• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ግንቦት 15፣2009

የቦኒ ፓርከር ነገር

በአሜሪካ ሉዚያና ቦኒ ፓርከር ‹‹ጉዞው ተፈፀመ›› ስትል ግሩም የሆነ ግጥም ፃፈች፡፡ ግጥሟንም ለእናቷ  ላከችላት፡፡ እናትየዋም ለጋዜጦች ሰጠቻቸው፡፡ ጋዜጦቹም አትመው አወጡት፡፡

ፓርከር የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በነበረችበት ወቅት የነበራት የስነ-ፅሁፍ ዝንባሌ እንዴት ያለች ታላቅ ደራሲና ግሩም ባለቅኔ ይወጣታል ተብሎላት ነበር፡፡

በመጨረሻ ግን መታዋቂያዋ ግጥምና ስነ-ፅሁፍ መሆኑ ቀርቶ ክላይድ ባሮው ከተባለ የዘራፊ ቡድን አለቃ ጋር የፍቅርም የውንብድናም ባልንጀራ ሆኖ ታሪኳ የውንብድና ሆነ፡፡

በውንብድናዋ የገጣሚነት ተስፋዋ በአጭሩ ተቀጭቶ ከነ ግብር አበሯ የተገደሉት የዛሬ 83 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

በ1930ዎቹ መጀመሪያ በታላቁ የዓለም የምጣኔ ሐብት ቀውስ አገሩን አመሰው፡፡ በዚያ ላይ የነቦኒ ፓርከር መጠነ ሰፊ ዝርፊያና ውንብድና ለአገር ምድሩ አስቸገረ፡፡

ዘራፊው ቡድን በማዕከላዊ የአሜሪካ ግዛቶች ከስፍራ ስፍራ በመዘዋወር ገጠር ከከተማ  አራቁቷል፡፡

ከትናንሽ መደብሮች እስከ ታላላቅ የገበያ ማዕከሎች ድረስ ዘርፏል፡፡ በደርዘን የሚቆጠሩ ባንኮችን ካዝና ገልብጧል፡፡

ዘጠኝ ፖሊሶች ገድሏል፡፡ የጨረሳቸው ሲቪሎች ብዛት ቤቱ ይቁጠራቸው የተሠኘላቸው ናቸው፡፡

የሕዝቡ ምሬትና እምባው በዛ፡፡

 

ፖሊስና የፀጥታ ኃይሎችም ይሄ ዝርፊያ ይሄ ውንብድና በሱም ምክንያት ዋይታው ሰቆቃው ግድያው መሳቀቁ ሊበጅለት ይገባል ብለው ቆርጠው ተነሱ፡፡

የነቦኒን ግብረ አበሮችና ተከታዮች ልክ አስገቧቸው፡፡

በመጨረሻው ግን እነሱም አልቀረላቸውም፡፡

በሰረቋት ፎርድ መኪና ሲሊስ በተባለ ስፍራ ፈልሰስ እያሉ ዚጓዙ አድፍጠው ይጠብቋቸው የነበሩ ስድስት የፀጥታ ሰዎች በተኩስ አጣደፏቸው፡፡ የጥይት መአት አወረዱባቸው፡፡ መኪናቸው ወንፊት ሆነች፡፡

ለሌሎች ሞት ሲያድሉ የነበሩት ፓርከርና ባሮው ወር ተረኞቹ ራሳቸው ሆኑ፡፡

አገር ያስቸገሩት እነ ቦኒ ፓርከር እስከወዲያኛው አንቀላፉ፡፡ በዝርፊያና በውንብድናቸው የተማረሩም እፎይ አሉ፡፡ ይህ የሆነው የዛሬ 83 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

ፓርከር አሁንም ድረስ የሚደነቅላትን ግጥሟን ለእናቷ የሰጠችው ከሞቷ ሁለት ሳምንቶች ቀደም ብሎ ነበር፡፡

ቦኒ ፓርከር የፃፈችው ግጥም የመጨረሻዋን የተነበየችበት ብቻ ሳይሆን የላቀ የግጥም ፀሐፊነት ችሎታ እንዳላትም ያስመሠከረችበት ሆነ፡፡

ቦኒ ዳሩ ምን ያደርጋል ውንብድናዋ በግጥሞቿ አንቱ እንዳትሰኝ አነቀፋት ችሎታዋን አጠላበት፡፡ በመጨረሻም የነቦ ፓርከር የውንብድና ታሪክ ለዝነኛ ፊልሞች ማጠንጠኛ ሆኗል፡፡

የዘፈን ርዕሠ ጉዳይ ሆኖ ብዙዎች አቀንቅነውበታል፡፡

የኔነህ ከበደ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers