• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሐምሌ 25, 2005:ታሪክን የኋሊት

ሐምሌ 25, 2005

ከ99 ዓመት በፊት አውሮፓ የጦርነት ዳመና አንዣቦባት ነበር፡፡ ታላላቆቹ ሀገሮች የጥቅም፣የገዢነት ስሜትና የተፅዕኖ አሳዳሪነት ፉክክራቸው ጣራ ነካ፡፡ በቡድን በቡድን ጐራ ለዩ፡፡ ሽርክና ፈጠሩ፡፡

ጀርመን፣ ኦስትሪያ ሐንጋሪ፣ የቱርክ አቶማን ግዛትና ቡልጋሪያ በአንድ ወገን ሆኑ፡፡ ፈረንሳይ፣ ብሪታንያና ሩሲያ በሌላው ወገን ተሰለፉ፡፡ እነዚህ ዋነኞቹ ቢሆኑም ሁለቱም ጐራዎች ሌሎች ትናንሽ መንግስታትን በአጫፋሪነት አሠለፉ፡፡ ቅራኔው ከረረ ተካረረ፡፡

እያበጠ እያበጠ መጥቶም መፈንጃው ተቃረበ፡፡ እንደጐርጐሮሳዊው የዘመን አቆጣጠር በሰኔ መጨረሻ 1914 የኦስትሪያ ሐንጋሪው አልጋወራሽ መስፍን ፍራንዝ ፈርዲናንድ ሰራይቮ ውስጥ በሰርብ ብሔረተኛ ተገደለ፡፡ ለጦርነቱ ዋነኛው ምክንያት ባይሆንም ጥሩ ሰበብ ሆነ፡፡ ኦስትሪያ ሐንጋሪ በሰርቢያ ላይ ጦርነት አወጀች፡፡ የአንደኛው የዓለም ጦርነት ፊሽካ ተነፋ፡፡ ይሄ የሆነው የዛሬ 99 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ ጀርመን የሰርቢያ አጋር በሆነችው ሩሲያ ላይ ሩሲያም በጀርመን ላይ ጦርነት አወጁ፡፡

የጀርመን የወረራ ስጋት የገባት ፈረንሳይም ተነስ ታጠቅ አለች፡፡ አንዱ በሌላው ላይ ተነሳ፡፡ዘመተ፡፡ በየስፍራው እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጠለ ጦርነቱ ከአውሮፓም በተጨማሪ ቻይናንም፣ ላቲን አሜሪካንም አፍሪካንም የሩቆቹንም ደሴቶች ሁሉ ነካካ፡፡ የአንደኛው የዓለም ጦርነት ተባለ፡፡ እንዳው ሌላው ሌላው ውድመትና ጥፋት ወደጐን ቢባል እንኳ ከግራ ቀኙ ተፋላሚዎች 10 ሚሊዮን ወታደሮች ተገድለዋል፡፡

ከዚህ በእጅጉ የሚልቁ ሲቪሎችም ተፈጁ ፡፡ ጦርነቱ 21 ሚሊዮኑን ቁስለኛና የአካል ጉዳተኛ አደረገ፡፡ ዓለማችን እስከዚያ ዘመን በአጥፊነታቸውና በአውዳሚነታቸው ከምታውቃቸው ጦርነቶች ሁሉ የከፋውና አሠቃቂው ሆነ፡፡ በየአገሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕፃናትን ወላጅ አልባ አድርጐ አስቀራቸው፡፡ ከፍተኛ የጤና ችግሮችንና ማህበራዊ ጠንቆችንም ትቶ አለፈ፡፡ የብዙዎችን ሕይወት አቃወሰ፡፡

ጦርነቱ በቬርሳይና ተዛማጅ የሰላም ስምምነቶች ተደመደመ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ የቬርሳይ የሰላም ስምምቶችን ስራ ላይ ማዋሉ እየላላ ሄዶ ጀርመንን ለሌላ ጦረኝነት አነሳሳት፡፡ የቬርሳይ ስምምነቶች ቸል መባልም ዓለማችንን ይበልጥ አጥፊ ወደነበረው የ2ኛው የዓለም ጦርነት ነዳት፡፡

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers