• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣መጋቢት 25፣2009

ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር

የሰበዓዊ መብት ታጋዩ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ከዛሬ 49 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን እስከዛሬም ዓለም የሚያስታውስላቸውን ‹‹ወደ ተራራው አናት ወጣሁ›› የሚለውን ንግግራቸውን አሰሙ፡፡

ከዚያች ታሪከኛ ንግግራቸው 24 ሰዓት በኋላም ተገደሉ፡፡

አፍሪካ አሜሪካውያን ለምርጫም ሆነ ለሁለንተናዊ መብትና እኩልነታቸው መስዋዕትነት የጠየቁ አታካች ትግሎችን አካሂደዋል፡፡

በቀደመው ዘመን የአፍሪካ አሜሪካውያኑን የመብት ትግል ከመሩ ተሟጋቶች መካከል ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር በአረዓያነት ይጠቀሳሉ፡፡

እኚህ የመብት ታጋይ ከመብት ተሟጋችነታቸው በተጨማሪ በመሳጭ አነቃቂና ቀስቃሽ ንግግሮቻቸውም ይታወቀሉ፡፡

አፍሪካ አሜሪካውያን በምድረ አሜሪካ ሁለንተናዊ መብትና እኩልነታቸው የሚረጋገጥበት ጊዜ እንደሚመጣ በታሰባቸው ጊዜ ሕልም አለኝ የሚለውን ተደናቂ ንግግራቸውን አደረጉ፡፡

ኪንግ በሜንፊስ ባደረጉት መሳጭና ቀስቃሽ ንግግር ሞታቸው እንደቀረበ ጠቅሰውት ነበር፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣መጋቢት 22፣2009

የዛሬ 81 ዓመት በዛሬው እለት በኢትዮጵያና በኢጣሊያ መካከል ትግራይ በሚገኘው በማይጨው ጦርነት ሆነ፡፡

ኢጣሊያ በአፍሪካ፣ በሊቢያና በሱማሊያ ከኢትዮጵያ ክፍል ኤርትራን በቅኝ ግዛትነት እÍ ካደረገች በኋላ፣ ጠቅላላ ኢትዮጵያን በሃይል ለመያዝ ጦርነት ከፈተች፡፡

ከ40 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛትነት የመያዝ አላማዋ በአድዋ ጦርነት ድል ሆና ተመልሳ ነበር፡፡ ግን አላማዋን ለማስፈፀም ቀን ጠበቀች፡፡

በምፅዋ ባህር ወደብ በኤርትራ በኩል ወደወሰን ዘመናዊ የጦር ሃይሏን አደራጀች፡፡

የወልወን ግጭት ሆን ብላ ከቀሰቀሰች በኋላ ተበዳይ ሆና ለመቅረብ ሞከረች፡፡

አከታትላም ዋናው የጦር ሃይሏን ባደራጀችባት ኤርትራ በኩል፣ ወሰን ጥሳ፣ በጥቅምት ወር መቐሌን ያዘች፡፡

ከወራሪው የኢጣሊያ ሃይል ጋር ሲወዳዳር፣ ኋላ ቀርና አነስተኛ መሣሪያ ያለው አብዛኛው፣ የኢትዮጵያ ሰራዊት፣ የክተት አዋጁን ተከትሎ፣ ጭብጦ ስንቁን ይዞ፣ ጦርና ጋሻውን አንግቦ ወደዘመቻው ተሰማራ፡፡

ኢጣሊያ፣ በሶማሊያ በኩል ባደራጀችው ዘመናዊ የጦር ሃይል፣ በምሥራቅ በዑጋዴንና በደቡብ በዶሎ በኩል፣ ጦርነት ጀመረች፡፡

ኢትዮጵያም ባላት ሃይል ለመከላከል ሰራዊቷን ወደ ሁለቱም የጦር ግንባር በእግር አጓጓዘች፡፡

ከማይጨው ጦርነት በፊት፣ በርካታ ውጊያዎች ተደርገው ብዙው ሰራዊትና አዛዞች ሞተዋል፡፡

የጎጃምና የጎንደር ጦር፣ በምዕራብ ትግራይ ተዋግቶ፣ እያሸነፈም፣ እየተሸነፈም በመጨረሻ በአይሮýላን መርዝ ተጠቅቶ ተበትኗል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣መጋቢት 21፣2009

ሩሲያ ለአሜሪካ በ7.2 ሚሊየን ዶላር የሸጠቻት አላስካ አሁን ለአሜሪካ በዓመት ከ40 ቢሊየን ዶላር ታሳፍሳለች…

አላስካ ከአሜሪካ ግዛቶች አንዷና እጅግ ሰፊዋ ነች፡፡

አሜሪካ አላስካን ከሩሲያ በ7 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር የገዛቻት የዛሬ 150 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

አላስካ እንደ ኤስኪሞ ያሉ ነባር ማህበረሰቦች መኖሪያ ብትሆንም በ18ኛው ክፍለ ዘመን በሩሲያ ንጉሳዊ ስርዓት ስር አዳሪ ነበረች፡፡

አላስካ የአሜሪካ 2ኛዋ ሰፊ ግዛት ከሆነችው ቴክሳስ ከሁለት እጥፍ በላይ ነች፡፡

ቴክሳስ ካሊፎርኒያና ሞንታና ቢጣመሩ እንኳ በስፋት አላስካን አያህሏትም፡፡

22 የአሜሪካ ትናንሽ ግዛቶችም በአንድ ላይ ቢጠቃለሉ እንኳ አላስካ ትበልጣቸዋለች፡፡

በተፈጥሮ ጋዝና በነዳጅ ዘይት የበለፀገች ነች፡፡ የአሣ ሐብቷም ተዝቆ አያልቅም፡፡ ከ3 ሚሊዮን በላይ ሐይቆችን ታድላለች፡፡

ሩሲያ አላስካን ለአሜሪካ በሸጠችበት ወቅት ከዛሬው ሐብቷና ጠቀሜታዋ ይልቅ የዚያን ጊዜ ዱርነቷ ብቻ ነበር የታያት፡፡

የዘመኑ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዊሊያም ሲዋርድ ሩሲያውያን አላስካ በአስተዳደራቸው ስር ብትሆንም ነገሬ እንዳላሏት ተገነዘቡ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣መጋቢት 20፣2009

የናዚ ጀርመን 4ኛው አርሚ…

ባለ ብዙ ክፍለ ጦሮችና ብረት ለበስ ኃይሎች ስብስብ የሆነው የ2ኛው የዓለም ጦርነት ዘመኑ የጀርመን 4ኛው አርሚ በታላላቅ ውጊያዎች በመካፈል ዝናው የገዘፈ ነበር፡፡

ወደ ጦርነቱ ማብቂያ ታሪክ ተቀየረ፡፡

የጀርመን 4ኛው አርሚ በሶቪየት ኃይሎች ዳግም እንዳይነሳ ሆኖ የተደመሠሠው የዛሬ 72 ዓመት በዛሬዋ እለት ነው፡፡

ጀርመን ምስራቃዊቱን ጐረቤቷን ፖላንድን በመውረር በ20 ቀናት ውጊያ ሙሉ በሙሉ በእÍ አስገባቻት፡፡

ይሄው የጦር ክፍል የጀርመን ኃይሎች ፖላንድን ሙሉ ለሙሉ በእጃቸው ያስገቧት በ20 ቀናት ውጊያ ነው፡፡

ዋነኛው የዘመቻው ኃይል ገናናው  የጀርመን 4ኛው አርሚ ነበር፡፡

ጀርመን ፈረንሳይን ስትወርም ከሌሎች የአገሪቱ የጦር ክፍሎች ጋር በመቀናጀት ቁልፍ ሚና ነበረው፡፡ 

ጀርመን በዘመቻ ባርባሮሳ በሶቪየት ህብረት ላይ ወረራ ስትፈፅም የአንበሳው ድርሻ የዚሁ የጦር ክፍል ነበር፡፡

በጦርነቱ መጀመሪያ ገናናው 4ኛው አርሚ በሶቪየቶች ላይ ታላላቅ የሚባሉ ድሎችን ተቀዳጀ፡፡ በበርካታ አውደ ውጊያዎች በለስ እየቀናው መጣ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣መጋቢት 19፣2009

ጄሲ ኦዌንስ

በመልካም ምግባራቸው፣ ባከናወኑት ታላቅ ተግባር፣ በጀግንነት ውሏቸው፣ ታላቅ አሻራን ያኖሩ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም ስማቸው ከመቃብር በላይ ነው፤ ይባልላቸዋል፡፡

ጄምስ ክሌቭላንድ ወይም ጄሲ ኦዌንስ፣ የተባለው አፍሪካ አሜሪካዊ አትሌት፣ ስማቸው ከመቃብር በላይ፣ ከዋለው ሰዎች አንዱ ነው፡፡

የቀድሞው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት፤ ጆርጅ ቡሽ ትልቁ፤ ለጄሲ ኦዌንስ ለሲቪሎች ከሚሰጡት እጅግ የላቀውን የኮንግረሱን የወርቅ ሜዳልያ ያበረከቱለት፤ አትሌቱ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ ከ10 ዓመት በኋላ የዛሬ 27 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

ኦዌንስ፣ የአጭር ርቀትና የአግድመት ዝላይ፣ ባለተሠጥኦ ነበር፡፡

በተለይ፣ ከ81 ዓመት በፊት፣ የተካሄደው፣ የበርሊን ኦሊምፒክ፣ ድንቅ ችሎታውን ያስመሠከረበት የስፖርት አውድማ ሆነ፡፡

በዘመኑ፣ የጀርመን ናዚዎች መሪ፣ አዶልፍ ሂትለርና ተከታዮቹ፣ በከፍተኛ ዕብሪትና ትምክህት ውስጥ ነበሩ፡፡

በዚህም ቀቢፀ ተስፋ በኦሎምፒኩ ፉክክር የጀርመን ተወዳዳሪዎች ሜዳሊያዎቹን እንደሚያግበሰብሱትና ለዓለም ማንነታቸውን የሚያሳዩበት መድረክ እንደሚሆን ታሰባቸው፡፡

ዓለምን በእጄ አስገባለሁ፤ ብሎ ክፉ ኃሳብ ያደረበት ሂትለር ኦሎምፒኩን ለፕሮፓጋንዳው ማራመጃነት፣ እንደ መልካም አጋጣሚ ቆጠረው፡፡

ናዚዎቹ፣ የሁሉም የበላይና የምርጥ የአርያን ዝርያዎች ነን፤ የሚለውን መርዘኛ ኃሳባቸውን አሠራጩ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers