• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣የካቲት 14፣2009

ቻይና እና አሜሪካ ጉዳይ

በቻይና በሊቀመንበር ማኦ ሴቱንግ የተመሩት ኮመኒስት የሸምቅ ተዋጊዎች ከ64 ዓመት በፊት የሻንጋይ ሼክን አስተዳደር ከአህጉራዊዋ  ቻይና አባረሩት፡፡

ሻንጋይ ሼክ ወደ ታይዋን በመሸሽ የቻይና ሪፖብሊክ የተሠኘውን  አስተዳደራቸውን መሠረቱ፡፡

አሜሪካ ቤጂንግ ላይ ጥርስ ነከሰችባት፡፡ ማኦ በሊቀመንበርነት ለሚመሯት  ኮሚኒስት ቻይናም እውቅና ነፍጋት ቆየች፡፡

የታይዋን አይዞሽ ባይ ሆነች፡፡

የዋሽንግተንና የቤጂንግ ግንኙነት በፍፁም ጠላትነት ተሞላ፡፡

በኮሪያ ጦርነት ወቅትም ቻይና ከሰሜን ኮሪያ ጋር ወገነች አሜሪካ ደግሞ በተቀራኒው ከደቡብ ኮሪያ ጐን ተሠለፈች፡፡

በቬየትናም ጦርነት ሁለቱ አገሮች ወገንተኝነታቸው ለየቅል ሆነ፡፡

ቅራኔና ጠላትነታቸው የመረረ ሆነ፡፡ 

ከ46 ዓመታት በፊት በዛሬዋ እለት ይህን የግንኙነት ገፅታ የሚለውጥ ክስተት ተፈጠረ፡፡

የዚያን ጊዜው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሪቻርድ ኒክሰን በቻይና ኦፊሴላዊ ጉብኝት ለማድረግ ቤጂንግ የገቡት የዛሬ 46 ዓመት በዛሬው እለት ነበር፡፡

 

ኒክሰን ከማኦ ጋር ተጨባበጡ፡፡

ክስተቱ የታሪክ መለወጥ ምልክት ሆነ፡፡

ከኒክሰን ጉብኝት በፊት በሁለቱ አገሮች የጠረጴዛ ቴኒስ (ፒንግ ፖንግ) ተጫዋቾች መካከል ወዳጅነት መፈጠሩ ለግንኙነቱ መታደስ መንገድ ከፋች ሆነ፡፡

በታሪክም የፒንግ ፖንግ ዲፕሎማሲ የሚል ስያሜ ተሰጠው፡፡

ብዙም ሳይቆይ ሁለቱ አገሮች አንዷ በሌላዋ በጉዳይ ፈፃሚ ደረጃ አገናኝ ቢሮዎቻቸውን ከፈቱ፡፡

በውጤቱ የቻይና ሪፖብሊክ ተብላ የምትታወቀው ታይዋን ይዛው የቆየችውን የፀጥታው ምክር ቤት አባልነት መቀመጫ ቤጂንግ ተረከበችው፡፡

ታይዋን ከፀጥታው ምክር ቤት ተባረረች፡፡

ከኒክስን የቻይና ጉብኝት 7 ዓመታት በኋላ አሜሪካና ቻይና በዋሽንግተንና በቤጂንግ ኤምባሲዎቻቸውን ከፈቱ፡፡

ግንኙነቱ ወደ ላቀ ደረጃ ተሸጋገረ፡፡ ቻይናና አሜሪካ በአስተዳደርና በፍልስፍና ዘይቤ፤ በምጣኔ ሐብታዊ ጉዳዮችና በሌሎችም ምክንያቶች ቅራኔና እሰጥ አገባቸው ያለ ቢሆንም የታደሰ ግንኙነታቸው ግን ፀንቶ እንደዘለቀ ነው፡፡

የኔነህ ከበደ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers