• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር | ወግ

በመንገዱ ርቀት እና አስቸጋሪነት ሳቢያ ልጆችዎ ቶሎ ቶሎ ወደ ቤት እየመጡ ሊጠይቅዎት ካልቻሉ ምን ያደርጋሉ ?

በመንገዱ ርቀት እና አስቸጋሪነት ሳቢያ ልጆችዎ ቶሎ ቶሎ ወደ ቤት እየመጡ ሊጠይቅዎት ካልቻሉ ምን ያደርጋሉ ? እርስዎ ራስዎ ይሄዳሉ ወይንስ…የ45 ዓመቱ ሕንዳዊ ጃላንድሃር ናያክ ግን ዶማ እና ድንጋይ መፈንቀያውን ይዞ ተነሳ - መንገድ ሊሰራ፡፡

እናም አደረገው…

በምስራቅ ሕንድ ባለች አንዲት የገጠር መንደር ውስጥ የሚኖረው ናያክ፤ 3 ወንድ ልጆቹ የሚማሩት 10 ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ ባለ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው፡፡ እናም … በርቀቱ ሳቢያ ልጆቹ ቶሎ ቶሎ ወደ ቤታቸው እየመጡ አያያቸውም፡፡ ለዚህም ችግር መፍትሄ ፍለጋ የዛሬ 2 ዓመት ግድም መንገድ ለመስራት ዶማ እና ድንጋይ መፈንቀያውን ይዞ ተነሳ…

እናም የቢቢሲው ድረገፅ ዘገባ እንደሚለው ሕንዳዊው አባት ያለማንም እርዳታ ብቻውን በአካፋና ዶማ 8 ኪሎሜትር መንገድ ሰራ፡፡

የናያክ ልጆች ከትምህርት ቤት ወደ አባታቸው ቤት 5 ኮረብታዎችን አቆራርጠው ለመምጣት የ3 ሰዓታት ያህል የእግር ጉዞ ማድረግ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡

ናያክ ግን ይህን ልጆቹን ቶሎ ቶሎ ወደ ቤታቸውን እንዳይመጡ ያደረገውን እንቅፋት ለማንሳት ላለፉት 2 ዓመታት በቀን 8 ሰዓታት በዶማ እና ድንጋይ መፈንቀያው አለት ሲፈነቅል፣ ጉብታ ሲንድ ከርሞ 8 ኪሎሜትር መንገድ ሰራ ይለናል የቢቢሲው ዘገባ…

ተጨማሪ ያንብቡ: በመንገዱ ርቀት እና አስቸጋሪነት ሳቢያ ልጆችዎ ቶሎ ቶሎ ወደ ቤት እየመጡ ሊጠይቅዎት ካልቻሉ ምን ያደርጋሉ ?

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የቻይናው መሪ የዢ ጂን ፒንግ ነገር…

“በበጎ ምግባር የሚያስተዳድር እንደ ሰሜናዊቷ ኮከብ ነው”

ማን ያውቃል አሁን “የእኔ ልጅ እኮ ቦስተን ነች” ተብሎ ሴቶች እድር ላይ እንደሚፎከረው ከዓመታት በኋላ “የእኔ ልጅ እኮ ቤይጂንግ ነች” ተብሎ ይፎከር ይሆናል፡፡

“የህልሜ ደረሰ፣ ልመናዬን ሰማኝ፡፡ 
“ምን ተገኝቶ ነው?”
“ልጄ ቻይና ሊሄድልኝ ነው”
“አትለኝም!” 
“ሙት ስልህ፣ እሁድ ማታ ነው የሚበረው”
“እግዜሐር ይወድሃለ ማለት ነው - በጣም እድለኛ ሰው ነህ”

ግዴላችሁም…ከዓመታት በኋላ እንዲሀ አይነት ምልልሶች የድራፍት ጠረጴዛዎችን የማይቆጣጣሩበት ምክንያት የለም፡፡

ጉዞ ወደ ቻይና ሆኗል፡፡ ለዘመናት “አሜሪካ፣ አሜሪካ” ሲባል እንደነበረው አሁን “ቻይና፣ ቻይና” ማለትን መለማማድ ጀምረናል፡፡ እንደውም እንደሚባለው ከሆነ ልክ እንደ አሜሪካ ጉዞ ሁሉ ወላጆች ልጆቻቸውን ቻይና ለመላከ ምንም አይነት ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ እየሆኑ ናቸው ተብሏል፡፡

አብዮተኞቹ በማኦ ዜዱንግ፣ የፊልም ወዳጆቹ ደግሞ በእነ ጃኪ ቻንና ጄት ሊ የሚያውቋት ቻይና የሚያቃጥል ጫማ ብቻ አይደለችም፡፡ አራት ቀን በርቶ፣ በአምስተኛው ቀን ጭል ጭል ብሎ በስድስተኛው ቀን ውድም እንደሚለው አምፖል ብቻ አይደለችም፡፡ እሱ፣ እሱ የእኛ የጥራት ቁጥጥር ጉዳይ ነው፡፡ የአሁኗ ቻይና “ስም ሲያወጡ ሸክላ ሳህን ድንጋይ ላይ እየከሰከሱ በሚወጣው ድምጽ መሰረት ነው” ብለን የምንቀልድባት የትላንቷ ቻይና አይደለችም፡፡

ታዲያ… ለአሁኗ ፈጣን ግስጋሴዋ በርካታ ምክንያቶች መዘርዘር ቢቻልም በዋንኝነት ከሚጠቀሱት መሀል አንድ ሰው አሉ … የአሁኑ መሪ ዢ ጂን ፒንግ፡፡ ጠንካራ መሪዎች በሀገር እድገት ላይ የሚያሳድሩት ተጽእኖ ምሳሌ ናቸው ነው የሚባለው፡፡

እንዲህ ሆኖ ታዲያ ሰውየው እጅግ ኋላ ቀር ከሆነች የገጠር መንደር እስከተንጣለለው የቤይጂንግ የስልጣን ማማ የነበራቸው ጉዞ ቀላል አልነበረም፡፡

ከአምስት አስርት ዓመታት በፊት ቻይና አየተናጠች ነበር - የባህል አብዮት ባሉት የማኦ ዘመቻ፡፡ ዢ ጂን ፒንግ 15 ዓመታቸው ነበር፡፡ በሀገሪቱ ገደላማ ሸለቆዎችና ተራሮች ከባዱን የገጠር ኑሮ እየተፋለሙ ነበር፡፡ የእርሻ ሥራቸውን ያካሂዱባት የነበረችው ያናን የተባለችው ስፍራ በእርስ በእርስ ጦርነቱ ጊዜ የኮሚኒስቶቹ መናኸሪያ ነበረች፡፡ እንደውም ያናን ራሷን “የቻይና አብዮት ቅድስት ስፍራ” ብላ ትጠራ ነበር፡፡

የዢ ታሪክ ታድሷል፣ አብዛኛዎቹ የቻይና ገጠራማ ስፍራዎች በሚያስደንቅ ፍጥነት ወደከተማነት ሲለወጡ እሳቸው ያደጉባት መንደር ለኮሚኒስት ፓርቲው አፍቃሪዎች የመንፈሳዊ አይነት ጉዞ መዳረሻ ሆናለች፡፡

በ1968 ማኦ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣቶች ከከተማ ወደ ገጠር ዘምተው ከአርሶ አደሮች ከባድ ህይወት ልምድ እንዲቀስሙ አዘዙ፡፡ “በ15 ዓመቴ ስደርስ ያልተረጋጋሁና ግራ የተጋባሁ ነበርኩ፣” ይላሉ ዢ፡፡ “በ22 ዓመቴ ለቅቄ ስሄድ የህይወቴ ግቦች ጠንካራ የሆኑና በራስ መተማመንም የተሞላሁ ነበርኩ፡፡”

በወጣትነታቸው የመጀመሪያ ዓመታት ዢ መልካም የሚባል አስተዳደግ ነበራቸው፡፡ አባታቸው የኮሚኒስቱ አብዮት ጀግና ነበሩና፡፡ ሆኖም በ1960ዎቹ ሁሉም ነገር የእምቧይ ካብ ሆነና አረፈው፡፡ የማኦ ተጠራጣሪነትና የበቀል ስሜት ጣራ ነካ፣ የአብዮቱ ጠላቶች የሚሏቸው ላይም ከባድ በትራቸውን ሰነዘሩ፡፡ ድፍን ቻይና ተርበደበደች፡፡

ብዙዎችም ሰለባ ሆኑ፡፡ በትሩ የዢ አባትንም አልማረም፡፡ መጀመሪያ ከፓርቲው ተባረሩ፣ ከዚያም ወደ ዘብጥያ፡፡ ቤተሰባቸውም በአደባባይ ተዋረደ፡፡ እንደውም አንድ እህታቸው ህይወቷ አለፈ፡፡ ምናልባትም በብስጭት ራሷን አጥፍታ ሊሆን ይችላል የሚል መላ ምት ነበር፣ ማንም አላረጋገጠም እንጂ፡፡

ዢ 13 ዓመት ሲሞላቸው ሳይወዱ መደበኛ ትምህርታቸውን አቆሙ፣ ምክንያቱም በድፍን ቤይጂንግ ትምህርት ቆሞ ነበርና ! ነገሩ አብዮት ልጇቿን ትበላለች ነበርና ትምህርት እንዲቆም የተደረገው ተማሪዎች አስተማሪዎቻቸውን እንዲተቹ፣ እንዲደበድቡና ብሎም እንዲገድሉ ለማስቻል ነበር ይላሉ የቻይናን ታሪክ በቅርበት የሚከታተሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: የቻይናው መሪ የዢ ጂን ፒንግ ነገር…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የባቲ እና አምባሰል ንግስት እያሉ ብዙዋች ይጠሯታል...ማሪቱ ለገሰ

Photo Courtesy:Enchewawot on Ebs tvዘለግ ያለ ጊዜዋን በሙዚቃ ሕይወት አሳልፋለችበግሏ ካበረከተችው አልበሞች በተጨማሪ ዛሬ በሕይወት ከሌሉት የባህል ሙዚቃ ቁንጮዎች ጋሽ ይርጋ ዱባለ፤ከተማ መኮንን፤ባህሩ ቃኜ፤ሐ/ሚካኤል ደምሴ ጋር በጋራ የሰራቻቸው ስራዎች ዛሬ ድረስ ተወደው እንደ አዲስ ይደመጣሉ

የባቲ እና አምባሰል ንግስት እያሉ ብዙዋች ይጠሯታል...ማሪቱ ለገሰ:: ቴዎድሮስ ወርቁ በአሜሪካ በቤቷ ተገኝቶ ያደረጉትን ቆይታ እነሆ...

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሙት መንፈሱ ነገር…

ሚኒባስ ታክሲ ላይ ነው … ሾፌርና ረዳት ብሶት ብቻ ነበር የሚያወሩት፡፡ ነዳጅ ውድ እንደሆነ፣ የታክሲ ታሪፉ ትንሽ እንደሆነ፣ ተራ አስከባሪዎች ጉልበተኞች እንደሆኑባቸው፣ ትራፊኮች በየመንገዱ እያስቆሙ አላሠራ እንዳሏቸው … ብቻ የማይኮንኑት የለም፡፡ እናም ሾፌር፣ 

“ይሄን ሁሉ የሚያደርገን እኮ መንግሥት ነው፣” ይላል፡፡

ረዳቱም፣ “እነሱ እኮ ታክሲ እንዲጠፋ ነው የሚፈልጉት” አይነት ነገር ይላል፡፡ ይሄኔ አንዱ ጎልማሳ ተሳፋሪ፣ “እናንተ አሁን ምን ሆንን ብላችሁ ነው መንግሥት ላይ የምታማርሩት ? እኛ ነን እንጂ በስንቱ ነገር የምንሰቃየው” ይላል፡፡

ሌላ ተሳፋሪም፣ “ተዋቸው እባክህ … ምን እንዳያመጡ ነው፣ ወሬ ብቻ!” ይላል፡፡

ይሄኔ ሾፌር ሆዬ “የንጉሡን መንግሥት የገለበጡት እኮ ታክሲ ነጂዎች ናቸው” ይላል፡፡ መጀመሪያ የተናገረው ሰው ምን ቢመልስለት ጥሩ ነው፣
“አዎ፣ እነሱ መንግሥት ገልብጠዋል፡፡ እናንተ ደግሞ የሰዉን ኪስ ትገለብጣላችሁ” አላቸው፡፡

ለጠቅላላ እውቀት ያህል … 1966 የታክሲዎች ኩዴታ ነበር እንዴ!.. እየጠራ ይሂድ ብለን ነው፡፡ ምናልባት እንደ ዘንድሮ አያያዛችን ከጥቂት ዓመታት በኋላ “የ66ቱ የታክሲዎች አብዮት” ነገር ማለት ይጀምር ይሆናል፡፡ ቃልና ታሪክ ለመለወጥ ሁሉም ሰው ሊቼንሳ ያለው የሚመስልባት አገር የእኛዋ ብቻ ሳትሆን ትቀራለች…

አንድ ነገር አለ፣ ባለፈው ታሪካችን እንኮራለን፡፡ ለምን አንኮራም … በበጎው ታሪካችን ሁሉ አሳምረን እንኮራለን ! ታሪክ የሌለው አገር ሁሉ እየፈጠረ ‘ግነን በሉኝ’ ሲል እኛ … ለሌላ በሚተርፍ ታሪካችን ብንኮራ ምንም የሚገርም ነገር አለው ! ትልልቆቹ አገሮች ሚጢጢ የምታክለውን ነገር ሁሉ ልክ እንደ ተአምራዊ ታሪከ ለማድረግ ሲሯሯጡ እኛ ማጋነንም፣ ማሳበጥም ሳያስፈልገን የምንኮራባቸው በርካታ ታሪኮች አሉን…

ግን ያለፍውን በጎ ታሪክ ክሬዲት ወይም ባለቤትነት ከሠሪዎቹ ወደእኛ ሲዞር አንገት ማስደፋት አለበት፡፡ ጥያቄው የቀደሞዎቹ በጣሉት መሰረት ላይ የኋለኞቹ ምን ጨመርንበት ነው ! እንዲህ ብለን የምንጠይቅ ብዙ አይደለንም እንጂ…

የሆነ መንደርተኛ በሆነ ነገር ከጎረቤቶቹ ተጋጨ እንበል፣ “እናንተማ ምን ታደርጉ፣ ይሄን እልም ያለ ጫካ ሰፈር ያደረጉትና ያቀኑት እኮ የእኔ ወላጆች ናቸው፡፡ አዳሜ ከየትም፣ ከየትም ጨርቅሽን ጠቅልለሽ መጥተሽ…” ምናምን አይነት ደረቱን ይነፋል፡፡ እናስ ! እነሱ መንደሩን አቀኑ፣ እሱ የየጎረቤቶቹን አጥር እየነቀነቀ አይደል እንዴ ! በወር አምስት ቀን ቀበሌ እየተጓተተ አይደል እንዴ ! እሱ መንደር እያመሰ፣ መንደር ያቀኑ ወላጆቹን ክሬዲት መመንተፍ ይፈልጋል፡፡

ለምሳሌ የሆነ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪ “አብዮቱን ያመጣው እኮ የተማሪ ንቅናቄ ነው፣” ምናምን ይል ይሆናል፡፡ እና የእዛ ዘመን ተማሪዎች የረገጡትን ካምፓስ ስለረገጠ በኩራት አየር ላይ ይንሳፈፍ ይሆናል፡፡ እሺ ይሁን…ግን ልዩነቱ ለአብዮቱ አንዱ ምክንያት ነው የሚባለው የተማሪ ንቅናቄ ጥያቄው ‘መሬት ላራሹ’ የመሳሰሉት ህዝባዊ ጥያቄዎች ነበሩ፡፡

ከጥቂት ዓመታት በፊት የነበረው ደግሞ “የዳቦው መጠን ቀነሰብን፣” አይነት ለየት ያለ ሪቮሉሽን ነው፡፡ ጦሙን እየዋለ “የእኛ ምግብ በድርቅ ለተጎዱት ወገኖቻችን ይሂድልን” በሚልና “ይቺን ዳቦ በልተን ነው የምንውል!” በማለት መካከል ሦስት ውቅያኖሶች ያህል ርቀት አለ፡፡

ዘንድሮ ክሬዲት በቆረጣ ከመውሰድ ይልቅ የባሰበትና አልለቅ ያለን ነገር ያለፈውን መርገም ነው፡፡ ከአርባ፣ ከሰባ፣ ከመቶ ምናምን ዓመት በፊት የተሠሩትን፣ ወይም ባይሠሩም በድፍረት ተሠሩ የምንላቸውን አያነሳን እርግማ ! እርግማን! እርግማን! ብቻ ሆኗል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: የሙት መንፈሱ ነገር…

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

“ብታምኑም ባታምኑም ቀለበት ውስጥ ከተውናል”

“ንቀውናል፣ ደፍረውናል - ብታምኑም ባታምኑም በቁማችን ሞተናል” ተብሎ ነበር ያኔ፡፡ ዘንድሮም ደግሞ ‘ብታምኑም፣ ባታምኑም’ የሚባል ነገር አይመጣም አይባልም፡፡“ንቀውናል፣ ከበውናል፣ ብታምኑም ባታምኑም ቀለበት ውስጥ ከተውናል” የሚያስብል ነገር አይመጣም አይባልም፡፡ ታንኩ በቅርብ እየሰፈረ ነው፣ ከባድ መሳሪያው በቅርብ እየሰፈረ ነው፣ የጦር መርከብና ጀልባው ከማዶ እያጓሩ ነው፡፡ በአፍሪካ ቀንድ ጦር ሰፈሮች ለማቋቋም የሚደረገው ሽሚያ የሚመስል ጥድፊያ ጦፏል … አፍንጫችን ስር ማለት ነው፡፡

ያኔ ምድረ ቅኝ ገዥ “ከዚህ እስከዚህ የእኛ”፣ “ከዚህ እስከዚህ ደግሞ የእኛ” እያሉ አህጉሪቷን ይቀራመቷት በነበረበት ዘመን ‘ዘ ስከራምብል ፎር አፍሪካ’ የሚባል ነገር ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ‘ዘ ስክራምብል ፎር ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ’ የሚል ነገር እየተፈጠረ ይመስላል፡፡ቀደም ባሉት ዘመናት እኮ ጣጣ አልነበረውም…ወይ ሶቪየት ህብረት ነች፣ አለበለዚያም አሜሪካ ነች፡፡ አሁን ግን በተለምዶ ጦራቸውን ከድንበራቸው አስወጥተው የማያውቁና ‘ሀያላን’ የሚል ቅጽል ገና ያልተሰፋላቸው ሀገራት በአካባቢያችን ጦር ሰፈሮች እየመሰረቱ ነው … ዙሪያችንን ለመባል ምንም በማይቀረው ሁኔታ፡፡

በተለይ ነሀሴ ላይ ቻይና በጅቡቲ የጦር ሰፈር ስትመሰርት ታላላቆቹ የዓለም መገናኛ በዙሀን ሁሉ “ይሄ ነገር እንዴት ነው?” ማለት ጀመሩ፡፡ ቻይኖቹ ማብራሪያ ነበራቸው፡፡ “ይሄ የጦር ሰፈር ሳይሆን በአካባቢው ላለን የሰላም ማስከበርና ሰብአዊ ተግባሮቻችን የአቅርቦት ጣቢያ ነው፣” አሉ፡፡ ማንም “እንዳላችሁ” አላላቸውም፡፡ እንደውም ቻይና በአፍሪካ ቀንድ፣ በመላው አፍሪካም ላላት የመስፋፋት ፖሊሲዋ እንዲመቻት ያደረገችው ነው ተባለ፡፡

የቅርብ ማስረጃ ሲባል… የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የበቀደሙ ኮንግርስ ላይ ፕሬዝደንቱ “ቻይና ዓለም ላይ የመሪነት ሚና መጫወት አለባት፣” ያሉትን ይጠቅሳሉ፡፡ ሆኖም አሁን የቻይና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በተለይ የባህረ ሰላጤው ሀገራት በአፍሪካ ቀንድ መሰባሰብ ጥያቄዎችም፣ መላ ምቶችም እያስከተለ ነው፡፡የባህረ ሰላጤውን ፍጥጫ ወደ አፍሪካ ቀንድ እያስፋፉት ነው ተብሏል፡፡ እንዳጋጣሚ አካባቢው ያሉት ሀገራት በሁሉም መለኪያዎች ኋላ ቀር መሆናቸው በገንዝብ ለማማባልም አያስቸግሩም ነው የሚባለው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: “ብታምኑም ባታምኑም ቀለበት ውስጥ ከተውናል”

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers