• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር | ወግ

ሁሉም በሽተኛ ሁሉም ራሴን ባይ በቤታችን ደህና መጥፋቱ ነው ወይ

ሰውየው ሠራተኛውን ወደ ወንዝ ይወስደዋል፡፡ አንዲህም ይለዋል፡፡
“ምን ይታይሀል?”
“ውብ የሆነ ወንዝ ይታየኛል፡፡”
“አሶች ይታዩሀል?”
“ምንም አሳ አይታየኝም፡፡”
ከዛም ውሀውን አልፎ ስር ውስጥ የሚያሳይ ፖላራይዝድ መነጽር ያደርግለታል፡፡
“አሁንስ ምን ይታይሀል?”
“አሶቹ ይታዩኛል፡፡”
ድንገትም ሁሉም ነገር ተለወጠ፡፡ ውሀ ውስጥ ያሉትን አሶች ሁሉ ማየት ጀመረ፡፡ ድንገትም ቀደም ብለው ያልነበሩ ሀሳቦች መጡ፡፡ በፊትም አሶቹ እዛው ነበሩ እኮ! ግን መነጽሩን እስኪያደርግ ድረስ ተደብቀውበት ነበር፡፡
ነገሮችን ላይ ላዩን ብቻ ሳይሆን በጥልቅት የምናይበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ ለማየት ደገሞ መነጽሩ ያስልገናል…የጋራ መነጽር፡፡ የጋራ መነጽር እንዲኖረን ደግሞ መጀመሪያ እርስ በእርስ መተማማናችን የግድ ነው፡፡
አዎ፣ እሱን ነው ያጣነው፣ መተማመን ነው ያጣነው፡፡ ከቤታችን የየግል ጓዳ እስከ አገራችን የጋራ አዳራሽ ድረስ ያጣነው መተማመን ነው፣ ለበርካታ ችግሮቻችን በጋራ መክረን፣ ዘክረን መፍትሄ ማበጀት ያልቻልነው በመሃላችን መተማመን ስለጠፋ ነው፡፡
‘መተማመን ጠፋ’ የሚለው ሀረግ ሊያከራክር ይችላል፡፡ መጀመሪያስ እዚህ አገር ውስጥ መተማመን የሚባል ነገረ ነበር ወይ? የሚል ሙግት ሊነሳ ይችላል፡፡
ግን እንደተባለው አሁን… ፈረንጅ እንደሚለው… በተስፋ ጣቶቻችንን አቆላልፈን ባለንበት ወቅት፣ “እስቲ ለጊዜውም ቢሆን ትናንትን ለትናንት እንተወውና ዛሬን እንይ፣ ነገን እንይ” በምንልበት ጊዜ መተማመን ከሌለ የትም አይደረስም፡፡ የአንዳችን ጥላ ሌላኛችንን የሚከብድ ከሆነ የትም አይደረስም፡፡
ሁሉም በሽተኛ ሁሉም ራሴን ባይ
በቤታችን ደህና መጥፋቱ ነው ወይ
ከማለት የሚገላግለንን ጊዜ እየናፈቅን ነው፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዓለም ዋንጫ…የእግር ኳስ ጥበብ፣ የፖለቲካ ትርምስ፣ የነውጠኝነት ስጋት

የሩስያው የዓለም ዋንጫ ደርሷል፡፡ በቢሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ይከታለዋል ተብሎ ነው የሚጠበቀው፡፡ ያለፈውን የብራዚል የዓለም ዋንጫ ወደ 3.2 ቢሊዮን ህዝብ አይቶታል ነው የሚባለው፡፡ በነገራችን ላይ ያለፈው የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ጀርመን ካሸነፈች እያንዳንዱ ተጫዋች 350‚000 ዩሮ ጉርሻ ያገኛል፡፡

ኔይማር ደግሞ ከብራዚል ጋር ዋንጫ ካሸነፈ ናይኪ 50‚000 ዶላር ይከፈለዋል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም የውድድሩ ምርጥ ተጫዋች ከሆነ ሌላ 200‚000 ዶላር ያገኛል፡፡ በእርግጥ ያጓጓል፡፡

በነገራችን ላይ በሩስያው የዓለም ዋንጫ አንድም እንግሊዛዊ ዳኛ የለም፡፡ አንድም! ፕሬሚየር ሊግ አንድም ለዓለም ዋንጫ የሚበቃ ዳኛ ይጣ! በቀድሞው ዘመን እኛም አኮ ለዓለም ዋንጫ ዳኛ ልከን ነበር! እንዲሁ ‘ነበር’ን ለለማብዛት እንለፈው እንጂ!

እግረ መንገድ…ያለፉት ውድድሮች እንደሚጠቁሙት ከሆን በዓለም ዋንጫው የተነሳ የሩስያ ህዝብ ብዛት ከዘጠኝ ወር በኋላ በጥቂተ መቶ ሺዎች ሊጨምር ይችላል፡፡ ምክንያቱም ከደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫ ዘጠኝ ወራት በኋላ በአገሪቷ የውልደት መጠኑ አሻቅቦ ነበርና፡፡

በ2006 ጀርመን ያዘጋጀች ጊዜም እንዲሁ በአንዳንድ የአገሪቱ ከፍሎች የውልደት መጠኑ በ30% አድጎ ነበር፡፡ እንግዲህ… ቤት ተቀምጦ ኳስ ሲያዩ ማምሸትና ውጪ ድራፍት ሲጨልጡ በማምሸት መሀል ያለው ልዩነት ማለት ነው፡፡ ይህ ግኝት እኛንም የሚመለከት ከሆነ ምን ማድረግ ይቻላል!… “ባሎች ቁጥራችን እንዳይጨምር ደጅ አምሹ፣” አይባል ነገር!

እንግዲህ በዓለም ዋንጫ ወቅት ገር፣ ገር የሆኑ ነገሮችን የምንጠብቅ ቢሆንም…ህይወት ኳስ ቦታም ይሁን የትም ስፍራ በአበቦች መሀል ሽርሽር አይደለችምና፡፡ የቴክኒኩን፣ የታክቲኩንና የመሳሰለውን ነገሮች ለባለሙያዎቹ ለስፖርት ጋዜጠኞች እንተወው፡፡ የዓለም ዋንጫ ግን እርካታ የሚፈጥረውን ያህል ደስ የማይሉ ክስተቶችም በየጊዜው ይታዩበታል…ጦር እስከማማዘዝ የደረሱ ክስተቶች፡፡

እጅግ አስቀያሚ የተባለው የቺሊው ዓለም ዋንጫ በእግር ኳስ ላይ የማይለቅ ጥቁር ነጥብ የተወ ነው ይባላል፡፡ ይህ የዓለም ዋንጫ እጅግ አስቀያሚና ከእግር ኳስ ጥበብ ይልቅ ቅልጥም ሰበራ የበዛበት ነው ተብሏል፡፡ በወቅቱ ‘ዘ ኤክስፕሬስ’ የተባለው የእንግሊዝ ጋዜጣ “ከስፍራው የሚመጡ ዘገባዎች ከጦር ሜዳ የሚላኩ ይመስላሉ፣” ብሎ ነበር፡፡

ለምሳሌ የጣልያንና የጀርመን ግጥሚያ ‘ነጻ ትግልና ጦርነት’ ነው የተባለው፡፡ “ተጫዋቾች ከመጫወት ይልቅ እግራቸውን ለማትረፍ ኳሷን እየሸሹ ይዘሉ የነበሩበት ጨዋታ ነው፣” ብሏል ጋዜጣው፡፡ ተጫዋቾች የሚሄዱት ለኳስ መሆኑ ቀርቶ ለእግር ነበር፡፡ በመጀመሪያ ሁለት ቀናት በተደረጉ ስምንት ግጥሚያዎች ብቻ አራት ቀይ ካርዶች ነው የተሰጡት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: የዓለም ዋንጫ…የእግር ኳስ ጥበብ፣ የፖለቲካ ትርምስ፣ የነውጠኝነት ስጋት

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

‘ዘ ኒው ኖርማል’

የኑሮ መወደድ ነገር፣ በየጓዳው ያለው ችግር መባባስ፣ የህዝባችን መቸገር ነገር…‘በኢመርጀንሲ’ ደረጃ፣ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ የነፍስ አድን ዘመቻ ደረጃ እየደረሰ ይመስለናል…በነገራችን ላይ… እንቁላል መመገብ እንደ ቅንጦት ሊቆጠር የሚችልባት አገር የእኛዋ ብቻ ሳትሆን አትቀርም፡፡ ወተት በቋሚነት መጠጣት ለተመቻቻው ብቻ የተፈቀደ የሚመስልባት ሀገር የእኛዋ ብቻ ሳትሆን አትቀርም፡፡ የሆነ ነገር ነው፡፡ ሰውየው ያማቸውና ሆስፒታል ይሄዳሉ፡፡ ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ ሀኪሙ ሰውነታቸው በሽታ የመቋቋም አቅም እንዳነሰው ከነገራቸው በኋላ ምክር ይሰጣቸዋል፡፡

“አባቴ፣ የበሽታ መቋቋም አቅምዎን እንደገና መገንባት አለብዎት፡፡ እንቁላል፣ ወተት፣ ሥጋ የመሳሰሉ ገንቢ ምግቦች ያዘውትሩ…” ምናምን ይላቸዋል፡፡ እሳቸውም በጥሞና ካዳመጡ በኋላ “እሺ ዶክተር፣ ያልካቸውን ምግቦች በሙሉ አመገባለሁ፡፡ አንተም እስቲ በነካ አፍህ ወጪውን ሸፍንልኝ አሉት፡፡ ሀኪሙ መስጠት ያለበትን ሙያዊ ምክር ሰጥቷል፡፡ እኛ ዘንድ ደግሞ “እንቁላል ብሉ፣ ሌላ፣ እንቁላል መብላት መቻል ሌላ፣” እያልን ነው፡፡እና ‘ዘ ኒው ኖርማል’ የሚሉት ነገር አለ፡፡ ይሄ ነገሮች መሆን ባይገባቸውም ምንም ማድረግ ስለማይቻል የግድ ይለመዳሉ፣ መደበኛም ይሆናሉ - አይነት ነገር፡፡

ለምሳሌ የመብራታችን ነገር ‘ዘ ኒው ኖርማል’ ሆኗል፡፡ ቀደም ሲል ለአንድ ሰዓት ጠፋ፡ ለሁለት ሰዓት ጠፋ እያልን እንበሳጭ ነበር፡፡ የአሁኑ ግን የሚገርም ብቻ ሳይሆን ግራ የሚገባ አይነት ነው፡፡ በቀደሙት ጊዜያት ጮሌ ወጣቶች መሬት ላይ ካርታ በትነው “በጨ፣ ጠቆረ” የሚሏት ነገር ነበረቻቸው፡፡ መብራታችን “በጨ ጠቆረ” እየመሰለ ነው፡፡ በራ፣ ‘ጠፋ/ ጠፋ፣ በራ፡፡’ አይነት ነው፡፡ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ምን ያህል ጊዜ እንደሚጠፋና እንደሚበራ መቁጠሩ ራሱ ሥራ ሆኗል፡፡

ልክ ምን ይመስላል መሰላችሁ…የሁላችን መብራት መቆጣጠሪያው የሆነ ቤት ሆኖ ልጆቹ ሲሯሯጡ ገመዱ ከሶኬቱ ተጎትቶ ይወጣል…እናንተ ትቆጣላችሁ፡፡ “እናንተ ልጆ ኧረ አባካቸሁ ቀስ ብላችሁ ተጫወቱ!…” ይባልና እንደገና ሲሰካ መብራት ይመጣል፡፡ የዘንድሮ ልጆች ደግሞ አያርፉም አይደል… እነደገና ሰሯሯጡ አሁንም ገመዱ ከሶኬቱ ይለያያል፡፡“እንደው እነኚህን ልጆች ምን አባቴ ባደርጋቸው ይሻላል!” አሁንም ሲተከል መበራት ፏ ይላል፡፡

ይሄ የለየለት የሞኝ አስተሳሰብ ሊመስል ይችላል፡፡ ምን እናድርግ! በዚች “ጫፍ ወጣች፣” “ተመነጠቀች፣” “ዓለምን ጉድ አሰኘች፣” ምናምን በሚባለበት ጊዜ፣ ያውም በዋና ከተማዋ እንዲሀ ሲሆን ምነው እንኳን ሞኝ ሌላ አንሆን! በዛ ሰሞን ከወደመካከለኛው ምስራቅ ከብዙ ዓመታት በኋላ የመጣ ወዳጃችን “አናንተ ዘንድ መብራት በስንት ጊዜ ነው የሚጠፋው?” ብንለው…ስቆ ወሬ ቀየረ፡፡ በመሆኑም አሁን መበሳጨት ብቻ አይደለም፣ መናደድ ብቻ አይደለም…የሚሰማንን ስሜት መግለጽ ሁሉ አቅቶናል፡፡....

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ቺቺንያ ሌላ፣ እኛ ሌላ!

‘ዳያስፖራ’ ነው፣ ከረምረም ብሎ ሊያየን ይመጣል፡፡ ከወዳጆቹ ጋር ማታ፣ ማታ ዞር፣ ዞር ይላል፡፡ እና በእሱ ድምዳሜ አገራችንን አያት፣ የቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ፣ የቺቺንያ አካባቢ ሌሊት ህይወት የእኛ ኑሮ መለኪያ ሆነለት፣ ወሰነም… “ተመችቷችሁ የለም እንዴ!” አለ፡፡

“ኸረ እባክህ አልተመቸንም! የእኛን ኑሮ ለማወቅ የሌሊቷን ቺቺንያ ሳይሆን የቀኗን የእኛን ጓዳ ጓዳችንን ተመልከት” ተባለ፡ በእጄ አላለም፡፡ እዚህ አገር እንዴት አስቸጋሪ እንደሆነችና እሱ እድለኛ እንደሆነ ምናምን ነገር ይነግሩታል፡፡ ለካስ እሱ አሜሪካ አልተመቸችውም፡፡ ምን በል ጥሩ ነው… “እናንተ ምን አለባችሁ!”

“እናንተ ምን አለባችሁ!” ብሎ ነገር ምንድነው? ብዙ፣ በጣም ብዙ ነገር አለብን እንጂ!ኑሮ እያደቀቀን፣ ብሶታችንን የሚሰማን እያጣን… “ኸረ ወገኖቻችን ከሰውነት ውጪ ሆኑ!” የሚል እያጣን ብዙ፣ በጣም ብዙ ነገር አለብን እንጂ!

መፈጠርን የሚያስጠላ ደረጃ የሚያደርስ የቤት ኪራይ አለብን፡፡ ያውም በየሦስት ወሩ የሚጨምር…ያውም አሮጌ ወንበር ስናስጠግን በታየ ቁጥር የሚጨምር…ያውም ግንባራችን ላይ የተንጠፈጠፈው ላብ የምቾት ሆኖ በታየ ቁጥር የሚጨምር፡፡

የሆነ ታሪክ ነው…እዚቹ አዲስ አበባ ውስጥ፡፡ ሰውየው አንዲት በጣም ጠባብ የሆነች፣ እግር እንኳን ሙሉ ለሙሉ የማይዘረጋባት ክፍል ተከራይቶ ይኖራል፡፡ ያከራዩት እናት ማንንም ሰው እንዳያመጣ አስጠንቅቀውታል፡፡ አንድ ጊዜ የሆነ ወዳጁ ችግር ይገጥመውና ደብቆ ሊያሳደረው ቤቱ ይወስደዋል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

“የመንግሥት ተግባር ጣፋጭ ማር ስኒ ውስጥ ማንቆርቆር ብቻ አይደለም…”

ኦፊሴላዊ ሪሴፕሽኖች ላይ ከሰው ጋር ለመቀላቀል መለኪያ ከመጨበጣቸው በስተቀር አልኮል በዞረበት አይዞሩም የሚባሉት ፑቲን ጠዋት ቁርሳቸውን ተመገበው ቡና ከጠጡ በኋላ ወደ አካል እንቅስቃሴ ነው የሚገቡት፡፡ ለሁለት ሰዓት ገደማ ይዋኛሉ ነው የሚባለው፡፡ ዋኝተው ሲጨርሱም ወደ ጂም ገብተው ክብደት ያነሳሉ…

እዚሀ ላይ አንድ አስገራሚ ነገር … ሰውዬው አገራቸውን በተመለከተ ብዙ ነገሮችን የሚያስቡትና እቅዶችን የሚነድፉት ውሀ ውስጥ እየዋኙ ባሉበት ጊዜ ነው…

ሮስቶቭ በምትባል የሩስያ ከተማ ነው፡፡ የሩስያው መሪ ቭላዲሚር ፑቲን ኮምባይን ሀርቨስተር እንዴት እንደሚያንቀሳቅሱ በሲሙሊቴር እየተማሩ ነበር፡፡ እናም ፑቲን መሪውን ጨበጡና እሳቸው ላይ ተደግነው ወደነበሩት ካሜራዎች ዘወር አሉ፣ ተናገሩም… “ነገሩ ሁሉ የሚበላሽ ከሆነ ከመጋቢት 2 በኋላ ኮምባይን ኦፕሬተር ሆኜ እሠራለሁ፡፡”

አሰልጣኝ የተባለው ሰውም “ምንም ችግር የለውም፣” አላቸው፡፡ የአገሪቱ ዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ጣቢያ አር.ቲ ይህነኑ አስተላላፈው፡፡ ምዕራባውያኑም “ቀልዱን ተዉ፣” አሉ፣ “አሁን ማን ይሙት ፑቲን ነው ክሬምሊንን የሚለቀው ተባለ፡፡

ቢወጡስ ምን አለበት! የምራባውያኑ መገናኛ ብዙሀን “ሰውየው እኮ ቅልጥ ያለ ዲታ ነው፣” ይሏቸው የለም እንዴ! እንደውም ወደ 40 ቢሊዮን ዶላር ገደማ አለው ነው የሚሏቸው፡፡
በእርግጥ በእርግጥ ይህን ያሀል ሀብት እንዳለቸው የሚያሳምኑ ብዙ ተጨባጭ የሚባሉ መረጃዎች እስካሁን አላቀረቡም፡፡ ፑቲን ግን ዶላር የሚያስነጥሰው ሀበታም ነው ሲሏቸው ዝም አላሉም፣ መልስ ነበራቸው… “አዎ፣ በአውሮፓ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ትልቁ ሀብታም ነኝ፣ ስሜቶችን እሰበስባለሁ፡፡”

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers