• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 29፣2009

የእስራኤልና ፍልስጤም ነገር

ከ69 ዓመታት በፊት የፍልስጤም ምድር በእሥራኤላዊያንና በፍልስጤም አረቦች ይዞታነት ከተከፋፈለ አንስቶ አካባቢው ግጭትና ውጥረት ተለይቶት አያውቅም፡፡

ከዚያን ጊዜ አነስቶ ታላላቅ ጦርነቶች አስተናግዷል፡፡

ከጦርነቶቹም መካከል ከ49 ዓመታት በፊት የተካሄደውና በታሪክ የስድስቱ ቀን ጦርነት የተሰኘው ውጊያ አንዱ ነው፡፡

በጦርነቱ እሥራኤል አስደናቂ የተባሉ ድሎችን ተቀደጅታለች፡፡

በጊዘው በፍልስጤማውያን ይዞታነት የተከለሉትን ምስራቅ እየሩሳሌምን፣ የጋዝ ሰርጥንና ዌስት ባንክን ለመያዝ በቅታለች፡፡

ከሶሪያም የጐላን ኮረብታን ነጥቃለች፡፡ ከዚያ ወዲህ ፍልስጤማውየን እሥራኤልን በተደራጀና ባልተደራጀ ሁኔታ ሲፋለሟት፣ ሲተናነቋትና ሲገዳደሯት ቆይተዋል፡፡

ከትግል መንገዶቻቸው አንዱ የሆነውን የሲቪል እምቢታና አመፅን ያጣመረውንና የመጀመሪያውን ኢንቲፋዳ የተሰኘ ትግላቸውን የቀሰቀሱት የዛሬ 29 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ፍልስጤማውያን በተለያዩ የአስተዳደር ዘርፎች ለእሥራኤል ግብር አንከፍልም አሉ፡፡

እዚህም እዚያም በሥፋት ሥራ ማቆምን ተያያዙት፡፡ የእሥራኤልን ምርቶችና ሸቀጦችን ላለመግዛትም አደሙ፡፡ እነዚህ የኢንቲፋዳው ሰላማዊ ጐኖች ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 28፣2009

የስፒታኩ ርዕደ መሬት

አርመኒያ የምትገኝበት የዓለማችን ክፍል በከፍተኛ የርዕደ መሬት አደጋ ተጋላጭነታቸው ከሚታወቁት አካባቢዎች አንዱ ነው፡፡

አገሪቱን አስከ 50 ሺህ የሚገመቱ ዜጐቿን የጨረሰባትና መጠነ ሰፊ ውድመት ያደረሰባት ርዕደ መሬት ያጋጠማት የዛሬ 28 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

አርመኒያ የምትገኝበት ሥፍራ ከአውሮፓው አልፕስ እስከ እስያው ሂማላያ ተራሮች የተዘረጋው የእሳተ ገሞራ ሰንሰለት የተዘረጋባት መሆኑ ለመሬት ነውጥ ከተጋለጡት አገሮች አንዷ ያደርጋታል፡፡

አገሪቱ በታላቁ ርዕደ መሬት ከመመታቷ ዓመት አስቀድሞ ካውካሰስ የተሰኘው አካባቢ በፖለቲካዊ ቀውስ ይናጥ ያዘ፡፡

በዚያ ጊዜ የሶቪየት ኅብረት አካል የነበሩት አርመኒያና አዘርቫጃን ናጐርና ካራባክ በተሰኘችዋ ግዛት ይገባኛል ጠባቸው ከጫፍ ደረሰ፡፡

ለገላጋይ አስቸገሩ፡፡

በቀጠናው የጦርነት ደመና አንዣበበ፡፡

አርመኒያ በዚህ ውጥረትና ፍጥጫ ውስጥ እያለች እንደ ጀበና የተጣደችበት እሳተ ገሞራም ሆድ ባሰው፡፡

ተራራማዋን አገር በርዕደ መሬት መለኪያ ሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 6 የተመዘገበ ነውጥ ለ20 ሰኮንዶች እንደ ኳስ አጐናት፡፡ አንቀረቀባት፡፡

ርዕደ መሬቱ የንቅናቄ ማዕከሉን ስፒታክ የተሰኘችውን ከተማ በማድረጉ በታሪክም የስፒታኩ ነውጥ የሚል ስያሜ ተሰጠው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 27፣2009

ፊንላንድ

ፊንላንድ በሩሲያ ቅኝ አገርነት ተይዛ የቄሳራዊቷን አገር ፈቃድ እየሞላችና እየፈፀመች ከአንድ ምዕተ-ዓመት በላይ ኖራለች፡፡

አገሪቱ እምብዛም ባላሰበችውና ባልጠበቀችው ሁኔታ ነፃነቷን የተጐናፀፈችው የዛሬ 99 ዓመት በዛሬዋ እለት ነው፡፡

በ18ኛው ክፍል ዘመን በፊንላንድ ጉዳይ የሩሲያ እጆች  ረጃጅሞች ነበሩ፡፡

በ19ኛው ክፍለ ዘመንም በፊንላንድ የሩሲያ ፍላጐት በጣሙን እየጨመረ መጣ፡፡

በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ሩሲያና ተመሳሳይ ፍላጐት ያደረባት ሲዊድን ፊንላንድን ለመቀራመት ታላቅ ጦርነት አደረጉ፡፡

በጦርነቱ በቀዳማዊ አሌክሳንደር የተመሩት ሩሲያውያን አሸነፉ፡፡

የዘመናዊዋ ፊንላንድ አብዛኛው ክፍል በቄሳራዊት ሩሲያ አገዛዝ ስር ወደቀ፡፡

በፊንላንድ ሿሚዋም ሻሪዋም ሩሲያ ሆነች፡፡

አድራጊ ፈጣሪዎቹ የሩሲያው ዛር ምስለኔዎች ሆኑ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 26፣2009

5 ሺ ሰዎችን የቀጠፈው “ታላቁ ጭጋግ”

ያኔም የነበረ ቢሆንም ፤ የአየር ብክለት ነገር የአገሮችም የዓለማችንም የዕለት ተለት ስጋትና አጀንዳ ሳይሆን የእንግሊዟ ርዕሰ ከተማ ለንደን ችግሩን ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት አንስቶ አሳምራ ታውቃለች፡፡

በአየር ብክለት ምክንያት በ5 ቀናት ውስጥ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ያለቁበት ታላቁ ጭጋግ የጀመራት የዛሬ 64 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነው፡፡

በጊዜው ለንደን ለኢንዱስትሪዎቿ መዘወሪያ በአብዛኛው ድንጋይ ከሰልን ማንደድ አብዩ የኃይል ምንጯ ነበር፡፡

የባቡሮቿም ቀለብ፣ ከክረምቱ ከፍተኛ ቅዝቃዜ ለማምለጥ በዚሁ የኃይል ምንጭ ላይ ተማምና ኖራለች፡፡

ታላቁ ጭጋግ ከመከሰቱ በፊት በለንደን ቅዝቃዜው በረታ፡፡

ለንደንም ቅዝቃዜውን ለመከላከል የምታነድ የምታጫጭሰውን የድንጋይ ከሰል አበዛች፡፡

በተለይም ከ2ኛው የዓለም ጦርነት በመለስ በነበሩት የችግር ዓመታት ለኢንዱስትሪዎች ማንቀሳቀሻም ሆነ ለቅዝቃዜ መከላከያ የሚማገድ የድንጋይ ከሰል ጥራቱ ዝቅተኛ ነበር፡፡

ጭሱ እንደጉድ ይትጐለጎላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 22፣2009

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ኃያላኑ አንዳቸው አጥቂ ሌሎቹ ተከላካይ ሆነው እየተቧደኑ ጐራ ፈጠሩ፡፡

የዘመኑ የጃፓን ንጉሰ ነገሥት ሂሩሂቶ አሜሪካንን ለመውጋት የመጨረሻውን ማረጋገጫ የሰጡት የዛሬ 75 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

በአዶልፍ ሂትለር ይመሩ የነበሩት የጀርመን ናዚዎች ዓለምን አንበርክከውና በተፅዕኗቸው ሥር እንደፈቃዳቸው አዳሪ ለማድረግ ባሰቡ ጊዜ ተባባሪዎች አላጡም፡፡

ከአውሮፓ የጣሊያን ፋሽስቶች አጋሮቻቸው ሆኑ፡፡

ከወደ ሩቅ ምሥራቅም የጃፓን ወራሪዎች በዓላማቸው ተባባሪነት ተሰለፉ፡፡ ይሄ ሦስትዮሽ የጥፋት ጥምረት አክሲስ ተሰኘ፡፡

ከ75 ዓመታት በፊት የጃፓን ከፍተኛ መኮንኖች በጦርነቱ ይዞታ ላይ ሲመክሩ፣ ሲያወጡና ሲያወርዱ ሰነበቱ፡፡ የጦር መኮንኖቹ በሸንጓቸው አሜሪካን ለመውጋት ቁርጥ ኃሳብ አደረጉ፡፡

ንጉሰ ነገሥት ሂሩሂቶም ይሁን እንዳላችሁት ሲሉ ለአሜሪካ መወጋት ፈቃደኝነታቸውን አረጋገጡ፡፡ ቡራኬያቸውን ሰጡ፡፡ ጃፓን አሜሪካን ለመውጋት ያቀደችው የደቡብ ምሥራቅ እስያን ክፍል ለመያዝ የነበራትን ዕቅድ እንዳታሰናክልባት አስባ ነው፡፡

ንጉሰ ነገሥቱ ለዕቅዱ ቡራኬያቸውን በሰጡ በሳምንቱ ጃፓን በሐዋይ የሚገኘውን የአሜሪካ የፐርል ሐርበር የባሕር ኃይል መደብ እንዳልነበረ አድርጋ ምንቅርቅሩን አወጣችው፡፡ ከ2 ሺህ 400 በላይ የአሜሪካ ባሕር ሐይል ወታደሮችና መኮንኖች ተሰዉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)