• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ታህሳስ 17፣2009

ታላቁ ነውጥ

ታላቁ የሕንድ ውቅያኖስ ነውጥ የደረሰው የዛሬ 12 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

የታላቁ ነውጥ መነሻ ከኢንዶኔዥያዋ ሱማትራ በስተሰሜን በ160 ኪሎ ሜትር ርቀት ከሴሜውሉ ደሴት በ30 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ከሚገኝ የውቅያኖስ ክፍል ነው፡:

መነሻው ከሲሜውሉ ደሴት ጥልቅ የውቅያኖስ አካል ቢሆንም እንቅጥቃጤው ሰፊ የዓለማችንን ክፍሎች አካልሏል፡፡

በርዕደ መሬት መለኪያ /ሬክተር ስኬል/ 7 ነጥብ የሚመዘገብ ነውጥ አደገኛ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡

በኢንዶኔዥያ ነውጥ ግን ከዚያ በላይ 9 ነጥብ 3 ሆኖ መመዝገቡ ከአደገኛ ይበልጥ አደገኛ እንደነበር ያስረዳል፡፡

ነውጥ በሬክተር ስኬል መለካት ከጀመረበት አንስቶ እስከዚያን ጊዜ በነበሩ 100 ዓመታት ውስጥ ከደረሱት በ3ኛው ከባድ ነውጥነት ተመዝግቧል፡፡

ነውጡ ሌላም ባህሪ ነበረው፡፡ እግጅ አደገኛ የተባሉት አብዛኞቹ ነውጦች ከፍተኛ ጥፋት የሚያደርሱት በጥቂት ሰኮንዶች ቅፅበት ሲሆን የዛሬ 12 ዓመት የደረሰው እስከ 10 ደቂቃ የዘለቀ ነበር፡፡

በዚያው ቅፅበት ኢንዶኔዥያን ብቻ ሳይሆን ባንግላዴሽን፣ ሕንድን ሲሪላንካን፣ ማያንማርን፣ ታይላንድን ሲንጋፖርንና የማልጂቭስ ደሴቶችንም ክፉኛ አርገፍግፏቸዋል፡፡

ነውጡ ከእስያ አገሮች አልፎ እስከ አሜሪካዋ አላስካ ድረስ ተሰምቷል፡፡

በወቅያኖስ ወለል ላይ መሰነጣጠቅን አስከትሏል፡፡

ክፋቱ የውቅያኖስ የውሃ ከፍታን እስከ 30 ሜትር በመጨመር በሱናሚ የባህር ማዕበል መታገዙ ጥፋቱን ያሰፋ ያከፋም ጭምር መሆኑ ነበር፡፡

የሱናሚ ማዕበሉ ከእስያዎቹ አገሮችም አልፎ የሕንድ ውቅያኖስ አዋሳኝ የሆኑ የአፍሪካ አገሮችን ሳይቀር አዳርሷል፡፡

በአጠቃላይ አደጋው 14 አገሮችን በጥፋቱ ጎብኝቷቸዋል፡፡

የሕንድ ውቅያኖሱ ነውጥና የሱናሚ ማዕበል በጥፋቱ ባዳረሳቸው አገሮች 280 ሺህ ያህል ሰዎችን መግደሉ የአደጋውን ታላቅነት ያሳያል፡፡

የኔነህ ከበደ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers