• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ግንቦት 14፣2009

የአሜሪካ ባሕር ሰርጓጅ መርከብ ዩ.ኤስ.ኤስ ስኮርፒዮ

ስኮርፒዮን ቃኚም ሰላይም ተዋጊም ነበረች፡፡

በሙሉ መጠሪያ ስሟ ዩ.ኤስ.ኤስ ስኮርፒዮን የተሠኘችዋ የአሜሪካ ባሕር ሰርጓጅ መርከብ  10ኛ አመት ልትደፍን አንድ አመት ሲቀራት ጥገና ተከናወነላት፡፡

የጦር መሳሪያ ስርዓቷ ሁሉም አካሎቿ በወግ በውጉ ስለመሆናቸው ፍተሻ ተደረገላቸው፡፡ ልምምድም ተካሄደባት፡፡

ከዚያም ለተልዕኮ ወጣች፡፡ ማዳረስ ያለባትን አዳረሰች፡፡ ማካለል የነበረባትን ቦታዎች አካለለች፡፡

መርከቧ ከወራት ተልዕኮ በኋላ ወደ ማረፊያዋ እየተመለሰች ሳለ በአትላንቲክ ውቅያኖስ በሳራጋሶ ባሕር ምሠራቃዊ ዳርቻ የሰጠመችው የዛሬ 49 ዓመት በዛሬው እለት ነበር፡፡

ከ99 ባሕረኞቿ ጋር መኖሪያዋን ከጥልቁ የውቅያኖስ ስርቻ አደረገች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ግንቦት 7፣2009

የአረቦችና እስራኤል ነገር

እስራኤልና አረቦች አነስተኛዎቹን ሣይጨምር ከአንዴም አምስት ጊዜ ታላላቅ ጦርነቶችን አድርገዋል፡፡

ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች ቀዳሚውን ታላቅ ጦርነት ማካሄድ የጀመሩት የዛሬ 69 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

የታላቁ ጦርነት መጀመሪያ የዛሬ 69 ዓመት የዛሬዋ ዕለት ብትሆንም በፍልስጤም ምድር እሥራኤልና ፍልስጤማውያን ቁርቋሷቸው የጀመረው ከዚህ ጦርነት በፊት ነው፡፡

ከ70 ዓመታት በፊት ብሪታንያ የፍልስጤም ግዛት ሞግዚታዊ አስተዳዳሪነቷን ስትተወው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፍልስጤም በአይሁዳውንና በፍልስጤም አረቦች ይዞታነት እንድትከፈል ወሰነ፡፡

ከ69 ዓመታት በፊት የእስራኤል ነፃ አገርነት መታወጁን በፀጋ አልተቀበሉትም፡፡

የእስራኤል ነፃ አገርነት በታወጀ ማግስት ግብፅ ሶሪያና ዮርዳኖስ በእስራኤል ላይ ጦርነት ከፈቱባት፡፡

የኢራቅ ወታደሮችም በግብፅ፣ ሶሪያና ዮርዳኖስ ደጋፊነት በውጊያው ተሰለፉ፡፡

ይሄ ከሆነ ዛሬ 69 ዓመት ሆነው፡፡

ጦርነቱ ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ ለ10 ወራት ተካሄደ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ሚያዝያ 25፣2009

እስከ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ያሉ የጃፓን መንግስታት ደርሶ ጦረኝነት የሚያጠቃቸውና ወታደራዊነት የሚያመዝንባቸው ነበሩ፡፡

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከጀርመን ናዚና ከጣሊያን ፋሺዝም ጋር አብረው ተሰላፉ፡፡ ኢስያን ለማስገበር ተነሱ፡፡

ታዲያ የኋላ ኃላ እንደ ጦር አጋሮቻቸው የነሱም መጨረሻ አላማረም፡፡

ጥቅም ላይ መዋሉ እምብዛም አሳማኝነት ቢጐደለውም አሜሪካ ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ በተባሉ ከተሞቿ ላይ እስካሁን  አሻራቸው አልለቀቀም የተባላላቸውን የአቶሚክ ቦንቦች ብትጥልባቸው ሰበብ ምክንያቷ ጦርነኝነታቸው ነበር፡፡

ኃላም እንደ ሀገር ለአሸናፊዎቻቸው እጅ መስጠትን አስከተለባቸው፡፡

ከዛን ጊዜ ወዲህ ጃፓን በፍፁም ሰላማዊ አገርነትዋ ነው የምትታወቀው፡፡

ለዚህ ሰላማዊነቷ ዋስትና የሰጠውና ፈር የቀደደው አዲሱ ሕገ-መንግስቷ ስራ ላይ መዋል የጀመረው የዛሬ 70 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

ሕገ መንግስቱ ጦረኝነት እርም ይሁንብን አለ፡፡ አነወረው፡፡

ከዚያ በፊት የጃፓኑ ንጉስ የፍፁም አዛዥ ናዛዥነት የአድራጊ ፈጣሪነት ስልጣን ነበራቸው፡፡ 

ሕገ-መንግስቱ ከመጣ በኋላ እርሶዎ የሀገር ተምሳሌት በመሆን ስልጣንዎ ይገደባል ተባሉ፡፡ እሳቸውም እሺ ብለው ተቀበሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ሚያዝያ 20፣2009

በኢትዮጵያ ላይ የጣሊያን ፋሽስቶች ወረራ በከፈቱበት ወቅት መሪያቸው የዘመኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒቶ ሙሶሊኒ ነበር፡፡

ነገሩ ሳያልቅ አያምር ሆኖበት ሙሶሊኒ ሽንፈት በሸንፈት ላይ ተደራርቦበት ከነፍቅረኛው ተዋርዶ የተገደለው የዛሬ 72 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

ሙሶሊኒ ወደ ፖለቲካው የተሳበው ገና በለጋ የወጣትነት ዘመኑ ነበር፡፡

ከመነሻው ወደ ሠራተኛው መደብ ባዘነበለ ፖለቲካ አቀንቃኝነት የጣሊያን ሶሻሊስት የፖለቲካ ማህበር አባል ሆነ፡፡

በነበረው የዳበረ የሥነ-ፅሁፍ ተሰጥኦና ዝንባሌ የፖለቲካ ማህበሩ ልሳን አዘጋጅ እስከመሆንም ደረሰ፡፡

በዘመኑ የ1ኛው የዓለም ጦርነት የሚካሄድበት ነበር፡፡

ሞሶሊኒ በመጀመሪያ ጦርነት አውጋዥ ፅሁፎችን ያበረክት ያዘ፡፡

ግን ብዙ አልገፋበትም፡፡ የመጀመሪያ አቋሙን ቀይሮ ጦርነት አቀንቃኝ ሆነ፡፡

በዚህን ጊዜ ሶሻሊስቶቹ ከእምነትና ከኃሳባችን አፈንግጠሃልና አታስፈልገንም ብለው ከፖለቲካ ማህበራቸው አባረሩት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ታሪክን የኋሊት፣ሚያዝያ 18፣2009

ሩዝቬልትና ፖልዮ…

በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የነበሩት ፍራንክሊን ዴላኖ ሩዝቬልት ጥሩ ሰምና ዝና ከነበራቸው የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች አንዱ ነበሩ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከአጋሮቻቸው ኃያላን የአውሮፓ መሪዎች ጋር ሆነው የድል መምቻውን አዘጋጁ፡፡ በጋራ መክረውና ዘክረው ጦርነቱ በኅብረቱ ኃይሎች አሸናፊነት እንዲደመደም ያስቻሉ ናቸው፡፡

ፕሬዝዳንቱን ምንም እንኳ ዓለም አቀፍ ጀግና ሆነው ስማቸው ከአጥናፍ አጥናፍ ቢናኝም ተዋግተው ያላሸነፉት እንደልባቸው እንዳይነቀሳቀሱና እንዳይላወሱ እግራቸውን አሰሮ ያሰቀመጣቸው ጠላት ነበራቸው፡፡

ይህ ጠላታቸው ፖሊዮ የተባለው በሽታ ነው፡፡

የፖሊዮ በሽታ ተጠቂ የነበሩት እኚሁ ፕሬዝዳንት ጠላታቸው ፖሊዮ ለማጥፋት ለሚደረግ ጥረት የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ ድርጅት በማቋቋም ሰማቸው በቀዳሚነት ይነሳል፡፡
አሜሪካዊው የሕክምና ባለሙያ ጆናስ ሳልክ በጥረቱ የደረሰበት የመጀመሪያው የልጅነት ልምሻ /ፖሊዮ/ መከላከያ ክትባት ሙከራ በቬርጂኒያ ሻርመን 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጀመረው የዛሬ 63 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

ካናዳና ፊላንድም የክትባት ፍተሻው የተካሄደባቸው ናቸው፡፡

በዓመቱ ገደማ ፍተሻው ውጤታማ እንደነበር ተመራማሪዎቹ አረጋገጡ፡፡ ይህም ለዓለም የምሥራች ሆነ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers