐላ መንግስት ወታደሮች ላይ ለቁጥር የበረከቱ ድሎችን ጨበጡ፡፡ በአንድ ወቅት ርዕሠ ከተማዋን ሉዋንዳን እስከመክበብ ደረሱ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣መጋቢት 11፣2009

የምፅዐት ቀን ናፋቂው እምነት

ሳሪን የተሰኘው መርዛማ ጋዝ ከአደገኛና ሕዝብ ጨራሽ ኬሚካላዊ ንጥረ ነገሮች ይመደባል፡፡

የነርቭ ሕዋሶችን በማጥቃትም ይታወቃል፡፡

በጃፓኗ ርዕሠ ከተማ ቶኪዮ የምድር ውስጥ ለውስጥ የባቡር መተላለፊያ መስመር የተለያዩ ጣቢያዎች የሳሪን ጋዝ ተረጭቶ 12 ሰዎችን የገደለው የዛሬ 22 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

የነርቭ ጋዝ ጥቃቱ መሪና ዋነኛ አቀነባባሪ ራሱን በራሱ አምላክ ያሠኘ ሾኮ አሠሃራ የተባለ ኦምሽነሪኪው ምፅአት ናፋቂ ቡድን መሪ ነው፡፡

ሾኮ አሳሃራ ከጥቃቱ ጥቂት ዓመታት ቀደም ብሎ የምፅዓት ቀን ሰባኪ መፅሐፍን ፃፈ፡፡ 
ዓለም ትቀበለዋለች ያላቸውን ፍዳዎችና መከራዎችም አተተ፡፡ ምጥ ጣሯን ተነተነ፡፡ 
ትንቢት ነው ያለውን መጥፎ መጥፎውንም መከራ ዘረዘረ፡፡

እዚህና እዚያ ይደርሳሉ ያላቸው መከራና ፍዳዎች በሦስተኛው የዓለም ጦርነት እንደሚደመደም ቀበጣጠረ፡፡

የጦርነቱ ማሳረጊያ ዓለምን የሚያጠፋት የኒኩሊየር አርማጌዲዮን ይሆናል አለ፡፡
ዓለምም ከ20 ዓመት በፊት እንደ ጐርጐሮሳዊው አቆጣጠር በ1997 እንደምትጠፋ አሟረተ፡፡

ከዚህ ምፅአት የሚተርፉት የኦምሸነሪኪው አማኞች ብቻ እንደሚሆኑም ሰበከ፡፡ 
በዚህ ኃሳብ ላይ የተንጠላጠለው የኦምሽነሪኪው ስብሰብ ከ32 ዓመታት በፊት በባለ አንድ ክፍሉ የሾኮ አሳሃራ መኖሪያ አፓርትመንት ተመሠረተ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣መጋቢት 7፣2009

የቀድሞው የኢራቅ መሪ ሳዳም ሁሴንና ሥርዓታቸው ፈፅመዋቸዋል ከሚባሉ ግፎች የሐላብጃው ፍጅት አንዱ ነው፡፡

የሐላብጃው የመርዝ ጋዝና የኬሚካል ጥቃት ከተፈፀመ ዛሬ 29ኛ ዓመቱን ደፈነ፡፡

በሰሜናዊ ኢራቅ የሚኖሩ የኩርድ ፔሽመርጋ ታጣቂዎች የሳዳም ሁሴንን አስተዳደር በመቃወም በተለያየ ጊዜ ብረት አንስተዋል፡፡

ፔሽመርጋዎች በሐላብጃ የመርዝ ጋዝና የኬሚካል የጦር መሣሪያ ጥቃት መቃረቢያም የሳዳም ሁሴንን አስተዳደር እምብዛም አደጋ ላይ የማይጥል ዓይነት አመፅ ቀስቅሰው ነበር፡፡

በአመፁ የተቆጡት ሳዳም ሁሴን የኩርድ አማፂያንን ዳግም እንዳይለምዳቸው ለመቅጣት ባሰቡ ጊዜ ሞት የተጫኑ የጦር አውሮኘላኖችን ወደ ሐላብጃ ከተማ ላኩ፡፡

ሚግና ሚራዥ ሥሪት የኢራቅ አየር ኃይል የጦር አውሮኘላኖች ከጦር ሜዳው ራቅ ብላ በምትገኘውና የኩርዶች መኖሪያ በሆነችው ሐላብጃ ከተማ ታጣቂ ከሰላማዊ ነዋሪ ባልለየ ሁኔታ የመርዝ ጋዝና አደገኛ ኬሚካሎችን የታጨቁ ቦምቦችን ያራግፉባት ያዙ፡፡

ሰው “ጋዝ” ኬሚካል እያለ መዳኛ መሸሸጊያ ፍለጋ ተሯሯጠ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣መጋቢት 6፣2009

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የተኩስ አቁም ስምምነት የተፈራረሙት የዛሬ 39 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር

በሶማሊያ የግዛት ይገባኛል መነሻ ኢትዮጵያ ከ4 አስርት ዓመታት በፊት የተፈፀመባትን ወረራ መክታ መልሳለች፡፡ወራሪው ኃይል ከኢትዮጵያ ወሰን ተጠራርጐ ከወጣ በኋላ በሁለቱ አገሮች መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት የተፈረመው የዛሬ 39 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

የአፄ ኃይል ስላሴ ስርዓት ከወደቀ በኋላ ወታደራዊ መንግስት አስተዳደርና በፍልስፍና ዘይቤ ልዩነት ከውስጥ ተቃዋሚዎቹ ጋር መተጋተግ መያዙን ሶማሊያ እንደ ምቹ አጋጣሚ ቆጠረችው፡፡በዛ በላይ የዘመኑ የኢትዮጵያ ጦር በቁጥሩ ውስን በትጥቁም በተነፃፃሪነት ደካማ ሆኖ መገኘቱን የሶማሊያ ጦር ሊያጣው የማይገባ እድል ሆኖ ታየው፡፡

በፕሬዝዳንት ሲያድ ባሬ ትመራ የነበረችው ሶማሊያ ጡንቻዋ እንደፈረጠመ  በተሠማት ጊዜ ሐምሌ 5 ቀን 1969 እስከ አፍጢሙ በታጠቀ ሠራዊቷ የኢትዮጵያን ግዛት ወረረች፡፡

90 በመቶ ያህሉን የኦጋዴን እንዲሁም አብዛኛውን የባሌና የሲዳሞ አካባቢዎች ያዘች፡፡

በጦርነቱ መጀመሪያ የሶማሊያ ጦር በታጠቀው ሶቪየት ሠራሽ ዘመናዊ ትጥቅ በመደገፍ ሰፊ የኢትዮጵያ ግዛት በእጁ ማስገባት ቻለ፡፡

የኢትዮጵያ ጦር በደካማ ትጥቅና ቁመናው በውጊያው ማለዳ በመከላከል ተወሰነ፡፡

ድሬዳዋ በጠላት እጅ እንዳትገባና ጠላት ከጂጂጋ ወደ ሐረር እንዳይዘልቅ የተደረገው የሞት የሸረት ተጋድሎ በመከላከሉ ውጊያ ሞስኮ ለሶማሊያ ስትሰጥ የቆየችውን ወታደራዊ እርዳታ ወደ ኢትዮጵያ አዞረች፡፡

ኩባ በሺህዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ከኢትዮጵያ ጐን አሠለፈች፡፡

ደቡብ የመናውያንም ለጦር እርዳታ መጡ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers