• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ታህሳስ 25፣2009

ቤኒቶ ሙሶሊኒ

በ2ኛው የዓለም ጦርነትና ከዛም በፊት በሰፊው የጥፋት አሻራቸውን ካኖሩት መካከል የጣሊያን ፋሽስቶች መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ ፍፁማዊ ፈላጭ ቆራጭ ገዢ መሆኑን ያወጀው የዛሬ 91 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ሙሶሊኒ በወጣትነቱ ልቡ ወደ ሶሻሊስታዊ ፖለቲካ አዘነበለ፡፡

የሥነ-ፅሁፍ ችሎታውን ተጠቅሞ ጦርነት አውጋዥ መጣጥፎችንና ትንታኔዎች ያቀርብ ያዘ፡፡

ለምሣሌ ከ100 ዓመታት በፊት ጣሊያን ሊቢያን ለመያዝ ታደርግ የነበረውን ሙከራ ኢምፔሪያሊስታዊ ተስፋፊነት ሲል ያብጠለጠለበት ፅሁፉ ይጠቀስለታል፡፡

በአንደኛው የዓለም ጦርነት ሂደት ሙሶሊኒ የነበረበት የጣሊያን ሶሻሊስቶች የፖለቲካ ማኀበር ጦርነቱን እቃወማለሁ አለ፡፡

ሙሶሊኒም ይሄንኑ የጦርነት አውጋዥ ውሣኔ ደጋፊ ሆነ፡፡

ግን በጦርነት ተቃዋሚነቱ ብዙም አልገፋበትም፡፡

ጥቂት ቆይቶ ጦርነት አራጋቢ ሆነ፡፡

የጣሊያን ሶሻሊስቶች ከውሣኔያቸው ውጭ የሆነውን ሙሶሊኒን አታስፈልገንም ብለው ከማኅበራቸው አባረሩት፡፡

ሙሶሊኒ የፋሽስት የፖለቲካ ማኅበሩን መሠረተ፡፡

የፋሽስት የፖለቲካ ማኅበሩ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ጡንቻው ፈረጠመ አቅሙ በረታ፡፡

 

በተቃውሞ ሰልፉ በግርግርና በቱማታ የጠቅላይ ሚኒስትር ሉዊጂ ፋክታን ሕጋዊ መንግሥት ገልብጦ ሥልጣን ለመያዝ በቃ፡፡

አፄ በጉልበቱ የነበረው ሙሶሊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ተሠኘ፡፡

ቀስ በቀስ ሕገ-መንግስታዊ የአስተዳዳር አካላትን መነጋግሎ ሲጥላቸው ሃይ ባይ አልነበረውም፡፡

የአገሪቱ ጦርና የፀጥታ ኃይሎች በፋሽስት አምሳል ቀረፃቸው፡፡

ሕዝቡን በሽብር አገዛዝ ሰጥ ለጥ አደረገው፡፡ በመጨረሻም ሥልጣኑን ጠቅልሎ በመዳፉ አስገባ፡፡ ይሄ መሆኑን በይፋ ካወጀ ዛሬ ልክ 91ኛ ዓመቱን ደፈነ፡፡

ከዚህም ተከትሎ ሙሶሊኒ በሉዓላዊቷ ኢትዮጵያ ላይ የግፍ ወረራ ፈፀመ፡፡

በ2ኛው የዓለም ጦርነት ሂደት ዓለምን እናስገብራለን ብለው በእብሪት ከተነሱት ከጀርመን ፋሽስቶችና ከጃፖን ተስፋፊዎች ጋር ማህበር ገባ፡፡

ኢትዮጵያ ጥራኝ ጫካው ጥሪኝ ዱሩ ባሉ አርበኞቿ መራር ተጋድሎና በአጋሮች ድግፍ ነፃነቷን አረጋገጠች፡፡

የጣሊያን ፋሽስቶች ለሰላም በቆሙት የኅብረቱ ኃይሎች የሽንፈት ፅዋን በመጐንጨት ቀዳሚዎቹ ሆኑ፡፡

ሙሶሊኒም ተይዞ ታሰረ፡፡ በናዚ ተባባሪዎቹ ድጋፍ አመለጠ፡፡

በመጨረሻ በጣሊያን አርበኞች ዳግም ተይዞ በሞት ተቀጣ፡፡

ቀጪዎቹ በዚህ ብቻ አልተውትም፡፡

አስክሬኑን ወደ ሚላን ከተማ ወስደው ዘቅዝቀው ሰቀሉት፡፡

የፋሺዝምና የሙሶሊኒ ምዕራፍ እስከወዲያኛው ተዘጋ፡፡

የኔነህ ከበደ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers