• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ታህሳስ 19፣2009

የሜሲናው የመሬት ነውጥ

ዓለማችን ለቁጥር የሚያታክቱ የመሬት ነውጦችን አሳልፋለች፡፡

የደቡባዊ ጣሊያኖቹን የሜሲናና ሬጂዮ ካላብሪያ ከተሞችን ሙሉ ለሙሉ እንዳልነበሩ አድርጎ ያጠፋቸው አስከፊ ርዕደ መሬት የደረሰባቸው የዛሬ 108 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

አስከፊው የሜሲና ርዕደ መሬት ዋነኛ የንቅናቄ ማዕከሉን የሲሲሊዋን ሜሲና ከተማን አደረገ፡፡

በርዕደ መሬት መለኪያ /ሬክተር ስኬል/ 7 ነጥብ 1 ተመዘገበ፡፡

አካባቢውን ከ30 እስከ 40 ሰኮንድ ክፉኛ አርገፈገፈው፡፡ ግልብጥብጡን አወጣው፡፡ እንደ ኳስ አነጠረው፡፡

የንቅናቄ ማዕከሉ የሲሲሊ ደሴቷ ሜሲና ብትሆንም በዋናዋ ጣሊያን ደቡባዊ ጫፍ የምትገኘውንም ሬጂዮንም መታት፡፡

በዚያ ላይ እዚህም እዚያም እሳት ተቀስቅሶ ቃጠሎ ሆነ፡፡

ጥፋቱና ውድመቱ በሜሲና  እና ሬጂዮ ካላብሪያ ከተሞች ላይ ቢከፋም በ300 ኪሎ ሜር መጠን ዙሪያ የተለያየ ደረጃ ጉዳት አስከትሏል፡፡

ርዕደ መሬቱ ከ108 ዓመታት በፊት የነበረችዋን የሜሲና ከተማን እንዳልነበረች አደረጋት፡፡

 

ከ90 በመቶ በላይ የከተማዋን ቤቶችና ህንፃዎች ወደ ፍርስራሽ ክምርነት ቀየራቸው፡፡

ከ150 ሺህ ነዋሪዎቿ የግማሽ ያህሉን ነፍስ ነጠቃት፡፡

ብዙዎችን ለተለያየ ደረጃ የአካል ጉዳት ዳረጋቸው፡፡

ከተማዋን ያለ ሁነኛ ታሪካዊ መታወሻ አስቀራት፡፡

ጥንታዊ መታወሻዬ ነው የምትለው ነገር ቢኖር ፎቶ ግራፎቿ ብቻ ናቸው፡፡

የካሌብሪያ ሬጂዮንም የ25 ሺ ነዋሪዎችን አሳጥቷታል፡፡

መተላለፊያ ድልድዮች በመደረማመሳቸውና የባቡር ሐዲዶች በርዕደ መሬቱ ከጥቅም ውጭ በመሆናቸውና የመገናኛ አውታሮች በመሰነካከላቸው አፋጣኝ የነፍስ አድን እርዳታ እንዳይደርስ እክል ፈጠረ፡፡

ከርዕደ መሬቱ በተጨማሪ በባህር ውስጥ የደረሰ የመሬት መንሸራተት የሱናሚ ማዕበል መቀስቀሱ በእቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆነ፡፡ መርከቦችን እርስ በርሳቸው በማላተም የአደጋውን መጠን ከፍ አደረገው፡፡ ከዛሬ 108 ዓመታት በፊት ከደረሰው አሰቃቂ የሜሲና ርዕደ መሬት በሕይወት ተራፊዎች ከእንግዲህ ምን ተስፋ አለን ብለው እስከወዲያኛው ትተዋት ስደት ገቡ፡፡

በታሪክ የሜሲናው የመሬት ነውጥ የሚል ስያሜ የተሰጠው ርዕደ መሬት ጣሊያን ካጋጠሟት አስከፊ የተፈጥሮ አደጋዎች አንዱ ሆኖ ይታወሳል፡፡

የኔነህ ከበደ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers