• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ሚያዝያ 20፣2009

በኢትዮጵያ ላይ የጣሊያን ፋሽስቶች ወረራ በከፈቱበት ወቅት መሪያቸው የዘመኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒቶ ሙሶሊኒ ነበር፡፡

ነገሩ ሳያልቅ አያምር ሆኖበት ሙሶሊኒ ሽንፈት በሸንፈት ላይ ተደራርቦበት ከነፍቅረኛው ተዋርዶ የተገደለው የዛሬ 72 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

ሙሶሊኒ ወደ ፖለቲካው የተሳበው ገና በለጋ የወጣትነት ዘመኑ ነበር፡፡

ከመነሻው ወደ ሠራተኛው መደብ ባዘነበለ ፖለቲካ አቀንቃኝነት የጣሊያን ሶሻሊስት የፖለቲካ ማህበር አባል ሆነ፡፡

በነበረው የዳበረ የሥነ-ፅሁፍ ተሰጥኦና ዝንባሌ የፖለቲካ ማህበሩ ልሳን አዘጋጅ እስከመሆንም ደረሰ፡፡

በዘመኑ የ1ኛው የዓለም ጦርነት የሚካሄድበት ነበር፡፡

ሞሶሊኒ በመጀመሪያ ጦርነት አውጋዥ ፅሁፎችን ያበረክት ያዘ፡፡

ግን ብዙ አልገፋበትም፡፡ የመጀመሪያ አቋሙን ቀይሮ ጦርነት አቀንቃኝ ሆነ፡፡

በዚህን ጊዜ ሶሻሊስቶቹ ከእምነትና ከኃሳባችን አፈንግጠሃልና አታስፈልገንም ብለው ከፖለቲካ ማህበራቸው አባረሩት፡፡

 

ወዲያውም የፋሽስት የፖለቲካ ማህበሩን አቋቋመ፡፡

የፖለቲካ ማህበሩ በአጭር ጊዜ አቅም አበጀ፡፡ ኃይሉ እየፈረጠመ መጣ፡፡

ከ90 ዓመታት በፊት ሮምን በደጋፊዎቹ ሰልፍ ይንጣት ያዘ፡፡

የለዘብተኛውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዊጂ ፋክታን አስተዳደር አስገድዶ ከስልጣን አሽቀነጠረው፡፡

ንጉስ ቪክቶር ኢማኑኤልም የሉዊጂ ፋክታን አስተዳደር ከውደቀት ለመታደግ ማድረግ ያለባቸውን ሳያደርጉ ቀሩ፡፡

የፋሸቶቹ መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ በአመፅ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ስልጣን ተቆጣጠረው፡፡

ሙሶሊኒ ጣሊያንን በፋሽሶቶች መዳፍ ውስጥ ለማስገባት ተጋ፡፡

የአገሪቱን ጦር፣ ፖሊስና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች በፋሺዝም አምሳል ቀረፃቸው፡፡

አገሪቱ በፋሺዝም ሳምባ ትተነፍስ ያዘች፡፡

ወደ 2ኛው የዓለም ጦርነት መዳረሻም ፋሽስቶቹ በአፍሪካ አህጉር ነፃነቷን ጠብቃ የዘለቀችውን ኢትዮጵያን በግፍ የወረሩት በቤኒቶ ሙሶሊኒ መሪነት ነው፡፡

ኢትዮጵያ ጥራኝ ጫካው ጥራኝ ዱሮ ባሉ አርበኞቿ ተጋድሎና በተባበሪዎቿ የጦር ድጋፍ ነፃነቷን ማፅናት ቻለች፡፡

ከጣሊያን ፋሽስቶች ጋር ዓለምን ለማስገበር ክፉ ኃሳብ አድሮባቸው የነበሩት የጦር ሸሪኮቻቸው የጀርመን ናዚዎችና የጃፓን ጦረኞችም ሕልማቸው እየመከነ መጣ፡፡

ከሙሶሊኒ ሞት 2 ዓመታት አስቀድሞ አገሪቱ በደረሰባት ሸንፈት ምስቅልቅል ውስጥ ወደቀች፡፡

ሙሶሊኒ ተይዞ ታሠረ፡፡

መጨረሻው ሲቃረብ የጀርመን ናዚዎች የልዩ ኃይል ኮማንዶዎችን ልከው ከእስር አስመለጡት፡፡

ግን የፋሽስቶቹ መሪ ማንነቱን ሸሸጐ ወደ ኦስትሪያ ለመሸሽ ሙከራ ባደረገበት ወቅት ከፍቅረኛው ክላራ ፔታሲ ጋር ተይዞ በጣሊያን አርበኞች በጥይት ተደብድበው ተገደሉ፡፡

ይሄ ከሆነ ዛሬ 72ኛ ዓመቱን ደፈነ፡፡

አርበኞቹ ገድለው ብቻ አልተዋቸውም፡፡ አስከሬናቸው ወደ ሚላን ከተማ ተወሰደ፡፡

በዚያም ለሕዝብ በግልፅ እንዲታይ ሆኖ ተዘቅዝቀው ተሠቀሉ፡፡ ፋሺዝምም ከነክፉ ኃሳቡ እንዳይመለስ ሆኖ ተሸኘ፡፡

የኔነህ ከበደ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers