• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር | ወግ

ዓይነ ስውሩ ፎቶ ግራፍ አንሺ ወጣት አብዱ ሰኢድ...

ይህ አይነስውር ወጣት አብዱ ሰኢድ ይባላል፡፡ፎቶ ግራፍ አንሺ ነው የሰዎችን ድምፅ በመስማት ብቻ ግሩም ፎቶ ያነሳል፡፡አብዱ በቋንቋና ሥነ-ፅሁፍ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡

ሥራ ቢጠፋም የልብ ፍላጐት ካለ የማይሳካ የለም ይላል አብዱ ሰኢድ

የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጅ ወንድሙ ሃይሉ አይነ ስውሩን ፎቶ ግራፍ አንሺ ላስተዋውቃችሁ ይላል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ይህቺ ወፍ ይህን ልጅ አትወደውም….

ለምን?

መልስ የለም…

በምስሉ ላይ የምታዩት የ5 ዓመቱን ማርኮን ሱራፌልን ይህች ወፍ በወጣ በገባ ቁጥር እያባረረች መሃል አናቱን ስትቀውረው እነሆ አመት አለፈ ይለናል የሸገሩ ወንድሙ ኃይሉ…ምክንያቱ ለምን እንደሆነ ማንም የሚያውቅ የለም፡፡ትምህርት ቤት ሲሄድ ከሰዎች መሃል ለይታ በመንቁሯ ቀውራው ትበራለች፡፡ ሲመለስም እንደዚያው፡፡

ወፏ እንዳትለየው ኮፊያ ቢያደርግም፣ ቢከናነብም፣ የእህቱን ልብስ ለብሶ ቢወጣም ከወፏ አያመልጥም… - ተከትላ ትቀውረዋለች፡፡ትንሹ ማርኮን፣ “እኔ ምንም አላደረግኳትም - ተከትላ ትቀውረኛለች” ይላል፡፡ይህን የአካባቢውን ሰው ሁሉ አጀብ ያስባለ እንቆቅልሽ ቦታው ድረስ ሄዶ የተመለከተው ወንድሙ ኃይሉ የገረመኝ ይግረማችሁ ብሎ የነገረንን ወሬ ሙሉውን እንድታዳምጡ ጋብዘናል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ፣ በብድር፣ በርዳታና ከዜጎቿ በሚሰበሰብ ገንዘብ መሰረት ልማቱን እና ሌላ ሌላውን እየተጋች ቢሆንም...

ኢትዮጵያ፣ በብድር፣ በርዳታና ከዜጎቿ በሚሰበሰብ ገንዘብ መሰረት ልማቱን እና ሌላ ሌላውን እየተጋች ቢሆንም፤ በብዙ ውጣ ውረድ የሚገኘው የሕዝብ ገንዘብ አለአግባብ እየባከነ ወጪው እየበዛ ይታያል፡፡ በበጀት የሚተዳደሩ መሥሪያ ቤቶች ገንዘባቸውን በቅንጦት እቃዎች ግዥ፣ በየሰበብ አስባቡ በከፍተኛ ሆቴሎች በመዝናናት እያባከኑ መሆናቸው እየታየ ዝም መባሉ እሮሮ ሲሰማበት ቆይቷል፡፡ ሸገርም በየዝግጅቶቹ በተደጋጋሚ አንስቷል፡፡ ዮሐንስ የኋላወርቅ ለዛሬ ያዘጋጀው ዘገባ ለረጅም ጊዜ ስሞታ የሚቀርብበትን የወጪ ማብዛት ጉዳይ ምላሽ የሚሰጥ ነው

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ውሸት ለመናገር አትሻም ምላሴ

እናት ልጇን… 

“ማሙሽ፣ ሂድና ከሸምሱ ሱቅ ስኳር፣ እጣንና፣ ሰንደል ገዝተህልኝ ና፡፡”
“እሺ፣ እማዬ፡፡”

ልጅ ይሄዳል፡፡ ተመልሶ ሲመጣ የያዘው ስኳርና ሰንደሉን ብቻ ነው፡፡ እንባ ህቅ፣ ህቅ ይለዋል፡፡

“እጣንም ግዛ ብዬህ አልነበር እንዴ፣ የት አደረግኸው?”
“እ..እማዬ፣ ልጆቹ ፍራንኩን ነጠቁኝ፡፡” የፓስቴው ዘይት እኮ ገና ሙሉ ለሙሉ ከከንፈሩ አልተጠረገም፡፡

እናት ጭኑ ስር ትገባና ልምዝግ… “ይሄን ውሸት ተው አላልኩህም! እ!... መዋሸት ይለምድብሀል አላልኩም!”

ቁንጥጫ ካልሠራ ቅጣቱ ወደ አለንጋ ‘አፕግሬድ’ ይደረጋል፣ በአለንጋም ካልሆነ ምን ችግር አለው… ያኔ በርበሬ እኮ በልተነውም ስለሚተርፈን እንደዕጣን ነገርም እንጠቀምበት ነበር፡፡

ቅጣቶቹ እንተዋቸውና... ትልቁ ነገር ግን ውሸት መናገር ምን ያሀል አስከፊ እንደነበር የሚያሳይ ነው፡፡ “መዋሸት ያድግብሀል አላልኩህም!” ከማለት የተሻለ ማገረጋገጫ ምን አለ!
እንደ ዘንድሮ ሳይሆን፣ “እከሌ ውሸታም ነው” ከተባለ እኮ መንደር ሙሉ ጣት ሲቀሳሰርበት፣ ከጀርባው ሲንሾካሾክበት ነው የሚውለው፡፡

“እከሊት የለየላት ቀጣፊ ነች፣” ከተባለች በቡናውም፣ በእድር እቃ አጠባውም በምናምኑም ስሟ ሲነሳና ሲወድቅ ነው የሚኖረው፡፡ የዛሬን አያድርገውና ውሸት እንዲህ ያስጠላ ነበር… ጊዜ ተለውጦ ከውሽት ጋር እንዲህ ከመዋደዳችን በፊት! ግን ውሸት ብዙ ነገር እያጠፋ ነው፡፡

የውሸት መግለጫና ማብራሪያ፣ የሀሰት መሀላ፣ የሀሰት ምስክርነት፣ የሀሰት ሰነድ፣ የሀሰት ማስታወቂያ፣ የሀሰት ምርት…ብዙ ነገሮች እየተበላሹ ነው፡፡

እንዲህ ሆኖ ታዲያ ውሸት…ተቀብለነው፣ ተግባብተነው አብረነው የምንኖረው አይነት ነገር እየሆነ ይመስላል፡፡ ከምናምናቸው ነገሮች የማናምናቸው ነገሮች እየበዙ ነው፡፡ እንዲህም ሆኖ “ምን ይደረግ፣ ጊዜው ነው፣ እያልን እናልፋቸዋለን፡፡

“ስሚ ያ የባንኩ ጉረኛ ከሚስቱ ሊፋታ ነው አሉ፡፡”
“በምን አወቅሽ?”
“ሰው ነገረኝ፡፡”
“ማን ነው የነገረሽ?”
“ያቺ ጎረቤቴ ነቻ…”

“ምነው! ምነው! እሷን ሰው ብለሽ የምትልሽን እሺ ብለሽ ትቀበያለሽ! አገር ያወቃት ቀዳዳ አይደለች እንዴ!”

ውሸት እንዲህ ያስጠላ ነበር…ዛሬ፣ ዛሬ ከማስወቀስ ይልቅ እሱ ነው ኖሮን ያወቀበት አስብሎ ኒሻን የሚያስጭን እየሆነ ነው እንጂ!

ውሸት ለመናገር አትሻም ምላሴ
ለእውነት እሞታለሁ አልሳሳም ለነፍሴ

ተብሎም ተዘፍኖ ነበር… ውሸት መናገር ነውር በነበረበት ዘመን፣ እውነተኝነት በያስከብርበት ዘመን፣ “እሱ እኮ የለየለት ቀጣፊ ነው” ከመባል የጠቆረ የስም ጥላሸት ያልነበረበት ዘመን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: ውሸት ለመናገር አትሻም ምላሴ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ከሐርላዎች ግፍ ምን እንማራለን…?

ሸገር ልዩ ወሬ፣ ‘ሐርላዎችን ያየ በእንጀራ ግፍ አይሰራም...’

ሐርላ በምስራቅ ኢትዮጵያ በአንድ ወቅት የነበረች ስልጡን ከተማ ነበረች፡፡ ቢያንስ ከ10ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ገናና የነበሩት ሐርላዎች በ16ኛው ክፍለዘመን እንደጠፉ ይነገርላቸዋል፡፡

አርኪዮሎጂስቶች በቅርቡ በቁፋሮ በርካታ ግንባታዎችና ከማዳጋስካር እስከ ቻይና ድረስ የመጡ ጌጣጌጦች የተገኙባት ሐርላ ሚስጥራዊ ነች፡፡ ስለሐርላውያንም በዝርዝር የሚታወቅ ነገር እምብዛም የለም፡፡

በምስራቅ ኢትዮጵያ በስፋት የሚነገረውና ስለሐርላውያን አጠፋፍ የሚገልፀው አፈታሪክ ግን የሐርላውያን መጥፋት ሰበቡ ግፍ ነው ይላል፡፡

አካላቸው ግዙፍ እና እጅግ ሐብታም ነበሩ የሚባሉት ሐርላዎች የመጥፋታቸው ሰበብ በሰርግ ድግሳቸው ላይ እንጀራ አንጥፈው ሰርገኛው በእንጀራው ላይ እየተራመደ እንዲሄድ ማድረጋቸው ነው የሚለው አፈታሪክ በዚህ ሳቢያ ፈጣሪ ተቆጥቶ ምድር ተገልብጣ ዋጠቻቸው ይላል፡፡

ለመሆኑ እውን የእነዚህ ድንገት ከታሪክ ገፅ የጠፉ ጥንታዊ ገናና ሕዝቦች ታሪክ ምን ይሆን ሲል የሸገሩ ወንድሙ ኃይሉ ይህን አጠናቅሯል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers