• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት/ ከዛሬ 131 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን አፄ ዮሐንስ በመተማው ጦርነት አረፉ

የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት አፄ ዮሐንስ 4ኛ በወረራ መተማንና አልፎም እስከ ሳር ውሃ ተቆጣጥሮ የነበረውን የሱዳን ሰራዊት ለመዋጋት ወደ መተማ ዘመቱ፡፡አፄ ዮሐንስ ወደ መተማ ሰራዊታቸውን አስከትለው የሄዱት፣ ሰሃጢ ላይ ከጣሊያኖች ጋር የነበራቸውን ፍጥጫ ትተው ነው፡፡ሰሃጢ ላይ፣ ጣሊያኖችን ከምፅዋ ምድር ለማስወጣት ዘምተው ሳለ ድርቡሾች (የሱዳን ጦር) ወሰን አልፎ መያዙን ሰሙ፡፡ወረራውን እንደሰሙ በንጉስ ተክለ ሃይማኖት የሚመራው የጐጃም ጦር የሱዳንን ወታደሮች እርምጃ እንዲቆጣጠር አዘዙ፡፡

የጐጃም ጦር፣ ሳር ውሃ በተባለው አካባቢ ከሱዳኖችጋር ፅኑ ውጊያ ቢያደርግም አልቀናውም፡፡ንጉስ ተክለ ሃይማኖት፤ ጥቂት ራሳቸውን ሆነው ሲያመልጡ፣ አያሌ ሰራዊት ለሞትና ለምርኮ ተዳረገ፡፡በኢትዮጵያኖቹ መማረክና ሞት እጅግ ያዘኑት አፄ ዮሐንስ የሰሃጢውን ዘመቻቸውን ትተው ወደ መተማ አቀኑ፡፡አብረዋቸውም ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና መቶ ሺህ የሚደርስ ሰራዊታቸው ተከትሏቸዋል፡፡

በዛኪ ቱማል የሚመራው የሱዳን ወራሪ ጦር በመተማ ላይ ጠንካራ ምሽግ ሰርቶ ውጭውኑም በሹል እንጨትና በድንጋይ አጥሮ 60 ሺህ ይደርሳል የተባለውን ሠራዊቱን አዘጋጅቶ ተሰለፈ፡፡መጋቢት 1 ቀን ጠዋት ጦርነቱ ተጀመረ፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት በጀግንነት እየተዋጋ የመጀመሪያውን ምሽግ ጥሶ ገባበት፡፡በሳር ውሃው ጦርነት የሞቱትን ዜጐቻቸውን ሲያዩ ቁጭት የገባቸው አፄ ዮሐንስ ራሳቸው እንደ አንድ ወታደር ሆነው በጦር ግንባር ገብተው ተዋጉ፡፡

በጦርነቱም የኢትዮጵያ ሠራዊት ድል ለማድረግ በተቃረበበትና የሱዳን ሠራዊት ከምሽጉ ወጥቶ ለመሸሽ በተዘጋጀበት ወቅት አፄ ዮሐንስ እጃቸው ላይ ቆሰሉ፡፡ ቢሆንም በጦርነቱ መካከል አልወጡም፡፡እንደገና በግራ እጃቸው አልፋ ወደ ደረታቸው የዘለቀች ጥይት መታቻቸው፡፡ አጃቢዎቻቸው ወደ ድንኳናቸው ወሰዷቸው፡፡የአፄ ዮሐንስ መቁሰል ሲሰማ በኢትዮጵያኖች ዘንድ ድንጋጤ ተፈጠረ፡፡

የያዙትን ትተው ወደ ኋላ መመለስ ጀመሩ፡፡ በዚህ የተበረታታው ዛኪ ቱማል ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋገረ፡፡የንጉሰ ነገስቱ መቁሰል መዘበራረቅ የፈጠረበት የኢትዮጵያ ሠራዊትም ወደ ኋላው አፈገፈገ፡፡አፄ ዮሐንስ በመቁሰላቸው ምክንያት በማግስቱ መጋቢት 2፣ 1881 ዓ.ም አረፉ፡፡የኢትዮጵያኖቹን መሸሽ ያየው የሱዳን ሰራዊት እግር በእግር እየተከታተለ ማጥቃቱን ቀጠለ፡፡

የአፄ ዮሐንስን አስክሬን ድንኳንም ከበበው፡፡ ታላላቅ የጦር መኮንኖቻቸውና በርካታ ታማኝ ሰራዊታቸውም የንጉሳችንን አስክሬን አናስማርክም፤ እያሉ ፅኑ ውጊያ አደረጉ፡፡ ብዙዎችም በአስክሬናቸው ዙሪያ ረገፉ፡፡በመጨረሻ የደርቡሽ ጦር ድል አድርጐ፣ የአፄ ዮሐንስን አስክሬን ማረከ፡፡ አንገታቸውንም ቆርጦ ካርቱም ገበያ ላይ አዞሩት፡፡

የአፄ ዮሐንስ ሰራዊት የሞተው ሞቶ የተማረከው ተማርኮ የቀረው ወደ ደጋው አፈገፈገ፡፡ምንም እንኳ አፄ ዮሐንስ ሞተው ሰራዊቶቻቸው ተበታትኖ ደርቡሾች ጊዚያዊ ድል ቢያገኙም የኢትዮጵያን መሬት ይዘው ለመቆየት አልቻሉም፡፡
አፄ ዮሐንስ አንገታቸውን የሰጡላት ኢትዮጵያም በነፃነት እስከ አሁን ኖራለች፡፡

እሸቴ አሰፋ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት ጥቅምት 30፣2010

ለ28 ዓመታት ጀርመንን ለሁለት ከፍሎ የነበረው የጀርመን ግምብ ሲፈርስ

የበርሊን ግምብ በፍልስፍናና በአስተዳደር ዘይቤ የአንድ አገር ሰዎችን ለሁለት በመክፈል የቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን የጥላቻ ግድግዳ ተደርጐ ይቆጠራል፡፡

ለዓመታት ጀመርኖችን ከፋፍሎ የቆየው ግንብ ክፍት ሆኖ ምሥራቅ ጀርመናውያን ወደ ምዕራቡ እንዲሻገሩ የተፈቀደላቸው የዛሬ 28 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

የጀርመን ናዚዎች ዓለምን በመዳፋችን ውስጥ እናውላለን ብለው ከ78 ዓመታት በፊት ጦርነት አቀጣጠሉ፡፡ የኋላ ኋላ በተነሱበት ፍጥነት መቀጠል ተሳናቸው፡፡

በሌሎች ላይ የለኮሱት እሳት ራሳቸውን ማቃጠሉን ያዘው፡፡

የህብረቱ ኃይሎች ከየአቅጣጫው መጡባቸው፡፡ የአንግሎ አሜሪካ ኃይል ከምዕራብ፤ የሩሲያ ሠራዊት ከምስራቅ አቅጣጫ መጡባቸው፡፡ መፈናፈኛ አጡ፡፡

አገራቸው በህብረቱ ኃይሎች ተፅዕኖ ስር ወደቀች፡፡

ከጦርነቱ በኋላ ምዕራባዊ ክፍሏ በአሜሪካ፣ እንግሊዝና ብሪታንያ አስተዳደር ስር ሆነ፡፡

የምስራቃዊው ክፍል ደግሞ በቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት ተፅዕኖ ሥር ወደቀ፡፡ 

ምዕራባዊው ክፍል የጀርመን ፌዴራል ሪፐብሊክ ተሠኝቶ ራሱን ቻለ፡፡ የምስራቁም ግዛት ምስራቅ በርሊንን ርዕሠ ከተማው በማድረግ በሶቪየት ተቀጥላነት የጀርመን ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ተባለ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ታሪክን የኋሊት መስከረም 29፣2010

ኤርኔስቶ ቼጉቬራ - ዓለማቀፉ ታጋይ

አርጀንቲናዊው ኤርኔስቶ ቼጉቬራ በትምህርቱና በሙያውም ሐኪም ቢሆንም ዓለም በብዙ የሚያወቅው በግራ ክንፈኛ ተዋጊነቱ ነው፡፡ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ በዓለም ዙሪያ በነፃነት አላሚ ወጣቶች ልቦና ውስጥ እንዳደረ ቦሊቪያ ውስጥ በዓላማ ተፃራሪዎቹ እጅ የገባውና የተማረከው የዛሬ 50 ዓመት በዛሬዋ እለት ነው፡፡ቼ ተኮትኩቶ ያደገበት የቤተሰብ መሠረቱ ሆኖ በወጣትነቱ ሲበዛ ለድሆች፣ ለተገፉና ለተጨቆኑ ተቆርቋሪ ሆነ፡፡

በወጣትነት ዘመኑ በብዙ የላቲን አሜሪካ አገሮች ተዘዋውሯል፡፡ይህም በዘመኑ በየአገሩ መንግስታት ጭቆና የሚፈፀምባቸውን፣ የተገፉትን፣ ፍትህ የራቃቸውንና የተበደሉትን በቅርበት ለማየት እድል ፈጥሮለታል፡፡ቼ ይሄን አይቶ ሁኔታው መቀየር እንዳለበት የጭቆናው ቀንበር መሠባበር እንዳለበት ማሰብ መብስልሰሉ አልቀረም፡፡

በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዳለ በሜክሲኮ በሙያው እየሠራና በዩኒቨርስቲ እያስተማረ በነበረበት ወቅት ከኩባውያኑ ወንድማማቾች ራውልና ፊደል ካስትሮ ጋር ተዋወቀ፡፡

እነሱም በአገራቸው የተንሠራፋውን ጭቆና መታገያ መንገዶችን መላ ለማለት በሜክሲኮ እንደሚገኙ ነገሩት፡፡

እውቂያቸው ወደ ዓላማ አጋርነት ተሸጋገረ፡፡

ወደ ኩባ ለመዝመት የወታደራዊና የሸምቅ ውጊያ ልምምድ ውስጥ ገቡ፡፡

በልምምዱ ቼ ከሁሉም ብልጫ ያለውና የላቀ ነበር ይባልለታል፡፡

ጊዜው ደረሰና 82 ሆነው በግራንማ ጀልባ ለታላቁ ተልዕኮ ወደ ኩባ ቀዘፉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ታሪክን የኋሊት መስከረም 23፣2010

የጀርመን ነገር

በ19ኛው ክፍለ ዘመን 2ኛ አጋማሽ ኦቶ ቮን ቢስማርክ የተበጣጠቁ ግዛቶችን በመሠብሰብ የተዋሐደችና የጠነከረች ጀርመንን ፈጠረ፡፡

ጀርመን ከ2ኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ከደረሰባት የምስራቅ ምዕራብ መከፋፈል ተገላግላ መልሳ የተዋሐደችው ደግሞ ዛሬ 27 በዛሬዋ እለት ነው፡፡

በ20ኛው ክፍል ዘመን የመጀመሪያ ሩብ ወደ ስልጣን የመጣው ኦዶልፍ ሂትለርና የናዚዎች የፖለቲካ ማህበሩ ዓለምን በጦር ኃይል የማንበርከክና የማስገበር ክፉ ኃሳብ አደረባቸው፡፡ 
የኋላ ኋላ የጫሩት የጦርነት እሳት እነሱንም አቃጠለቸው፡፡

መራራ ሸንፈትን ተጐነጩ፡፡ የእነሱ መዘዝ ለአገራቸውም ተረፋት፡፡

ጀርመን በአሸናፊዎቹ የህብረቱ ኃይሎች ተፅዕኖ ስር ወደቀች፡፡ አሸናፊዎቹ በምዕራብና በምስራቅ ሸነሽኗት፡፡ አንዷ አገር ለሁለት ተከፈለች፡፡

በአሜሪካ፣ ብሪታንያና ፈረንሳይ የተፅዕኖ ክልልነት የቆየው የአገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል ምዕራብ ጀርመን ወይም የጀርመን ፌዴራላዊ ሪፖብሊክ ተባለ፡፡

በሶቪየቶች ይዞታነት የቆየው ምስራቃዊ ክፍል ምስራቅ ጀርመን ወይም የጀርመን ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ተሰኘ፡፡ በሞስኮ ሳምባም ሲተነፍስ ቆየ፡፡

ከ32 ዓመታት በፊት ሚሐየል ጐርባቾቭ በቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት መሪነት ወደ ክሬምሊን መምጣታቸው ለቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃት መንገድ ጠረገ፡፡

“ግላስኖስት” ግልፅነት፤ “ፔሬስትሮይካ” ተሐድሶ አሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ታሪክን የኋሊት መስከረም 10፣2010

ፖርቹጋላዊው አሳሽ ፈርዲናንድ ማጂላን

ፖርቹጋላዊው አሳሽ፣ ፈርዲናንድ ማጂላን፣ ምዕራባዊውን የባሕር መስመር ተከትሎ፣ ከአትላንቲክ ወደ ሰላማዊ ውቅያኖስ በማቋረጥ ፋና ወጊ ነው፡፡

ማጄላን፣ 270 ባሕረኞችን ያካተተና አምስት መርከቦችን ያቀፈውን አካል እየመራ፣ ለታላቁ ተልዕኮ፣ ከስፔን ባሕር ዳርቻ የተነሳው የዛሬ 498 ዓመት በዛሬው እለት ነው፡፡

አሳሹ፣ ውጥኑን ለዘመኑ የስፔን ንጉስ ቻርልስ አምስተኛ አሳውቃቸው፡፡

ንጉሱም እንዳልከው ይሁን አሉት፡፡

አምስት መርከቦችንና አስፈላጊ ቁሳቁሶችና ስንቅም ፈቀዱለት፡፡

ከፖርቱጋል፣ ከስፔን፣ ከጣሊያን፣ ከጀርመን፣ ከግሪክ ከእንግሊዝና ከፈረንሳይ የተውጣጡ 270 ባሕረኞች፣ ለታላቁ የባሕር መስመር አሰሳ ተሰለፉ፡፡

በመጀመሪያ ጉዟቸው፣ ካናሪ ደሴት ደርሰው፣ ወደ ምዕራብ አፍሪካ የባሕር ዳርቻ፣ ተሻገሩ፡፡

ኬፕቬርዴን አገኙ፡፡

ወደ ምዕራብ አቅጣጫ በማምራት፣ ብራዚል ደረሱ፡፡

ወደ ላቲን አሜሪካ ደቡባዊ ጫፍም አቆለቆሉ፡፡

ጉዞው አልጋ በአልጋ አልነበረም፡፡ ይልቁንም በአድካሚና አታካች ፈተናዎች ተሞላ፡፡

በላቲን አሜሪካ ደቡባዊ ጫፍ፣ የአየሩ ቅዝቃዜ የሚያንዘፈዝፍና አጥንትን የሚሠረስር ነበር፡፡

በዚያ ላይ የሚበላና የሚጠጣው ተሟጠጠ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers